Gibi Gubae

Gibi Gubae

ግቢ ጉባኤ


#ይመልሱ_ይሸሐሙ


ውድ የልዑል እግዚአብሔር ቤተሰቦች ባለፈው ሳምንት ለጠየቅናቸው ጥያቄዎች ትክክለኛውን መልስ በሰዓቱ የላኩልን ሶስት ተወዳዳሪዎቻችን


1. አብነት

2. ዮሴፍ

3. ማስረሻ


ለአሸናፊዎች እንዲሁ ለተሳተፋችሁ ሁሉ ቃለ ህይወትን ያሰማልን


የጥያቄዎቹ መልስ


1. ምሥጢረ ቁርባን

A. ኀብስቱ ወደ ሥጋ መለኮት ወይኑ ወደ ደመ መለኮት የሚለወጥበት ምሥጢር ✅

B. ከአምስቱ ምሥጢራተ ቤተ ክርስትያን የሚመደብ ነው

C. በቤተክርስቲያን ውስጥ ብቻ የሚሰጥ ነው

D. ሁሉም መልስ ይሆናሉ


💠 ምሥጢረ ቁርባን የተዘጋጀው ኅብስት በጻህል ወይኑ በጽዋ ተደርጎ በጸሎተ ቅዳሴ ሲባረክ ኀብስቱ ተለውጦ ሥጋ መለኮት ወይኑ ተለውጦ ደመ መለኮት ይሆናል። እኛም የዘለዓለም ህይወት ለማግኘት ይህንን የክርስቶስ ስጋና ደም የምንቀበልበት ታላቅ ምሥጢር ነው።


👉አስተውሉ ምሥጢረ ቁርባን እጅግ ለታመሙ ሰዎች ባሉበት ቦታ ይሰጣቸዋል በቤተ ክርስቲያን ብቻ ብለን መወሰን አንችልም እንዲሁም ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን ሰባት እንጂ አምስት አይደሉም።


2. ከ 6ቱ ቃላተ ወንጌል ያልሆነው የቱ ነው

A. በወንድሙ የሚቆጣ ይፈረድበታል

B. በምክንያት ሚስተን የሚፈታ የተፈታችውንም ያገባ አመነዘረ✅

C. ጠላታችሁን ውደዱ

D. ክፉውን በክፉ አትቀዋወሙ

E. መልስ የለም


💠6ቱ ቃላተ ወንጌል የምንላቸው

1 በወንድሙ ላይ በከንቱ የተቆጣ ሁሉ በፍርድ ይፈረድበታል

2 ወዴ ሴት አይቶ የተመኛት በልቡ አመነዘረባት

❗️3 ያለ ዝሙት ምክንያት ሚስቱን የሚፈታ የተፈታችውንም የሚያገባ አመነዘረ

4 ፈፅማችሁ አትማሉ

5 ክፍውን በክፍ አትቃወሙ

6 ጠላታችሁን ውደዱ



3. ዕጣን በቤተክርስቲያን ያለው ምሳሌነት፡

A. የቅዱሳን ጸሎት መዓዛ ነው

B. የእመቤታችን ምሳሌ ነው

C. የተስፋ መንግሥተ ሰማያት ምሳሌ ነው

D. ሁሉም✅


💠ዕጣን ለቤተመቅድስ አገልግሎት ይውላል።ሃያ አራቱ ካህነተ ሰማይ ዕጣንን የተመላ ሰማያዊ ማዕጠንት በእግዚአብሔር ዙፋን ፊት እየሰገዱ ለዓለም ድኅነት የሚለምኑበት ነው። በቤተክርስቲያን ካህናት መንፈቀ ሌሊት በነግህ ጊዜ በቅዳሴ

ጊዜ በየማዕዘኑ ዕጣን ያጥናሉ ቅዳሴውን ጸሎቱንና

ልመናውን ወደ እግዚአብሔር ያሳርጉበታል።


👉በዚህም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ትመሰልበታለች እንዲሁም ተስፋ የምናደርጋት መንግስተ ሰማያት ትመሰላለች


4. ኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ 5 ስለምን ይነግረናል

A. ስለ ኖኅ መርከብ አሰራር

B. ስለ አቤል በቃየል መሞት

C. ከአዳም ጀምሮ ስለነበሩ አበው እና ዕድሜያቸው✅

D. ስለ አዳም እና ሔዋን ከገነት መባረር


💠ይህ ምዕራፍ 32 ቁጡሮች የያዘ ሲሆን ከአዳም ጀምሮ እስከ ኖህ የለውን ትውልድ ከእድሚያቸው ጋር የሚነግረን ነው


5. ከመጻጉዕ በፊት ያሉት ሦስት ሰንበታት ስያሜያቸው ምንድነው

A. ኖላዊ ፣ ቅድስትና ምኩራብ

B. ቅድስት ፣ ኖላዊና ኒቆዲሞስ

C. ዘወረደ ፣ ቅድስትና ምኩራብ✅

D. ዘወረደ ፣ ኖላዊና ገብርኄር


💠የአብይ ጾም የስምንቱ ሰንበታት ስያሜ ዘወረደ፣ ቅድስት፣ ምኩራብ፣ መጻጉዕ፣ ደብረ ዘይት፣ ገብርኄ፣ ኒቆዲሞስ እና ሆሳዕና ናቸው።


ለዚህ ሳምንት ጥያቄዎች ማታ 2 ሰዓት እንገናኝ


👉ማንኛውንም አይነት ጉዳይ ላይ ያላችሁን ጥያቄዎች እንዲሁም ሃሳብ እና አስተያየት በዚህ ላኩልን:

@gibigubaehasb_bot


አ/አ/ሣ/ቴ/ዩ/ግቢ ጉባኤ

ትምህርት ክፍል

Report Page