Hrj h1

የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
በፍ/ባለመብት አቶ ሙሉቀን ቦጋለ እና በፍ/ባለዕዳ ወ/ሮ ብርሃነሽ አባተ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 125082 በ20/8/2009 ዓ.ም መ/ቁ 29714 በ 09/09/2008- ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 7 የቤ.ቁ አዲስ የሆነ ቤት ሶስት ክፍል ቤት የተጠሪ ሲሆን ሁለት ክፍል ቤት እና ኣንድ ሽንት ቤት ሰነድ አልባ የቦታ ስፋት በፕሮፖርሽን 51 ካ.ሜ የሆነው የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 17,568.84(አስራ ሰባት ሺህ አምስት መቶ ስልሳ ስምንት ከሰማንያ አራት ሳንቲም ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ለሚያዝያ 29 ቀን 2012 ዓ. ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ በ4:30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
የሐራጅ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬከቶሬት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሦስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት. ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ሰዓት ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን፤እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4 ኛውን በባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት።
በተጨማሪ ተጫራቾች ካፒታል ጌይን እና ታክስ ስምን ይዛወርልኝ የሚልን ጥያቄ፣ ሐራጁ ጐድቶኛል የሚሉ ጥያቄዎችን ዳይሬክቶሬቱ የማያስተናግድና በችሎት የሚጠየቅ መሆኑን እንገልፃለን።
የኢ. ፌ. ዴ. ሪ ጠቅላይ ፍ/ ቤት የፌዴራል ፍ/ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት
_______________________________
Category : Foreclosure., House and Building Foreclosure, House and Building., House and Building Sale, Sale.
Posted Date : አዲስ ዘመን መጋቢት 24፥2012
Deadline :2020-05-07