Gut Microbe & Healthy Gut

Gut Microbe & Healthy Gut

Crohn's & Colitis Ethiopia

'ጤናማ አንጀት' ምንድን ነው?

ሁላችንም የእለት ተእለት ህይወታችንን የምንመራባቸው የተለያዩ አካባቢዎች፣የተለያዩ ልማዶች እና ባህሎች አሉን። በዚህ ምክንያት እያንዳንዳችን ከወላጆቻችን፣ ወንድሞቻችን ወይም እህቶቻችን ወይም የባህር ማዶ ጓደኞቻችን ለየት ያለ የአንጀት ማይክሮባዮም መጠን እና የጤና ሁኔታ  አለን ፡፡ የእርስዎ ማይክሮባዮም ለእርስዎ የተለየ የጠቃሚ ባክቴሪያ አሻራ ነው።በዚህ ምክንያት እና ስለ ማይክሮባዮሞች ገና ሙሉ በሙሉ በሳይንሱ ያልተብራሩ ነገሮች ስላሉ በሁሉም ሰው ዘንድ የጤናማ ማይክሮባዮሞች መጠን እና ጤና ይህ ነው ተብሎ ድምዳሜ ላይ መድረስ አስቸጋሪ ነው ፡፡

የአንጀት ማይክሮባዮም ምንድን ነው?

የአንጀት ማይክሮባዮም በትሪሊዮን የሚቆጠሩ በአንጀት ክፍል ውስጥ የሚኖሩ ረቂቅ ተሕዋስያን ናቸው። እነዚህ  ረቂቅ ተሕዋስያን ጠቃሚ ባክቴሪያዎችን ብቻ ሳይሆን ፈንገሶች፣ጥገኛ ነፍሳት እና ቫይረሶችን ያካትታሉ።

አንጀታችን ገና በማህፀን ውስጥ እያለ በባክቴሪያ መሞላት ይጀምራል፤ ከተወለድን በሗላም በአንጀት ውስጥ የሚኖሩ እና የሚበቅሉ የባክቴሪያ ዓይነቶች ላይ ተጽዕኖ የሚያደርጉ ብዙ ምክንያቶች አሉ። እያደግን ስንሄድ እንደ አካባቢያችን ሁኔታ፣ በህይወታችን በሚያጋጥሙን አስጨናቂ ክስተቶች፣ በህመም፣ በአንቲባዮቲክ መድሃኒቶች አጠቃቀም እና እንደ የአመጋገብና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ያሉ የአኗኗር ዘይቤ ለውጦች የተነሳ በአንጀት ውስጥ የሚኖሩ ባክቴሪያዎች መጠን እና ጤንነት ሊለያይ ይችላል።

የአንጀት ማይክሮባዮም ጠቀሜታ ምንድን ነው?

በአንጀት ውስጥ የሚገኙ ጠቃሚ ረቂቅ ተሕዋሲያን ለጤናችን ወሳኝ ለሆኑት በርካታ ተግባራት ተጠያቂ ናቸው፡፡ ከእነዚህ ተግባራት መካከል በዋነኝነት የሚጠቀሱት፡-

v የአንጀት የምግብ መፍጨት ስርዓትን ማሳለጥ እና ከምግብ የሚገኙ አስፈላጊ ንጥረ ነገሮች በተገቢው መጠን ወደ ሰውነት እንዲመጠጡ ማገዝ፤

  • የአንጀትን ግድግዳ መዋቅራዊ ቅርፅ መጠበቅ፤
  • የሰውነት በሽታን የመከላከል አቅም ማገዝ፤
  • የመድሃኒትን የመፈጨትና የመዋሃድ ሂደት ማሳለጥ፤
  • አንጀትን ከበሽታ አምጪ ተህዋሲያን መከላከል፤
  • ከስሜት ጋር የተያያዙ የአእምሮ ተግባራትን  መቆጣጠር ፤
  • የተወሰኑ በሰውነታችን ውስጥ አስፈላጊ የሆኑ እንደ ቪታሚን ዲ እና ኬ ያሉ ቪታሚኖች እንዲመነጩ  ይረዳሉ፤
  • ለአንጀት ባዕድ የሆኑ እንደ የምግብ ማጣፈጫ ቅመሞች፣የኢዱስትሪና የከባቢ በካዮችን ከሆድ እቃ ውስጥ የማስወገድ ሂደትን ማገዝ፡፡

ጤናማ የሆነ የማይክሮባዮም መጠንን ለማጠናከር ምን ማድረግ እችላለሁ?

  •  አትክልቶችን መመገብ
  • በኢንዱስትሪ የተቀነባበሩ ምግቦችን የምንጠቀምበትን መጠን መቀነስ
  • የፕሮባዮቲክስ ምንጮችን መጠቀም ( ፕሮባዮቲክ ምንጮች ምንድን ናቸው? በቀጣይ ሳምንታት)
  • የአንቲባዮቲክ መድሃኒቶችን አወሳሰድ ማስተካከል ( ሀኪም ያዘዘውን መድሀኒት ብቻ መውሰድ)
  • በቂ የሆነ እረፍት እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ፡፡

 

 

ስለዚህ ጤናማ አንጀት ማለት የእነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ማይክሮባዮሞች ፤ እንደ የምግብ ማሳለፊያ ቱቦ፣ጨጓራ እና አንጀት ውስጥ በአስፈላጊው መጠን መገኘት እና ከመመገብ ጀምሮ አላስፈላጊ ነገሮችን እስማስወገድ ያለው የምግብ መፈጨት ስርዓትን ያለ እንከን ማከናወንን ያካትታል፡፡

 

በቀጣይ ሳምንት……

በኩላሊት ህመም እና በአንጀት ህመም መካከል ያለ ግንኙነት ምንድን ነው?

ይከታተሉ!

                                  እናመሰግናለን!


Report Page