IBD & Menses
Crohn’s & Colitis Ethiopia
#quickfact የወር አበባ ዑደትና የአንጀት ቁስለት
መፍትሔዎች
🟣 ህመሙ ከፍተኛ ከሆነ፣ ሀኪምን አማክሮ የህመም ማስታገሻን መውሰድ፤
🟣 የእርግዝና መከላከያዎች ፡- እርግዝናን ከመከላከል ባሻገር ከሰውነታችን ሆርሞኖች ጋር መስተጋብር ስላላቸው የወር አበባ ዑደትን መዛባት የማተካከልና በዑደቱ ወቅት የሚከሰተውን ከፍተኛ የሆነን ቁርጥትና ህመም የመቀነስ ባህሪይ አላቸው፡፡ ሆኖም እነዚህን የእርግዝና መከላከያዎች ካለሃኪም ትዕዛዝ መውሰድ በፍፁም አይመከርም፡፡
🟣 የአመጋገብ ለውጥ ፡- እንደሚታወቀው የአንጀት ቁስለት ህመምን ለመቆጣጠር፤ ከመድሃኒቶች ባሻገር የአመጋገብ ስርዓትን መከታተልና ማስተካከል እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ በተለይም በወር አበባ ወቅት ደግሞ ህመሙ ይበልጥ እንዳይባባስ ቀስቃሽ የሚሆኑብንን ምግቦች መለየት እና ማስወገድ ይመከራል፡፡
🟣 በቂ ውሃን መጠጣት፡- በተለይም እንደ ቡና ያሉ መጠጦች የሆድ እቃን እንቅስቃሴ በመጨመር ተቅማጥ የሚያስከትሉብን ከሆነ ከመጠጣችን ውስጥ በማስወገድ በምትኩ ዉሃን መጠቀም እንችላለን፡፡
🟣 ተጨማሪ ንጥረ ነገር ያላቸው ማሟያዎች ፡- የአንጀት ቁስለት ባጋጠማቸው ታካሚዎች ዘንድ፣ በአንጀት ቁስለቱ የተነሳ ሰውነታችን ከምግባችን ውስጥ ሊያገኛቸው የሚገባውን ንጥረ ነገሮች ሳያገኝ ሊቀርና አንጀታችን እነዚህን ንጥረ ነገሮች በአስፈላጊው ልክ ወደ ደማችን እንዲመጠጥ ለማድረግ ሊቸገር ይችላል፡፡ ስለዚህም በወር አበባ ዑደት ወቅት አስፈላጊ የሰውነት ንጥረ ነገሮች እጥረት እንዳይከሰት፣ ከሃኪማችን ጋር በመመካከር ተጨማሪ ንጥረ ነገር ያላቸውን ማሟያዎች መውሰድ ይቻላል፡፡
🟣 የስሜት ለውጦቻችንን ማስተዋልና በአጠገባችን ካሉ ሰዎች እርዳታን መጠየቅ፡- በተለይም የቤተሰብ አባላትና የትዳር አጋሮች ይህንን በወር አበባ ምክንያት የሚከሰት የስሜት ለውጥን ጤናማ የሰውነት ለውጥ እንደሆነ በማገናዘብ ለሴት እህቶች ድጋፍ ማድረግ፤ እንዲሁም ሴቶችም በተለይም በአንጀት ቁስለት ንቁ ደረጃ ላይ የወር አበባን ዑደት ማስተናገድ አስቸጋሪ ቢሆንም፤ ንቁ በመሆን፣ተዝናኖትን ለሰውነት በመስጠት፣ እረፍት በማድረግና ወደ ተባባሰ የድብርትና የድባቴ ስሜት ላለመግባት መልካም የሆኑና የምናመሰግንባቸው ነገሮች ላይ ትኩረት ማድረግ አለብን፡፡