Healthy Gut, Healthy Kidney

Healthy Gut, Healthy Kidney

Crohn's & Colitis Ethiopia

Written By Yeabsira Taye

Medically Reviewed by Dr. Hamelmal Gebeyehu Nephrologist

ኩላሊት ምንድን ነው?

ኩላሊታችን ሁለት የተያያዘ የባቄላ ቅርፅ የሚመስልና የእጅ ጡጫ መጠን የሚያክል የሰውነት ክፍል ነው፡፡ ኩላሊታችን በሰውነታችን ውስጥ ያለን ትርፍ ውሃን፣ጨውንና በደማችን ውስጥ ያለን ቆሻሻ በማጣራት ሽንትን ያመርታል፡፡ የኩላሊት ህመም ማለት ኩላሊታችን መጎዳቱን እና በሰውነታችን ውስጥ ያለውን ተግባር በአግባቡ ማከናወን አለመቻሉን የሚገልፅ ነው፡፡

የኩላሊት ህመም በሁለት ይከፈላል፡፡ የመጀመሪያው አጣዳፊ የኩላሊት ህመም (acute kidney injury) በመባል የሚታወቀው በሰዓታት፣በቀናት ወይም በሳምንታት ውስጥ የሚከሰት ሲሆን ይህ ህመም ብዙውን ጊዜ ሊታከም የሚችል ነው፡፡ ሁለተኛው ደግሞ ስር የሰደደ የኩላሊት ህመም ሲሆን ለረጅም ጊዜ የሚቆይና በህክምና ሙሉ በሙሉ ለመዳን አስቸጋሪ የሆነ ነው፤ ሆኖም ህመሙን ለመቆጣጠር የተለያዩ የህክምና ሂደቶች አሉ፡፡ የደም ግፊት እና የስኳር ህመም ያለባቸው ሰዎች ለዚህ ስር ለሰደደ የኩላሊት ህመም የመጋለጥ እድላቸው ሊሰፋ እንደሚችል ይጠቀሳል፡፡ ስር በሰደደ የኩላሊት ህመም የመጨረሻ ደረጃ ላይ ለደረሱ ታካሚዎች እንደ የኩላሊት እጥበት ወይም ዲያለሲስ እና የኩላሊት ንቅለ ተከላ ያሉ ህክምናዎች ይሰጣሉ፡፡ 

በሆዳችን ውስጥ የሚገኙ ጠቃሚ ረቂቅ ህዋሳት እና የኩላሊት ህመም

የአንጀት ማይክሮባዮም በትሪሊዮን የሚቆጠሩ በአንጀት ክፍል ውስጥ የሚኖሩ ረቂቅ ተሕዋስያን ናቸው። እነዚህ  ረቂቅ ተሕዋስያን ጠቃሚ ባክቴሪያዎችን ብቻ ሳይሆን ፈንገሶች፣ጥገኛ ነፍሳት እና ቫይረሶችን ያካትታሉ።

አንጀታችን ገና በማህፀን ውስጥ እያለ በባክቴሪያ መሞላት ይጀምራል፤ ከተወለድን በሗላም በአንጀት ውስጥ የሚኖሩ እና የሚበቅሉ የባክቴሪያ ዓይነቶች ላይ ተጽዕኖ የሚያደርጉ ብዙ ምክንያቶች አሉ። እያደግን ስንሄድ እንደ አካባቢያችን ሁኔታ፣ በህይወታችን በሚያጋጥሙን አስጨናቂ ክስተቶች፣ በህመም፣ በአንቲባዮቲክ መድሃኒቶች አጠቃቀም እና እንደ የአመጋገብና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ያሉ የአኗኗር ዘይቤ ለውጦች የተነሳ በአንጀት ውስጥ የሚኖሩ ባክቴሪያዎች መጠን እና ጤንነት ሊለያይ ይችላል።

በጤነኛ የሰውነት ሁኔታ ውስጥ በሰውነታችን ውስጥ የሚገኙ መርዛማ ንጥረ ነገሮች በከፊል በሰገራ ይወገዳሉ፡፡ በአንፃሩ ኩላሊታችን በአንጀታችን ወደ ሰውነታችን ተመጠው የሚገቡ ማንኛውም መጠን ያላቸውን መርዛማ ነገሮች በሙሉ ያስወግዳል፡፡ ሳይንሳዊ መረጃዎች እንደሚያሳዩት የአንጀት ማይክሮባዮም ላይ ምንም አይነት ለውጥ ሲኖር አንጀት ውስጥ እንዲሁም ከአንጀት ባሻገር ተጽዕኖው ይስተዋላል፡፡ አንጀት ውስጥ ምንም አይነት መቆጣት ሲኖር ኩላሊት ከሚጠቁት የሰውነት ክፍል አንዱ ነው። ከአጣዳፊ የኩላሊት ህመም እስከ ስር የሰደደ ህመም ሊዳርግ ይችላል። ከዛም ባሻገር ለአንጀት ቁስለት እና የመሳሰሉት ህመሞች የሚሰጠው መድሀኒት ኩላሊት ላይ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል።

የኩላሊት ተግባር መዳከምም እነዚህ ከሆድ እቃ የሚመነጩ ከሰውነት መወገድ ያለባቸው መርዛማ ነገሮች ረዘም ላለ ጊዜ በሰውነት ውስጥ እንዲቆዩ ያደርጋል፡፡ ስለዚህ በአንጀት መቆጣት የመጣው የኩላሊት ድክመት መልሶ አንጀታችን ላይ ድጋሚ ጉዳት ያደርሳል። በፍጥነት ህክምና ተደርጎ እንዲሁም የአኗኗር ለውጦች ተከትለው ካልተገታ አንዱ አንዱን እየጎዳ ስር የሰደደ ህመም ሊሆን ይችላል።

የአንጀት ማይክሮብ ወይም ረቂቅ ተህዋሲያንን ጤና ለመጠበቅ የሚረዱን የአኗኗር ለውጦች ምንድን ናቸው?

