Honey

Honey

Crohn’s and Colitis Ethiopia

የማር የጤና ጥቅሞች


ማር በውስጡ የተለያዩ ንጥረ ምግቦችን ይዟል


ማር በዋነኝነት ያልተደባለቀ ስኳር ይዟል፤ በውስጡም ስብ የለውም በተጨማሪም ሙጥቅላ ፕሮቲን እና አሰር/Fiber/ ይዟል።


በፀረ-ኦክሲደንት/Anti-oxidant/ የበለጠገ ነው


ከፍተኛ ጥራት ያለው ማር በዝግጅት ሂደት ውስጥ በብዙ ያላለፈ፣ ሙቀት ያላገኘው እንዲሁም ትኩስ ማር በውስጡ ብዙ ጠቃሚ የዕፅዋት ህይወት-ገቢር ውህድ/Bioactive compounds/ እና ፀረ-ኦክሲደንት ይዟል። ፀረ-ኦክሲደንት በተለያዩ የሰውነታችን ህዋሶች ውስጥ የሚከማቹ እንዲሁም ጉዳት የሚያድረስ እፀግባሪ የኦክሲጅን ዝርያዎች/Reactive Oxygen Species(ROS)/ የተሰኙ ኬሚካሎችን በማርከስ የበኩሉን አስተዋፆ ያደርጋል። እፀግባሪ የኦክሲጅን ዝርያዎች በሰውነታችን ከሚያደርሱት ጉዳቶች መካከል ያለጊዜው እርጅና፣ የስኳር ህመም እና የልብ ህመም ተጠቃሽ ናቸው።


በደማችን ውስጥ ለሚገኘው መጠነኛ የስኳር መጠን፣ ከመደበኛ ስኳር ማር የተሻለ ነው


በደማችን ያለውን የስኳር መጠን ከመቆጣጠር አኳያ ማር ከመደበኛ ስኳር የተሻለ ጠቀሜታ አለው። በውስጡ የያዘው ፀረ-ኦክሲዳንት የስኳር በሽታን እንዲሁም ሜታቦሊክ ሲንድሮም'ን በመከላከል ረገድ የበኩሉን አስተዋጽኦ ያደርጋል ሆኖም ግን ምንም ያህል ከመደበኛ ስኳር የተሻለ ጠቀሜታ ቢኖረውም፤ በስኳር ህመም የተያዙ ሰወች ማር'ን በመጠኑ መጠቀም ይኖርባቸዋል።


ማር'ን መጠቀም የላቀ የምግብ ይዘትነት እንዲሁም ለጤና ጠቀሜታ አለው


በማር ውስጥ የሚገኘው እፀ-ኬሚካል/phytochemical/ መጠን በአበባ ምንጩ፣ በማሩ አይነት እንዲሁም የንቦቹ ዝርያ ላይ ይወሰናል። እንዚህ ምክኒያቶች የእያንዳንዱ የማር ዓይነት ህይወታዊ ገቢርነቱ/Biological Activities/ ላይ ተፅዕኖ ያኖራሉ። በመሰረቱ አብዛኛው የማር ለጤና ጠቃሚ የሆኑት ባሕሪያት ከPolyphenols የመነጩ ናቸው።


ጥናቶች እንዳረጋገጡት በማር የሚገኙ የPolyphenols መጠን ወደ ሰውነታችን የደም ዝውውር ስርዓት ውስጥ በመስረፅ የሚገኘው መጠን ከሌሎች ተግባራዊ ምግቦች እጅግ የላቀ ነው፤ ይህም በማር ውስጥ የሚገኘው Polyphenol እንደ ማውጣት/Extraction/ እና መረቅ/decoction/ ያሉ ጥራቱን የሚቀንሱ ኬሚካላዊ ለውጦች የተጋለጠ አይደለም። በዚህም ምክኒያት በሰውነታችን እንደ አንጀት መቆጣት ያሉ የጠኑ የሰውነት መቆጣት ታማሚዎች ከማር የሚገኘውን የመድሃኒትነት እንዲሁም በሰውነታችን የሚለቀቁ ብግነትን የሚያባብሱ ሳይቶካይንስ/Cytokines/ የሚባሉ ንጥረ ነገሮችን በመቆጣጠር ብግነትን የመከላከል ጠቀሜታውን መቋደስ ያችላሉ።



በተጨማሪም ማር'ን ወደ እለት ምግባችን ለመጨመር ቀላል ነው


ከማር የሚገኘውን የፀረ-ኦክሲዳንት ጥቅም ትንሽ መጨመር ለማግኘት መደበኛ ስኳር'ን በምንጠቀምበት መንገድ መጠቀም እንችላለን። ሻይ፣ ቡና እንዲሁም ተራ እርጎን ለማጣፈጥ ተመራጭ ነው። ምግብ ስናበስል እንዲሁም ስንጋግር መጠቀም እንችላለን።


በቤት ውስጥ እንደሚሰጡ መፍትሔዎች፤ አነስተኛ መቃጠል እንዲሁም ቁስል ባሉበት ቦታ ማሩን በቀጥታ መቀባት እንችላለን በተጨማሪም ለሳል ህመም በአፋችን መውሰድ ይቻላል። ማስታወስ ያለብን ነገር ቢኖር፣ ማር ከአንድ ዓመት በታች ላሉ ህፃናት ቦቱሊስም ለተሰኘ የሰውነት ነርቮችን የሚያጠቃ በሽታ ተጋላጭ ስለሆኑ ማር መሠጠት የለበትም። በመጨረሻም ለረጅም ጊዜ ብዙ መጠን ማር መጠቀም ለሰውነት ክብደት መጨመር ስለሚዳርግ መካከለኛ አልያም አነስተኛ መጠን መጠቀም ተገቢ ነው።

Report Page