GoE

GoE


የኢትዮጵያ መንግስት አምነስቲ ኢንተርናሽናል እና ሂዩማን ራይትስ ዎች በጣምራ ባወጡት ሪፖርት ዙሪያ ምላሽ ሰጥቷል።

መንግስት በወልቃይት ላይ ትኩረቱን ያደረገውን ሪፖርት ይዘት በጥንቃቄ እየመረመረ እንደሚገኝ ገልጿል።

ሪፖርቱ በሰብአዊ መብት ላይ የሚነሱ ከባድ ጥሰቶች ከሚባሉት በተጨማሪ በሀገሪቱ ውስጥ የተከሰቱትንና በጥንቃቄ መታየት የሚገባቸውን የፖለቲካ ለውጦች፣ ሰላምና ደህንነት፣ የውስጥ ወሰን ጉዳዮችን ያካተተ መሆኑንም መገንዘብ ያስፈልጋል ብሏል።

የዘር ማጽዳት፣ የጦር ወንጀል እና በሰው ልጆች ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን ክስንም ያቀረበ ሪፖርት መሆኑን ገልጿል።

የሰብአዊ መብት ጥሰት የፈፀሙትን ሁሉ ተጠያቂ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኑን የገለፀው መንግስት ለዚህም ነው የኢሰመኮ እና የተመድ የሰብአዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽነር ፅ/ ቤት የጋራ ምርመራ ዉጤቶችን ተከትሎ መንግስት የሚኒስትሮች ግብረ ሃይል ማቋቋሙን አስታውሷል።

ግብረሃይሉ ዛሬ ሁለተኛ ስብሰባ አካሂዶ የምርመራ ሂደቱን ለማፋጠን የተለያዩ መመሪያዎችን አውጥቷል፤ ግብረ ሃይሉ ለአሁኑ ሪፖርትም ተገቢውን ትኩረት በመስጠት በቅርበት ይመረምራል ሲል አስረድቷል።

መንግስት ሁለቱ ተቋማት ጉዳዪን ለመመርመር የተጠቀሟቸውን በርካታ ፖለቲካዊ ጉዳዮች ትክክለኛነት ላይ ጥያቄ ማቅረቡን ገልጿል።

👉 የውስጥ ወሰን ጉዳዮች ሊታዩ የሚገባቸዉ ሕገ መንግሥታዊ ሥልጣን ባላቸው አካላት በመሆኑ እንዲህ ባሉ ጉዳዮች ላይ የአንቂ ድርጅቶቹ ፍርድ መስጠት ብልህነት የጎደለዉ ነዉ ፤እንዲህ አይነቱ ሪፖርታቸው ለፖለቲካ ፍጆታ እንደሚውልም የታወቀ ነው። ይህ አመለካከት ምርመራው በተገቢው ጥንቃቄ አለመፈፀሙን ከማሳየቱም በላይ በፍፁም ተቀባይነት የሌለው ነው ብሏል።

👉 የሪፖርቱ ብሔር ተኮር ይዘትም መንግሥት ያሳስበኛል ብሏል። አንዱን ወገን ለማስደሰት በሚሞክርበት ጊዜ ውንጀላውን ተመጣጣኝ ባልሆነ መንገድ የሚከፋፍል ይመስላል። ይህ ምልከታ ጥላቻን በማቀጣጠል ጠንካራ ሃገርን ለመገንባት በፅኑ የሚያስፈልገውን እርቅ የበለጠ ያርቀዋል ብሏል።

👉 የሪፖርቱ ስሜት ቀስቃሽ ተደርጎ መቅረብና የሚዲያ ዘገባ አቀራረብን መከተል የግኝቶቹንም ይዘትና ተአማኒነት ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባም ነው ብሏል።

👉 አንድን ቡድን ብቻ መውቀስ ለሰብአዊ መብት መከበርና ለሰላም መስፈን አይበጅም ብሏል።

በሪፖርቱ ውስጥ ያሉ ሌሎች ድክመቶችም በግልፅ የሚታዩ ናቸው ሲል ገልጿል።

ሪፖርቱ የተመሰረተዉ በአብዛኛው ለአንዱ ቡድን ቀረቤታ ባለቸዉ እማኞች ወይም ምስክሮች ላይ መሆኑም ሚዛናዊነቱን አስቶታል ብሏል።

የሪፖርቱ ጉልህ ድክመቶች እንደተጠበቁ ሆነው በሀገር መከላከያ ሰራዊትና በአማራ ልዩ ሃይል ላይ ፍትሃዊ ያልሆነ ዉንጀላ በሪፖርቱ ቢሰነዘርም የመንግስት የተዋቀረው ግብረሃይል በተገቢው መንገድ ምርመራ ያካሂድበታል ብሏል መንግስት።

መግንስት ሪፖርሩ ለሰብአዊነት ሲባል ግጭትን የማቆም ዉሳኔን በመተግበር ያልተገደበ የሰብአዊ እርዳታ ወደ ትግራይ ክልል እንዲገባ ባለው አቅም ሁሉ እየሰራ ባለበት ወቅት የወጣ ነው ያለ ሲሆን በመንግስት በኩል የተወሰደዉ ይህ እርምጃ ግጭቱን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ለሚደረገው ጥረት እውነተኛ መሰረት እንደሚጥልም ፅኑ እምነት አለዉ ብሏል።

ሪፖርቱ በሚያሳዝን ሁኔታ ለየትኛውም የሰላም ጥረት የማይጠቅሙ ምክረ-ሃሰቦችን ያስቀመጠ ቢሆንም መንግስት ሁሉንም የሰብአዊ መብት ጥሰት ክሶችን በጥልቀት በመመርመር የተገኘውን ውጤት ለህዝብ ይፋ ለማድረግ ያለውን ቁርጠኝነት በድጋሚ ያረጋግጣል።


የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

Report Page