Holiness Abune Mathias
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ምንድነው ያሉት ?

" ከቅርብ ቀናት በፊት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል አካባቢ በተፈፀመው ዘግናኝ እና እጅግ የሚያሳዝን ድርጊት ሀዘኔን ለመግለፅ ነው።
በዚህ በያዝነው ወር መጋቢት /2014 ዓ/ም 12 የሚሆኑ የትግራይ ተወላጆች በግልገል በለስ ማረሚያ ቤት ታስረው ከሰነበቱ በኃላ ፍርድ ቤት በነፃ ለቋቸው ማስረጃ ሰጥቷቸው ወደ ቤታቸው ሲሄዱ መንገድ ቆይተው የመንግስት የፀጥታ አካላት ሌሎችም የተጨመሩ አሉ እየተባለ ነው ገለዋቸዋል። ከእነሱ አንዱ ለማምለጥ ሞክሮ ከተሸሸገበት አግኝተው ከነህይወቱ አይኑ እያየ ከነህይወቱ በቁመናው በእሳት እንደእንጨት ማገዶ ወርውረውት አብረው በጥይት ተገለው በእሳት ከተቃጠሉት መሀከል ውስጥ ጥለው ኧረ ባካችሁ ተውኝ ማሩኝ እያሉ እየለመነ በጭካኔ በአረመኔነት ወደእሳት ወርውረውት እሱም አብሮ ተቃጥሎ አልፏል።
ይሄ አለምን ያስደነቀ፣ አለምን ያሳዘነ ድርጊት ነው። የአረመኔነት ድርጊት ነው። መቼም ባለፈው 2013 ዓ/ም ጦርነቱ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ያላየነው ያልሰማነው ካሁን ቀደም ታይቶ ተሰምቶ በማይታወቅ ሁኔታ በትግራይ ህዝብ ላይ የደረሰው መከራ እጅግ የሚያሳዝን እጅግ የሚያስለቅስ መፈጠረን ሁሉ የሚያስጠላ ድርጊት ተፈፅሟል ነገር ግን ይሄ ደግሞ ከሁሉ የባሰ ድርጊት ተፈፅሟል በአሁን ጊዜ።

ባለፉት ወራት የተፈፀመው (አንድ አመት ከ5/6 ወር በትግራይ የተፈፀሙት ድርጊቶች ተቆጥረው ተሰፍረው የማያልቁ ናቸው። ድርጊቱም እጅግ አሳዛኝ ነው። ጦርነቱ እንዳለ ሆኖ ወጣቶች በጎን ከጦርነቱ ጎን ወደ መንደር እየተኬደ ወጣቶች እየተለቀሙ እንደ አውሬ እየታደኑ እየተገደሉ ወደ ገደል እየተጣሉ እንደነበር እናውቃለን። ለዚህ ማህበረ ዴጉየ ምስክር ነው። ይህም በአለም ጋዜጠኞች የታየ የተረጋገጠ ነው። በCNN እና በበርካታ የውጭ ሚዲያዎች የተረጋገጠ ነው።
እንደገና ደግሞ የጅምላ ግድያ በአክሱም አውደምህረት የተፈፀመው ከ800 - 1000 ህዝብ ተረሽኗል። እንደገና በማርያም ደንገላት ደግሞ ምእመናን ቅዳሴ አስቀድሰው ወደ አውደምህረቱ ከወጡ በኃላ ሴት የለ ወንድ የለ ህፃን የለ ሽማግሌ የለ ወደ 150 የሚሆኑ ካህናት እና ምእመናን እንደተረሸኑ ያለፈው ታሪክ ነው የሚታወስ ነው ምንም የማይረሳ ዘግናኝ የሆነ ግድያ ነው።
እንደገና ደግሞ በየገበያዎች የህዝብ ስንት ሺዎች በተሰበሰቡበት ገበያ በድሮን ያለቁት ወገኖቻችን ስፍር ቁጥር የላቸውም። እንደገና ከዚህ ሁሉ አልፎ ነገሩ ተቆጥሮ የሚያልቅ አይደለም ዘረፋው፣ ግድያው ፣ የሴቶቹ መደፈር ምናልባት ሪፖርት ያደረጉት ወደ ክሊኒክ እና ሆስፒታል ያስመዘገቡትን የወሰድን እንደሆነ 120 ሺ ሴቶች እንደተደፈሩ ተነግሯል ይሄ እንግዲህ ሪፖርት ያደረጉትን ነው በየገጠሩ በየአካባቢው የተፈፀመውን ተቆጥሮ አይደለም እንጂ ስፍር ቁጥር የላቸውም የተደፈሩት ሴቶች እጅግ የሚያሳዝን እጅግ የሚዘገንን ነው።

