Green Tea & Our Gut

Green Tea & Our Gut

Crohn's & Colitis Ethiopia

አረንጓዴ ሻይ ምንድን ነው?

አረንጓዴ ሻይ Camellia sinensis ከተሰኘ የእፅዋት ቅጠል የሚሰራ የሻይ አይነት ነው። ስድስት ዓይነት ፈርጅ ያላቸው የሻይ አይነቶች አሉ። የሻይ ቅጠሎቹ ለመዘጋጀት የሚያልፉበት ሂደት የሻዩን አይነት ይወስኑታል።

በዓለም አቀፍ ደረጃ ቻይና እና ጃፓን ከ1,500 በላይ ያሉ የአረንጓዴ ሻይ አይነቶችን ያመርታሉ። እንደ ሻይ አምራቾቹ፣ የእያንዳንዱ አረንጓዴ ሻይ ልዩ ልዩ ገፅታዎች ሠፊ እና በርካታ ምርጫ እንዲኖረን አድርጓል።

በጃፓን በብዙ ትውልዶች ውስጥ አረንጓዴን ሻይ ከጤና ጋር በተያያዘ መንገድ ይጠቀሙባቸዋል። አንደኛው የአረንጓዴ ሻይ ጥቅም የሰውነታችንን የምግብ የመፍጨት ሂደት ማሻሻል ነው። አረንጓዴ ሻይን መጠቀም በተፈጥሮ መንገድ የተለመዱ የሆድ ህመሞችን ለማስታገስ እና ለማሻል አይነተኛ መንገድም ነው፡፡

ይህን ያውቁ ይሆን?

አረንጓዴ ሻይን መጠቀም የሰውነታችንን ምግብ የመፍጨት ስርዓት ያፋጥናል

አረንጓዴ ሻይ በውስጡ Polyphenols ይዟል፣ ይህም በሆድ እቃ ውስጥ የሚገኙ ጠቃሚ ባክቴሪያዎችን በማነቃቃት የምግብ የመፍጨት ስርዓትን ለማሻሻል ወይም ምግብን ስኬታማ በሆነ መንገድ ለመፍጨት ይጠቅማል። በቀን ከሁለት እስከ ሶስት ኩባያ አረንጓዴ ሻይ ስንጠጣ ከ100-300mg Polyphenols መጠን ወደ ሰውነታችን መስረፅ/ መምጠጥ ያስችላል።

የሰውነታችንን ምግብ የመፍጨት ስርዓት ለማሻሻል አርንጓዴ ሻይን በምንጠቀምበት ጊዜ፤ በተጨማሪ አረንጓዴ ሻይ በውስጡ Caffeine /በቡና ውስጥ የሚገኘው ንጥረ ነገር አይነት/ እንደሚይዝ ማወቅ ይኖርብናል። በአዎንታዊ ጎኑ Polyphenols የምግብ መፍጨት ስርዓታችንን ላይ በጎ ተፅዕኖ እንደሚያመጡ ሁሉ፣ Caffeine ደግሞ በአሉታዊ መልኩ ተፅዕኖ ሊያመጣ ይችላል። ሰውነታቸው ለCaffeine የላቀ ምላሽ የሚሰጥ ሰዎች ለሆድ ህመም፣ ለተቅማት እንዲሁም ለማቅለሽለሽ ስሜት ሊዳረጉ ይችላሉ። ለCaffeine የላቀ ምላሽ/High Sensitivity/ ያላቸው ሰዎች የሚጠቀሙትን የአረንጓዴ ሻይ መጠን መቀነስ ይኖርባቸዋል።

አረንጓዴ ሻይ የአንጀት ቀስለትንና መቆጣትን ለመከላከል እና ለማከም ይጠቅማል

አንዳንድ ጥናቶች እንደሚያሳዩት በአረንጓዴ ሻይ ውስጥ የሚገኙ ንጥረ ነገሮች የአንጀት መቆጣትንና መቁሰልን ለመከላከል ትልቅ አስተዋፆ አላቸው፡፡ከዚያ በተጨማሪ አረንጓዴ ሻይን መጠቀም የአንጀት ቁስለት ያለባቸው ሰዎች ላይ የአንጀት ካንሰር የመከሰት ዕድሉን እንደሚቀንስም ያመለክታሉ። በአረንጓዴ ሻይ ውስጥ የሚገኘው Polyphenol የካንሰር ህዋሶችን/Cells/ በፍጥነት የመራባት መጠን ይቀንሳል ። በመሆኑም ማንኛውንም ከአንጀት ቁስለት ጋር ተያያዥ የሆኑ ስሜቶችን ለመቀነስ አረንጓዴ ሻይን መጠቀም ምርጡ አማራጭ ነው።

