Guji Zone

Guji Zone


#GujiZone


" እስከ ሃምሌ 15 ቀን 2014 ዓ/ም ባለው ጊዜ የ12 ሰዎች ህይወት አልፏል ፤ ቁጥሩ ግን ሊጨምር ይችላል " - የሰባ ቦሩ ቡሳ ጎኖፋ ቢሮ


" የሞቱት ዜጎች ምናልባት በፀጥታ ችግር ምክንያት ሊሆን ይችላል " - የጉጂ ዞን ኮሚኒኬሽን



በጉጂ ዞን ሰባ ቦሩ ወረዳ በድርቅ ምክንያት የወገኖቻችን ህይወት እያለፈ መሆኑ ተገለፀ።


በኦሮሚያ ክልል፣ በጉጂ ዞን በሰባ ቦሩ ወረዳ ረሃብ ተከስቶ 12 ሰዎች መሞታቸውን የወረዳው ቡሳ ጎኖፋ ቢሮ ማስታወቁን ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል።


ቢሮው ፤ እስከ ሃምሌ 15 ቀን 2014 ዓ/ም ባለው ጊዜ ብቻ የ12 ሰዎች ህይወት ማለፉን ገልጾ ቁጥሩ ግን ሊጨምር እንደሚችል አሳውቋል።


በወረዳው 35,442 ዜጎች አቸኳይ የምግብ እርዳት ያስፈልጋቸዋል የተባለ ሲሆን እነዚህ ዜጎች በንሳ፣ በደጋላልቻ፣ ሰባሎሌማሞ፣ ኡቱሉ፣ ኦዴ ፣ ሀራጌሳ ቀበሌዎች ከፍተኛ የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ተገልጿል።


የወረዳው ቡሳ ጎኖፋ ቢሮ ኃላፊ መኮና ሀጤሳ ፤ ለወረዳው አልፎ አልፎ የምግብ እርዳታ ቢመጣም ምግብ ከሚያስፈልጋቸው ዜጎች ጋር የሚመጣጠን አይደለም ብለዋል።


በወረዳው የሟቾች ቁጥር በየቀኑ እየጨመረ ሲሆን ባለፉት 2 ወራት የምግብ እና መሰል እርዳታቸዎች መቋረጣቸው ማህበረሰሙ ለከፋ የምግብ እጥረት መጋለጡን ገልፀዋል።


በወረዳው ያለውን አስቸኳይ የምግብ እጥረት ቢኖርም ጉዳዩን ትኩረት ሰጥተው የሚዘግቡ የመገናኛ ብዙሃን ባለመኖራቸው ረሃቡ ስር የሰደደ ነው ብለዋል።


የጉጂ ዞን የኮሚኒኬሽን ቢሮ በበኩሉ ፤ በዞኑ ቆላማ አካባቢዎች 5 ወረዳዎች ድርቅ ተከስቷል ፣ ወረዳዎቹ ከሶማሌ ክልል ጋር እና ከቦረና ዞን ጋር የሚዋሰኑ ቦታዎች ናቸው በዝናብ እጥረት ሳቢያ ለከፍተኛ የምግብ እጥረት የተጋለጡ ዜጎች ብዙ ናቸው ብሏል።


የቢሮው ኃላፊ አቶ ዮሐንስ ኦልኮ ፤ በረሃብ ምክንያት ስለሞቱ ሰዎች መረጃ የለኝም ብለዋል። ነገር ግን በአካባቢው የፀጥታ ችግር አለ ሲሉ ገልጸዋል።


" በሰባ ቦሩ ወረዳ የተፈጠረ ችግር ሊኖር ይችላል " ያሉት ኃላፊው " የሞቱት ዜጎች ምናልባት በፀጥታ ችግር ምክንያት ሊሆን ይችላል " ብለዋል።


ጉሜ ኤልደሎ ፤ ሊበን ፣ጎሮ ደላ፣ ዋደራ፣ ገርጃ፣ ሰባ ቦሩ ወረዳዎች እና አዶላሬዴ 7 ቆላማ ቀበሌዎች ላይ ድርቅ መከሰቱን የሚገልፁት አቶ ዮሐንስ በረሃብ ምክንያት ሞቱ የተባለው ከፊል ቀበሌዎች ላይ በህ/ተ/ም/ቤት አሸባሪ ተብሎ በተፈረጀው " ሸኔ " ቁጥጥር ስር የሚገኙ ናቸው ብለዋል።


በወረዳው መንግስት አስቸኳይ የምግብ እርዳት እንዳማይችል፣ ለገበያ የወጡ ዜጎችን ኦነግ ሸኔ 200 ብር ግብር እንደሚያስከፍል መረጃ ደርሶኛል ብለዋል።


ባለው የፀጥታ ችግር የምግብ ድጋፍ ለማቅረብ አለመቻሉንም አስረድተዋል።


መረጃው ከሪፖርተር ጋዜጣ የተገኘ ነው።

Report Page