ንብረት አልቀረም ፤ ሹካ ሳይቀር ፣ ሲኒ ሳይቀር ፣ ካልሲ ሳይቀር ምኑ ቅጡ የሚችሉትን ያህል ይወስዱታል ያልቻሉትን ያህል በእሳት ያቃጥሉታል በጎተራ የተቀመጠው እህል ደግሞ እንዲበቅል እና ሰው እንዳይጠቀምበት ውሃ እየጨመሩ ይሄዳሉ።
እንደገና ደግሞ ዱቄትን ከአመድ ጋራ እየደባለቁ ሰው እንዳይጠቀምበት አበላሽተው ይሄዳሉ። ዱቄቱን ከአፈር ጋራ እየጨመሩ ሰው እንዳይጠቀምበት እያደረጉ እያበላሹ ሄደዋል። ከበቶቹ እየተነዱ፣ ተወስደዋል፣ ታርደዋል ፣ በሬዎች ሁሉ አልቀዋል የሚችሉትን አርደው በልተዋል የቀሩትን አጓጉዘዋቸዋል። አህዮች ሳይቀሩ አስመራ ተጉዘዋል፣ ስፍር ቁጥር የሌላቸው አህዮች፣ በሬዎች፣ ላሞች፣ በጎች ሁሉ ወደ አስመራ ተጉዘዋል።
ይሄ ሁሉ ነገር ቆጥሬም የምጨርሰው አይደለም ይሄ ጉዳይ ብዙ ነው፤ ጣጣው ብዙ ነው።
ክሊኒኮች ሆስፒታሎች፣ ትምህርት ቤቶች፣ መድሃኒት ቤቶች ወመዋል፣ ፋብሪካዎች በጠቅላላ ወድመዋል፣ የቀረ ነገር የለም በትግራይ ውስጥ ፤ አሁን ደግሞ እንደገና ህፃናት በእናቶች እቅፍ ሆነው፣ ምግብ አጥተው እያለቀሱ እንደቅጠል ደርቀው በምግብ እጦት በእናቶቻቸው እቅፍ ሲሞቱ እናቶቻቸው እያለቀሱ ጡት እንዳያጠቧቸው እነሱም እራሳቸው በረሃብ ስለደረቁ ወተት የለም እንደዚህ እየታየ ነው ያለው።

የዓለም በጎ አድራጊዎች የሰጠው ምግብ እና መድሃኒት እንዳይገባ ተክልክሎ ይኸው ሰው እየረገፈ ይገኛል። በህመም የሚሞቱት ፣ በረሃብ የሚሞቱት ፣ በመድሃኒት እጥረት የሚሞቱት ስፍር ቁጥር የላቸውም። እና ይሄን ሁሉ አይተናል፤ ለምደነዋል።
አሁን ደግሞ ይባስ ብሎ ከነህይወቱ ሰውን ወደ እሳት መክተት ፣ እንደ እንጨት እንደማገዶ እንጨት ወደ እሳት አይዩ እያየ ህይወቱ ሳያልፍ ፣እንዳለወደ እሳት መክተት ይባስ ይሄብ አይተናል።
በእውነቱ ይሄ መፈጠርን የሚያስጠላ ነው ይሄ ፤ ለምን ተፈጠርን ፤ እንግዲህ ትግሬዎችን ለማጥፋት ተብሎ፣ ትግሬዎችን ለማውደም ከምድረገፅ ለማጥፋት ተብሎ የተጀመረው ጦርነት አሁን በመላ ኢትዮጵያ ተስፋፍቶ ፣ በአብዛኛው በኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ ሁከት ፣ እና ብጥብጥ ፣ ረሃብና ችግር በአብዛኛው የኢትዮጵያ ክፍል እየደረሰ ነው ያለው። በኦሮሚያ ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ...በተለያዩ አካባቢዎች እየደረሰ ያለው ሁከት እና ጥብጥብ፣ እልቂት ብዙ ነው። በሁሉም እየደረሰነው ያለው፤ ሁሉንም አዳርሷል አሁን። ይሄ ደግሞ የሚያሳዝን ነው፤ ይሄ ሊሆን የማይገባው ድርጊት ተፈፅሟል።