አረንጓዴ ሻይ ሰውነታችን ለ Insulin የሚሰጠውን ምላሽ ያሻሽላል

አረንጓዴ ሻይ ሰውነታችን ለInsulin የሚሰጠውን ምላሽ ያሻሽላል። አብዛኛው ሰው Insulin'ን ከስኳር/Diabetes/ በሽታ ጋር ያይዘዋል ነገር ግን ሰውነታችን ለInsulin የሚሠጠው ምላሽ ማንኛውም ሰው ላይ ተፅዕኖ ሊያመጣ ይችላል። Insulin ከጣፊያችን የሚለቀቅ ንጥረ ነገር ሲሆን፣ ሰውነታችን Glucose'ን ከተለያዩ ምግቦች የሚጠቀምበትን ሂደት ይቆጣጠራል። ሰውነታችን ከምንመገባቸው ምግቦች ውስጥ Carbohydrate'ን በመፍጨት ወደ Glucose መቀየር ይኖርበታል። በደማችን ውስጥ ያለውን የGlucose መጠን ምን ያህል መሆን እንዳለበት ለመቆጣጠር Insulin ይጠቅማል።

አረንጓዴ ሻይን መጠቀም ሰውነታችን ለ Insulin የሚሰጠው ምላሽ በላቀ ደረጃ ያሻሽላል፣ በዚህም ጊዜ ከጣፊያችን በሚለቀቀው መጠነኛ Insulin ፣ በደማችን ውስጥ የሚገኘውን የGlucose/ስኳር/ መጠን እንዲቀንስ ያደርጋል። ይህም ጥሩ የሆነ የGlucose ቁጥጥር እንዲኖረን ይሆናል።

አርንጓዴን ሻይ በመጠቀም የምግብ መፍጨት ስርዓትዎን ያሻሽሉ

አሀን አርንጓዴ ሻይ በሰውነታችን ስለሚሠጠው የተለያዩ አስደናቂ ጥቅሞች አይተናል። ነገር ግን ከምግብ መፈጨት ጋር በተያያዘ የሚያሳየውን ጥቅም ለማየት ምን ያህል መጠን መጠቀም ያስፈልገናል?

በሰውነታችን ምግብ የመፍጨት ስርዓት ውስጥ፣ አርንጓዴ ሻይ አዎንታዊ ጥቅም ያለው ቢሆንም፣ ከመጠን ያለፈ በምንጠቀምበት ጊዜ ደግሞ አሉታዊ ተፅዕኖ ሊያመጣብን ይችላል። በቀን ከሁለት እስከ ሶስት ኩባያ አርንጓዴ ሻይ ስንጠጣ፣ ከ100-300mg Polyphenols መጠን ወደ ሰውነታችን መስረፅ/ መምጠጥ ያስችላል።

የሰውነታችንን ምግብ የመፍጨት ስርዓት ለማሻሻል አርንጓዴ ሻይን በምንጠቀምበት ጊዜ፤ በተጨማሪ Green Tea በውስጡ Caffeine እንደሚይዝ ማውቅ ይኖርብናል። በአዎንታዊ ጎኑ Polyphenols የምግብ መፍጨት ስርዓታችንን ላይ በጎ ተፅዕኖ እንደሚያመጣ ሁሉ፣ Caffeine ደግሞ በአሉታዊ መልኩ ትፅዕኖ ሊያመጣ ይችላል። ለCaffeine የላቀ ምላሽ የሚሰጡ ሰዎች ለሆድ ህመም፣ ለተቅማት እንዲሁም ለማቅለሽለሽ ስሜት ሊዳረጉ ይችላሉ። ለCaffeine የላቀ ምላሽ/High Sensitivity/ ያላቸው ሰዎች የሚጠቀሙትን የአረንጓዴ ሻይ መጠን መቀነስ ይችላሉ።

በአንድ ኩባያ አረንጓዴ ሻይ ውስጥ ምን ያህል Caffeine ይኖራል?

በአማካኝ በሚቀርብ 230ml አርንጓዴ ሻይ ውስጥ 35mg Caffeine ይኖራል። ነገር ግን ይህ መጠን ሊቀያየር ይችላል። በአጠቃላይ ከ30-50mg Caffeine በ230ml አርንጓዴ ሻይ ውስጥ ይገኛል። በአረንጓዴ ሻይ ውስጥ በተፈጥሮ የሚገኘው የCaffeine መጠን ከእፅዋት እፅዋት፣ እፅዋቱ የሚያድግበት ሁኔታ፣ የሚዘጋጅበት እና የሚጠመቅበት ሂደት ላይ ይወሰናል። ለምሳሌ፦ ቆየት ካሉ ቅጠሎች የሚሰራ ሻይ በውስጡ ከለጋ ቅጠሎች ከሚገኘው Caffeine ያነሰ ነው። በተጨማሪም የCaffeine መጠኑ የአረንጓዴ ሻይ አይነት እና አዘጋጃጀት ይወስነዋል።

