Haraj Hibret bank46 excava

Haraj Hibret bank46 excava


የመጀመሪያ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ


ሕብረት ባንክ አማ በመገናኛ ቅርንጫፉ በኩል ለሰጠው ብድር በመያዣነት የያዘውን ከዚህ በታች በሠንጠረዡ የተመለከተውን ማሽነሪ በአዋጅ ቁጥር 97/90 ወይም 98/90 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት በግልጽ ሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

የሐራጅ ደንቦች፣

ተጫራቾች የሐራጁን መነሻ ዋጋ አንድ አራተኛ በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ። አሸናፊ የሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በአሥራ አምስት (15) ቀናት ውስጥ አጠቃልሎ ካልከፈለ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሐራጁ ይሠረዛል፡፡ በተጨማሪም ንብረቱ ድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል።
በሐራጅ ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች፣ ተበዳሪዎችና አስያዦች ብቻ ናቸው፡፡
ሽያጩ የሚካሄደው የመያዣው ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ ነው።
የተጫራቾች ምዝገባ ከሐራጁ መዝጊያ ሰዓት ሰላሳ ደቂቃ በፊት ይጠናቀቃል፡፡ በሐራጁ የመጨረሻ ሰላሳ ደቂቃዎች የተጫራች ምዝገባ አይካሄድም።
ለሐራጅ የቀረበውን ንብረት ለመጎብኘት የሚፈልጉ ከአበዳሪው ቅርንጫፍ ወይም ከሕግ አገልግሎት ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ መጎብኘት ይችላሉ
የተጨማሪ እሴት ታክስ እና ሌሎች ገዢ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ታክስና ግብሮችን የጨረታው አሸናፊ/ገዢው ይከፍላል፡፡

ማሽነሪው ከቀረጥ ነፃ ወደ አገር ውስጥ የገባ በመሆኑ ተመሳሳይ የቀረጥ ነፃ መብት ካለው ተጫራች ውጪ የሆነ ተጫራች የሐራጁ አሸናፊ ቢሆን መንግስት ከማሽነሪው የሚፈልገውን ቀረጥ መክፈል ይኖርበታል፡፡

ማሽነሪው እስከ የካቲት 2 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ የእርጅና ቅናሽ ተደርጎ የብር 903,254.03 (ዘጠኝ መቶ ሶስት ሺ ሁለት መቶ ሃምሳ አራት ብር) ቀረጥና ታክስ ይፈለግበታል፡፡

***ባንኩ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡***

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- (ሕግ አገልግሎት መምሪያ 011-4-70-03-15/47/69) ወይም (0116670121/0063 መገናኛ ቅርንጫፍ) ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

ሕብረት ባንክ አ. ማ


Posted: አዲስ ዘመን ግንቦት 20 ቀን 2012

Deadline: June 23, 2020


©walia tender

Report Page