በዓለም ታይቶ የማይታወቅ፣ ደርሶ የማይታወቅ ጄኖሳይድ ወይም የህዝብ ዘር ማጥፋት እርምጃ ተወስዷል። የታሰበው ነገር ሁሉ ሳይሳካ ስለቀረ ወጣቶቹን፣ ከአምስት አመት በላይ የሆነውን ወንድ ልጅ ሁሉ ግደሉ ተብለናል እያሉ በአፋቸው እየመሰከሩ ህፃናትን ከየመንደሩ፣ መከላከያ የሌላቸው ፣ ጥይት ሳይተኩሱ ድንጋይ ሳይወረውሩ ወጣቶች እየተለቀሙ ወደ ገደል ተጥለዋል፣ በእሳትም ተቃጥለዋል፤ የኃይሊት እየታሰሩ ለምሳሌ በሁመራ ነዋሪዎች ሁሉ ሁለት እጃቸው በኤሌክትሪክ ገመድ እየታሰረ በጥይት መተው ሲያበቁ ወደ ተከዜ ወንዝ ተጥለዋል። ስፍር ቁጥር የሌላቸው የሁመራ ነዋሪዎች አሁንም እየተደረገ ነው ያለው ይሄ ጉዳይ አላባራም።
እንዲህ አይነቱ ጭካኔ የአረመኔ ስራ ነው። በእውነቱ አራዊት እንኳን በተፈጥሮ መሰሉን አይበላም፤ ሌላውን ነው እንጂ ነብር ነብርን አይበላም ፣ አንበሳም አንበሳን አይበላም፡ የተፈጥሮ መሰሉ ስለሆነ ሰው በሰው ላይ እንዲህ አይነት ድርጊት መፈፀም ማለት ምን ማለት ነው ? አሁን እግዚአብሔር ያሳየን ይሄንን አለም ያስገረም ያስደነቀ ፣ ያስደመመ ሰው አይኑ እያየ ከነህይወቱ እንደ ማገዶ እንጨት ወደእሳት መክተት ማለት ምን ማለት ነው ? ይሄን አረመናዊያ እንኳን የማያሰርጉት ነው። እንዲህ ያለው ነገር ተደርጎ የማይታወቅ ነው። በጣም ከልክ ያለፈ ጭካኔና ከልክ ያለፈ ጥላቻ ነው።
ነገሩ የባሰ እየባሰ ነው እየሄደ ያለው። ሀገሪቱ መቼስ ከሚገባ በላይ ተጎድታለች እንጂ አልበለፀገችም። ትግራዮችን ለማጥፋት ተብሎ ጥፋቱ የጋራ እየሆነ ነው ያለው። እኔ በዚህ ጉዳይ እጅግ አዝኛለሁ። እኔ እስካሁን ድረስ እንዲህ ያለውን እድል ብዙም አላገኘሁም። አንድ ጊዜ ነው ሾልካ የወጣች ነገር ነበረች እንጂ እስካሁን ድረስ እንዲህ አይነት እድል አግኝቼ አላውቅም።

እኔ ከእንግዲህ ወዲህ ያለው ችግር በበቃን፣ ቢበቃ ጥሩ ነው ፤ የተረፈው ህዝብ እንኳን በሰላም እንዲኖር የተረፉ ልጆች በሰላም እንዲያድጉ ቢደረግ ፣ ሰላም ቢፈጠር እንዴት ጥሩ ነበር እላለሁኝ።
መቼስ ያለው ጥላቻ ጣራ የነካ ስለሆነ፣ ከመጠን በላይ እያለፈ ስለሆነ፣ በጥላቻ ሀገር አያድግም ከሚወድቅ በቀር ሀገር አያድግምና ማነው የሚጠቀመው በጥፋት ? በመገዳደል ? ፣ በመጠፋፋት ? የሚጠቀም ሰው ማነው ? ደግሞ ሰው እግዚአብሔር የፈጠረውን ሰው ከእግዚአብሔር ጋር ነው ጠቡ እኔ እንደሚመስለኝ ትግሬዎች የሚባሉቱ ሰዎች ለምን ተፈጠሩ ፣ እግዚአብሔር ለምን ፈጠረ ፣ ትግራይ የምትባል ሀገር ቋንቋ ለምን ተፈጠረ ? ከእግዚአብሔር ጋር ነው ጠቡ ይመስለኛል እኔ ፣ ከእግዚአብሔር ጋር ጠብ ደግሞ የሚያዋጣ አይደለም ።
እና ይሄ ሁሉ ተፈፅሟል፤ እየተፈፀመም ነው ያለው ፣ ከሁሉ ከሁሉ የሚያሳዝነው ቅድም እንደጠቀስኩት ፣ በጎ አድራጊዎች የሰጡትን እርዳታ የምግብ፣ የመድሃኒት፣ የመሳሰሉት ነገሮች ሁሉ በመንገድ ላይ መኪኖች ተገድግደው እየተንጠቀጠቀጡ በጭነት ሰው በዚህ በኩል ይሞታል፤ ለምን ? ለምንድነው ይሄ ? ልክ አይደለም። መቼም ሰው ጠፍቶ አይጠፋም፤ ብዙ አይተናል በታሪክ ጄኖሳይድ የደረሰባቸው ሰዎች ጠፍተው አልጠፉም እና የትግራይ ህዝብ ሊጠፋ አይችልም፤ መቼም ሰው ነውና እግዚአብሔር በአርያውና በአምሳሉ የፈጠረውም ፍጥረት ጨርሶ እንዲጠፋ አይፈልግም ስለዚህ ይሄ ጉዳይ ዓለም ቢመለከተው ፣ ዓለም ቢያውቀው ... አይቶታል ይጠፋዋል ማለቴ አይደለም፤ እንደውም ሰልችቶታል፤ ተው ፣ ታረቁ ተው ሰላም ሁኑ እያለ እየለፈለፈ ነው ያለው የዓለም ህዝብ ነገር ግን ሰሚ ጠፍቷል። ይሄ ጉዳይ ምን እንደሚጠቅም እየታየ ነው ያለው፤ ቁልቁል እየወረድን ነው ያለውነው እንጂ ወደሽቅብ አልወጣንም።