የታሸጉ ሻዮች በCaffeine በይበልጥ የበለጠጉ ናቸው፣ ምክኒያቱም የሻይ ቅጠሎቹ ተፈጭተው እና ታሽገው ስለሚሆን፣ ብዙ Caffeine ከሻይ ቅጠሉ ወደ መጠጡ በውጣት ይችላል፤ በተቃራኒው ከብትን ቅጠሎች የሚገኘው ሻይ ደግሞ በውስጡ ያነሰ የCaffeine መጠን ይኖረዋል። እንዲሁም ደግሞ Matcha የተሰኘው እጅግ በደቃቁ የተዘጋጀ አረንጓዴ ሻይ ሲሆን በውስጡ ከታሸጉም ሆነ ከብትን ቅጠሎች በበለጠ መልኩ የCaffeine መጠን ይዘዋል።

በመጨረሻም ሻዩን ረዘም ላለ ጊዜ ካፈላነው፣ የሙቀት መጠኑ ይጨምራል፣ እንዲሁም ወደ መጠጡ ብዙ Caffeine የለቀቃል።

ስለ አረንጓዴ ሻይ ደህንነት ምን ያህል እናውቃለን?

አረንጓዴ ሻይን ለመጠጥ መጠቀም ጠቃሚ እና የሚስማማ ነውን?

በእርግዝና እንዲሁም ጡት በምናጠባበት ጊዜ፣ አረንጓዴ ሻይን መጠቀም የሚስማማ ነው። ነገር ግን የምንጠቀመው የCaffeine መጠን ከ200mg በላይ መሆን የለበትም። ከዚህ መጠን በላይ መጠቀም ጊዜ አሉታዊ ጉዳቶች እንዲከሰቱ ያደርጋል። የFolic Acid እጥረት እንዲከሰት በማድረግ ፅንሱ ላይ እክል ያመጣል። ጡት የሚጠባንም ህፃን በወተት በማለፍ ይጎዳል።

ብዙም የተለመዱ ባይሆንም፣ በተለይ ከአርንጓዴ ሻይ የሚሰሩ ኪኒኖችን/Tablet/ በሚጠቀሙ ሰዎች ላይ የጉበት ህመሞች ተዘግበዋል። የጉበት ህመም ያለባቸው ሰወች፣ እንዚህን ኪኒኖሽ ከመጠቀማቸው በፊት የህክምና ባለሞያን ማማከር ይኖርባቸዋል፤ እየወሰዱም ያሉ የጉበት ህመም ምልክቶችን ካስተዋሉ ለምሳሌ ፦ የሆድ ህመም፣ የጠቆረ ሽንት፣ እንዲሆም የአይን እና ሰውንት ቀለም ወደ ቢጫነት መቀየር ሲሆን፤ እንኚህን ምልክቶች ካስተዋሉ፣ የሚወስዱትን በማቆም የህክምና ባለሞያን ማማከር ይኖርቦታል።

አረንጓዴ ሻይ በተለያዩ የሱቆች መደርደሪያ ላይ በቀላሉ ማግኘት በሚቻሉ የክብደት መቀነሻ እና የተለያዩ የምግብ ደጓሚ ምርቶች ውስጥ እንደ ይዘት ሆኖ ይገኛል። እጅግ ባልተለመደ ሁኔታ ለጉበት ጉበት ህመም መንስኤ ሊሆን ይችላሉ።

ከአረንጓዴ ሻይ የሚገኘውን ጥቅም ለማግኘት እንደ አሁኑ ሰዓት ያለ ሁነኛ ጊዜ የለም። አረንጓዴ ሻይን ወደ ዕለታዊ ምግባቹ ለማካተት ስትጀምሩ ይሄንን መመሪያ በውስጣቹ ያዙ በመቀጠልም የሰውነታቹን ምግብ የመፍጨት ስርዓት እና ደንብን እንዲሁም በአጠቃላይ ያልዎትን ጤናዎን ያልቁ።

በቀጣይ ሳምንት ስለ እርድና ቁንዶ በርበሬ የጤና ጥቅሞች ሰፊ ማብራሪያ ይዘን እንቀርባለን፡፡ ይከታተሉን! 

Crohn's & Colitis Ethiopia


ማጣቀሻ / References:

Chronic Inflammatory Diseases and Green Tea Polyphenols (nih.gov)

Green Tea and Its Relation to Human Gut Microbiome - PMC (nih.gov)

Moderate Caffeine Consumption During Pregnancy | ACOG

Association Between Maternal Caffeine Consumption and Metabolism and Neonatal Anthropometry: A Secondary Analysis of the NICHD Fetal Growth Studies–Singletons | Neonatology | JAMA Network Open | JAMA Network

How Much Caffeine Is in Green Tea? (healthline.com)

Report Page