#HAWASSA

#HAWASSA


በሀዋሳ ከተማ ችግር ፈጣሪዎችን አሳልፎ በመስጠት ሰላሙን ለመጠበቅ ህብረተሰቡ ከፀጥታ አካላት ጋር ሊተባበር እንደሚገባ የከተማዋ ጊዜያዊ የፀጥታ ኮማንድ ፖስት አሳሰበ፡፡

ኮማንድ ፖስቱ በከተማዋ ጊዜያዊ የፀጥታ ሁኔታና ቀጣይ ተግባራት ዙሪያ ዛሬ ከነዋሪዎች ጋር ተወያይቷል፡፡

ውይይቱን የመሩት የኮማንድ ፖስቱ ሰብሳቢ ኮሎኔል ተክለብርሀን ገብረመድኅን “የሲዳማ ህዝብ የጠየቀው በክልል የመደራጀት ጥያቄ ሕገ-መንግስታዊ ነው “ብለዋል፡፡

ሆኖም ጥያቄውን በነውጥ ለማስመለስ መጣር ኢ-ህገመንግስታዊ መሆኑን ተናግረዋል።

ኮሎኔሉ እንዳሉት ከጥያቄው ጋር ተያይዞ በሀዋሳ ከተማና በሲዳማ ወረዳዎች የተፈጠረውን ችግር ለመቆጣጠር በተደረገው ጥረት ውስጥ የህብረተሰቡም ድጋፍ የራሱ ሚና ነበረው፡፡

ነውጡን የማይደግፉ እንዳሉ ሁሉ ከህብረተሰቡ መሀል በተግባር ጭምር የደገፉና የተሳተፉ መኖራቸውን ገልጸዋል፡፡

በነውጡ ውስጥ ተሳትፎ የነበራቸውና በቁጥጥር ሥር ያልዋሉ ግለሰቦች እንዲሁም የከተማዋ ነዋሪ ህብረተሰብ ሠላምና ደህንነት ሥጋት ላይ የሚጥሉ ወንጀሎች አሁንም እንዳሉ የኮማንድ ፖስቱ ሰብሳቢ አስታውቀዋል፡፡

ኮማንድ ፖስቱ በየክፍለ ከተማው መቋቋሙንና እስከ ቀበሌዎች በመውረድ ሕግ የማስከበርና የህብረተሰቡን ደህንነት የማስጠበቅ ተግባራት እንደሚያከናውን ገልጸዋል።

የከተማው ነዋሪ ህዝብም በያለበት አካባቢ አጥፊዎችን አጋልጦና አሳልፎ በመስጠት ከፀጥታ አካላት ጋር ሊተባበሩ እንደሚገባ አስገንዝበዋል ፡፡

ሰላሙን አጥብቆ በመጠበቅም የኮማንድ ፖስቱን ሥራ ማቃለል እንዳለበትም አመልክተዋል፡፡

ከተማዋን ወደ ቀድሞ ሠላሟ ለመመለስ አመራሮች ፣ የኃይማኖች መሪዎችና የሀገር ሽማግዎች ኃላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲውጡም ጠይቀዋል።

አባቶች ልጆቻቸውን በመምከርና በመገሰፅ የሚጠበቅባቸውን መወጣት እንዳለባቸው እንዲሁ፡፡

በፌዴራል ፖሊስ ፈጥኖ ደራሽ ዳይሬክቶሬት የደቡብ ዲቪዥን ዋና አዛዥ ኮማንደር ሙሉዓለም ዘውዴ በበኩላቸው በወቅቱ ተፈጥሮ በነበረውን ነውጥ የከተማው ህዝብ ከፍተኛ ሥጋት ውስጥ ወድቆ እንደነበር አስታውሰዋል፡፡

የፀጥታ አካላት ባደረጉት ጥረት ነውጡን ማርገብ እንደተቻለ ጠቁመው ሆኖም በድርጊቱ የተሳተፉ አካላት ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ሥር ባለመዋላቸው አሁንም ለህብረተሰቡ ሥጋት የሆኑ ህገወጥ ተግባራት እንደሚፈፀሙ አስረድተዋል፡፡

ኮማንደሩ እንዳመለከቱት ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ለሠላም ዋጋ ሰጥቶ ሊረባረብና የፀጥታ አካላቱን ሥራ ሊያግዝ ይገባል።

በከተማዋ ያለፈውን አንድ ዓመት በተለያዩ የፀጥታ ችግር ሥጋት ውስጥ ማሳለፏን የገለጹት ደግሞ የከተማው ሠላምና ፀጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ ኃይሌ ነጌሶ ናቸው።

ከሁሉም የፀጥታ ኃይሎች ጋር በመቀናጀት ችግሮቹን ለማስወገድ ሲሰሩ መቆያታቸውን ተናግረዋል።

ሐምሌ 11/2011ዓ.ም የተፈፀመው የጥፋት ድርጊት ለሕብረተሰቡ ለሰው ህይወት መጥፋትና ንብረት መውደም ምክንያት እንደሆነ አመልክተዋል።

እንደ አቶ ኃይሌ ገለፃ አሁንም በከተማዋ ውስጥ ዝርፊያን ጨምሮ የተለያዩ ወንጀሎች እየተፈጸሙ ነው፡፡

“የኮማንድ ፖስቱ ዓላማ በአካባቢው የህግ የበላይነት ሰፍኖ ዜጎች በነፃነት እንዲንቀሳቀሱና ጥያቄ ያላቸውም በህግ አግባብ የሚካሂዱበት ምቹ ሁኔታ መፍጠር ነው “ ብለዋል።ሁ ሉም የህብረተሰብ ክፍል ከኮማንድ ፖስቱ ጋር በመተባበር የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡

ምንጭ፦ ኢዜአ

@tsegabwolde @tikvahethiopia

Report Page