የሆድ እቃ ጤናን ለመጠበቅ የሚስማማንን አንድ የምግብ አይነትን ብቻ መጠቀም ውጤታማ አያደርግም፡፡ ይህ ነው የሚባል አንድ እና ቀላል ዘዴም የለም፤ሆኖም ጥናቶች እንደሚያሳዩት ጤናማ የአመጋገብ ስርዓቶችን ( እንደ በአትክልትና ፍራፍሬ የበለፀዱ፣የአሳ ምርቶች፣የጥራጥሬ እህሎችና ፋይበሮች መመገብ እና የቀይ ስጋ፣የጨውና የስኳር መጠን መቀነስ) በስር የሰደደ የኩላሊት ህመም የሚከሰት ሞትን ከመቀነስ ጋር ተያይዘው ተጠቅሰዋል፡፡

በቀጣይ የአመጋገብ ስርዓትና፤ ጤነኛ የሆድ እቃና ጤነኛ የሰውነት አካል ተያያዥነት ዙሪያ በሰፊው የምንዳስስ ይሆናል፡፡

ማጠቅለያ

የአንጀት ማይክሮባዮም ተህዋሲያን ባህሪይና ተግባር ለውጥ የአንጀት ቁስለትን ጨምሮ ለተለያዩ የሰውነትን መቆጣትን ለሚያስከትሉ ህመሞች እንደምክንያት ይጠቀሳል፡፡ የአንጀት ማይክሮባዮም መጠን በተገቢው ልክ አለመገኘት የአንጀት ግድግዳን ንጥረ ነገሮች የማሳለፍ ባህሪይ በማጥቃት መርዛማ ነገሮች ወደ ደም እንዲቀላቀሉ እና የሰውነት ስርዓታችን እንዲዛባ እና ሰውነታችን እንዲቆጣ ያደርገዋል፡፡ ልክ እንደዚሁ የእነዚህ የአንጀት ማይክሮባዮም መዛባት የሰውነትን በሽታን የመቋቋም አቅም በመቀነስ፣የደም ግፊት መጠንን በመጨመር ፣ የምግብ መፈጨት ስርዓትን በማዛባትና ረዘም ያለ የሰውነት መቆጣትን በማስከተል ስር የሰደደን የኩላሊት ህመም መባባስ ያስከትላሉ፡፡


በቀጣይ ሳምንት የአንጀት ቁስለት ህመም እና ኩላሊት እንዴት ይገናኛሉ የሚለውን በሰፊው ይዘን የምንቀርብ ይሆናል።

የአብስራ ታዬ ክሮንስ & ኮላይተስ ኢትዮጲያ

ዶ/ር ሀመልማል ገበየሁ ኢትዮጲያ ኪድኒ ኬር


ማጣቀሻ

1.    Kathryn J. Pflughoeft and James Versalovic Annual Review of Pathology: Mechanisms of Disease 2012 7:1, 99-122.

Available from Human Microbiome in Health and Disease | Annual Review of Pathology: Mechanisms of Disease (annualreviews.org)

2.    Wehedy E, Shatat IF and Al Khodor S (2022) The Human Microbiome in Chronic Kidney Disease: A Double-Edged Sword. Front. Med. 8:790783. doi: 10.3389/fmed.2021.790783

Available from Frontiers | The Human Microbiome in Chronic Kidney Disease: A Double-Edged Sword | Medicine (frontiersin.org)

3.    Wu IW, Lin CY, Chang LC, Lee CC, Chiu CY, Hsu HJ, Sun CY, Chen YC, Kuo YL, Yang CW, Gao SS, Hsieh WP, Chung WH, Lai HC, Su SC. Gut Microbiota as Diagnostic Tools for Mirroring Disease Progression and Circulating Nephrotoxin Levels in Chronic Kidney Disease: Discovery and Validation Study. Int J Biol Sci 2020; 16(3):420-434. doi:10.7150/ijbs.37421.

Available from Gut Microbiota as Diagnostic Tools for Mirroring Disease Progression and Circulating Nephrotoxin Levels in Chronic Kidney Disease: Discovery and Validation Study (ijbs.com)

4.    Simona Mihai, Elena Codrici, Ionela Daniela Popescu, Ana-Maria Enciu, Lucian Albulescu, Laura Georgiana Necula, Cristina Mambet, Gabriela Anton, Cristiana Tanase, "Inflammation-Related Mechanisms in Chronic Kidney Disease Prediction, Progression, and Outcome", Journal of Immunology Research, vol. 2018, Article ID 2180373, 16 pages, 2018. https://doi.org/10.1155/2018/2180373

Available on: Inflammation-Related Mechanisms in Chronic Kidney Disease Prediction, Progression, and Outcome (hindawi.com)

5.    Mafra, Denise et al. “Dietary Components That May Influence the Disturbed Gut Microbiota in Chronic Kidney Disease.” Nutrients vol. 11,3 496. 27 Feb. 2019, doi:10.3390/nu11030496

Available on Dietary Components That May Influence the Disturbed Gut Microbiota in Chronic Kidney Disease - PMC (nih.gov)

6.    Mertowska, Paulina et al. “A Link between Chronic Kidney Disease and Gut Microbiota in Immunological and Nutritional Aspects.” Nutrients vol. 13,10 3637. 17 Oct. 2021, doi:10.3390/nu13103637

Available on A Link between Chronic Kidney Disease and Gut Microbiota in Immunological and Nutritional Aspects - PMC (nih.gov)

Report Page