እና በእውነቱ እኔ ቢበቃ፣ የሆነው ሆኗል፣ የጠፋው ጠፍቷል፣ የሞተው ሞቷል፣ ያለቀው አልቋል፤ እና የንፁሃን ደም ደግሞ እግዚአብሔር አይጥለውም የራሄልን እንባ ተቀብሏል፤ የአቤል ደም እግዚአብሔር ፊት ደርሷል ከአሁን ቀድም በመፅሐፍ ቅዱስ እንደምናውቀው በባቢሎን የነበረው ገናና ንጉስ ናቡከደነፆር 3 ወጣት እስራኤላውያን አናንያ፣ ሚሳኤል ፣ አዛርያ ወደ ነበልባል እሳት ከተታቸው ግን እግዚአብሔር አዳናቸው ። ሶስቱን ወጣቶች ከእየሩሳሌም ማርኮ አምጥቶ ካመጣቸው ሰዎች ተመርጠው ሶስቱ ወጣቶች እንዲህ አርጓቸው ነበር ፤ ንጉሱ ቢጨክንባቸውም እግዚአብሔር አድኗቸዋል። እነዚህ ትግሬዎች ግን ተቃጥለዋል፤ እጅግ ያሳዝናል፤ እጅግ እጅግ ያሳዝናል ፣ መፈጠረን ያስጠላል፤ ሰው ሆኖ መፈጠር ያስጠላል።
እኔ ሀዘኔ እጅግ ከባድ ነው፤ ይሄ ደግሞ የሁሉም የኢትዮጵያዊያን በተለይ የትግራይ ህዝብ ሀዘን ነው እና መከራው ግን በሁሉም ደርሷል ፣ ቀስ እያለ እየተስፋፋ በመላ ኢትዮጵያ ደርሷል፤ እና በቃው ከእንግዲህ ወዲህ ምናለ ለተረፈው ህዝብ ይቅርታ ቢደረግለት ወይም ደግሞ ቢያሳዝነን ለምን እንዲህ አይነት ችግር ይፈጠራል የሚለው ነው።

እግዚአብሔር አምላክ ምህረቱን ያምጣ፣ እግዚአብሔር አምላክ ለህዝባችን ሁሉ የትግራይ ህዝብ ቅጠል እየበላ ነው ያለው ፣ የታመመው በመድሃኒት እጦት እያለቁ ነው ያሉት እና ይሄ ሁሉ ግፍ ቢበቃ ፣ ሰው በሰው ላይ ይሄን ያህል ጭካኔ እና ግፍ ማድረስ በሰው ላይ ቢቀር፣ ይብቃን ነው የምለው።
እግዚአብሔር አምላክ ምህረቱን ያምጣ፣ እግዚአብሔር አምላክ ሰላሙን፣ ፍቅሩን ያውርድልን ፣ እርስ በእርስ ከመበላላት ያድነን ፤ አሜን ! "
@tikvahethiopia