H2 Computer School

H2 Computer School



ሚሚና መሰል ተበዳዮች በሰላሙ ጊዜ ሀፍቶም የሰጧቸውን ደረቅ ቸክ ይዘው ወደ ባንክ ቢያመሩም ባንክ በሀፍቶም ኃይሌ ስም የተመዘገበ የባንክ ሂሳብ ቁጥር ውስጥ ምንም አይነት ገንዘብ እንደሌለው እንዳረጋገጠላቸው ጠቁመዋል። ሌሎችም በውል እና በማስረጃ ለሀፍቶም ገንዘብ ያበደሩ ተበዳዮች ገንዘባቸውን የሚመልሰበት ሁኔታ አስከ አሁን ድረስ እንዳላገኙ ተናግረዋል።ሌላኛው ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ ተበዳይ እንደገለጹት 1ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር እንደተጭበረበሩ ተናግረዋል።ተበዳዩ አክለውም “የተፈጸመብን አደገኛ የሆነ፣ ተደርጎ የማያውቅ ታሪካዊ ጥፋት ነው።” ሲሉ የደረሰባቸውን በደል አስረድተዋል።

ተበዳዮች እንዳስረዱት የትምህርት ቤቱ ሰራተኞች የነበሩ ሰዎችም ደምወዝ እንዳልተከፈላቸው እና ትምህርት ቤቱ ባለቤት በማጭበርብር ከአነስተኛ የገንዘብ ተቋም(micirofinance) በስማቸው በማሰፈረም ገንዘብ ተበድረው ባለ እዳ አድረገዋቸው እንደተሰወሩ ተመላክቷል።

አዲስ ማለዳ ከምንጮቼ አረጋገጥኩ እንዳለው ሀፍቶም በተበዳዮች ላይ የሰሩት ማጭበርበር ተግባር ከሰራተኞች እና ከአበዳሪዎች አልፎ ከአንድ ሺህ በላይ በሚሆኑ ሰዎች ላይ የተደራጀ የማጭበርበር ስራ እንደፈጸሙ ተጠቁሟል።


ምንጮች እንደገለጹት የትምህርት ቤቱ ሰራተኛ ባልሆኑ ሰዎች ላይ የተፈጸመው የማጭበርበር ስራ የድርጅቱ ሰራተኞች እንደሆኑ በማስረዳት ከአነስተኛ ገንዘብ አበዳሪ ተቋማት በማስፈረም በስማቸው ገንዘብ ተበድሮ የብድሩ እዳ ከፋይነት ጉዳዮን ምንም ለማያውቁት እና የጥቅም ተጋሪ ላልነበሩት ግለሰቦች ማውረስ መሆኑ ተመላክቷል።ተበዳዮች ፍትህ ለማግኘትና የተጨበረበሩትን ገንዘባቸውን ለማስመለስ ኮሚቴ በማቋቋም በፍትብሔር ህግ እና በሀፍቶም ቤተሰቦች በኩል ሽማግሌ ልከው ምላሽ በመጠባበቅ ላይ ሲሆኑ፣ አንዳንዶች የደረሰባቸውን በደል ለመናገር የሀፍቶምን በህግ ቁጥጥር ስር መዋልና ገንዘባቸውን የማግኘት እድል እንደሚያጠበው በመፍራት በደላቸውን ለመናገር ፈቃደኛ ሳይሆኑ በመቅረታቸው ሀሳባቸውን አልገለጹም።ኤችቱ የቋንቋ እና ኮምፒተር ትምህርት ቤት በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች የቋንቋ እና የኮምፒተር ስልጠናዎችን እና ትምህርቶችን ሲሰጥ የነበረ ተቋም ሲሆን፣ በአሁኑ ጊዜ በአዲስ አበባ በመገናኛ ቤቴልሄም ፕላዛ ሶስተኛ ፎቅ ላይ የሚገኘው ዋና ቢሮው መታሸጉን ሰራተኞች አረጋግጠዋል። የአራት ወር የቤት ኪራይ እንዳልከፈለም ተረጋግጧል። ከአዲስ አበባ ውጭ የሚገኙ ቅርንጫፍ ቢሮዎች ሙሉ በሙሉ መታሸጋቸውን አሁን ተበዳይና የተቋሙ ሰራተኛ የነበሩት ሚሚ አረጋግጠዋል።


Via Addis Maleda

@YeneTube @FikerAssefa1

Report Page