Geography Tutorial.

Geography Tutorial.


📚 Geography of Ethiopia and The Horn.

📚 Chapter 1 - Meaning and Scope of Geography.

📖TheMeaning, scope, approach and themes of geography.

what is geography❓

📚 It is difficult to forward a definition acceptable to all geographers at all times and places because of the dynamic nature of the discipline and the changes in its scope and method of study.

📌 በሁሉም የጂኦግራፊ ባለሙያዎች ዘንድ ተቀባይነት ያለው ፥ ሁሉንም የ ጂኦግራፊ ባለሙያዎች የሚያስማማ አንድ ወጥ የሆነ የ Geography Definition(ፍቺ) ማግኘት ከባድ ነው። ምክንያቱም ትምህርቱ በተለያዬ ጊዜ የተለያዩ ነገሮችን ስለሚያጠና የተለዋዋጭነት ባህሪ(dynamic nature) አለው፤ እንዲሁም ጂኦግራፊ የተሰማራባቸው መስኮች በጊዜ ሒደት ሊለዋወጡ ስለሚችሉ(change of scope) እና ጂኦግራፊ ነገሮችን የሚያጠናበት ሳይንሳዊ ዘዴ በተለያዬ ምክንያት የመለዋወጥ ባህሪ(change in method of study) ስላለው ፤ ለጂኦግራፊ አንድ ወጥ የሆነ ትርጓሜ(definition) የለውም።

👨‍🏫👩‍🏫 ብዙ ምሁራን ለጂኦግራፊ የራሳቸውን የሆነ ትርጉም ሲሰጡት ይስተዋላል። እንደ Alexander Von Humboldt, Richard Hartshorne, M.Yeates, Martin Kenzer, Gregg Wassmansdorf የመሳሰሉት ወዘተ የራሳቸውን ትርጓሜ ከመስጠት የዘለለ ሁሉንም የሚያስማማ definition አልተገኘለትም። 😁ታዲያ ትርጉሙ በቅጡ የማይታወቅ ትምህርት ነው እየተማርን ያለነው❓

😁ሳይንስ ነው ና define መደረጉ አይቀርም። በብዛት ጥቅም ላይ የሚውለው definition ይህ ነው 👇

📚 Geography is the scientific study of the Earth that describes and analyses spatial and temporal variations of physical, biological and human phenomena, and their interrelationships and dynamism over the surface of the Earth.

🎯 Geography ምድርን(earth) ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ የሚያጠና ነው! ማለትም ምድር ላይ ያሉ ተፈጥሯዊ/አካላዊ(physical) ፤ ባዮሎጂካላዊ ፤ ሰው ሰራሽ ክስተቶችን ና ለውጦችን ያጠናል እንዲሁም ከጊዜ እና ከ ቦታ( spatial and temporal ) አንጻር ተፈጥሯዊ ፥ ባዮሎጂካላዊ ና ሰው ሰራሽ ክስተቶችን ና ለውጦችን የሚተነትን ሳይንስ ነው።

👉 ተፈጥሯዊ/አካላዊ ክስተት(physical phenomenon) ማለት ፥ ስለ ተሯሯው ሜዳው ስለ እሳተ-ገሞራው ስለ አየር ንብረት ወዘተ ማለት ነው።

👉 ባዮሎጂካላዊ ክስተት(Biological Phenomenon) ማለት ደግሞ ፤ ህይወት ያላቸው ነገሮች እርስ በርሳቸው ና ምድር ላይ ካሉ ግዑዝ አካላት ና አካባቢያቸው ጋ ያላቸው ግንኙነት ማለት ነው።😁 National Geography ብታዩ።

👉 ሰው ሰራሽ ክስተት ማለት ደግሞ የሰው በስልጣኔ ና በቴሌክኖሎጂ አልያም በሌላ ምክንያት የሚፈጥራቸው ነገሮች ለምድሪቱ ያለው ጠቀሜታ ና የሚያመጣውን መዘዝ ማለት ነው።

🙌 እሺ አሁን ደግሞ Geography የሚዳስሳቸዉ ቦታዎች(scope) እንመልከት።

 📙Scope of Geography

📌 scope of geography is wide.

📌 The scope of Geography is the surface of the Earth, which is the very thin zone that is the interface of the atmosphere, lithosphere, hydrosphere and biosphere, which provides the habitable zone in which humans are able to live.

🏄‍♀🏂🪂 Scope of Geography ማለት ፤ ጂኦግራፊ ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ የሚያጠናቸው ቦታዎች ፤ የሚዳስሳቸው የተሰማራባቸው መስኮች ማለት ነው። ያ ማለት ምን መሰላችሁ Scope ስንል አንድ subject የት የት ቦታ ላይ ትኩረት እንደሚሰጥ ፥ እስከየት ድረስ እንደሚሰፋ እና ገደቡ እስከ የት እንደሆነ ይነግረናል።

📚 ጂኦግራፈሮች የምድርን ገፅ አካላዊ ባህሪያትን ና በእርሱ ላይ የተንሰራፋውን የሰው ማህበረሰብ የሚያጠኑ ከሆነ ፡ የሚያጠኑት በምን አይነት መንገድ ነው? [ ምንን ተጠቅመው ነው ? ] የGeography ወሰንስ እስከ የት ይሰፋል ? ብለን ብንጠይቅስ እስኪ አስቡ። የgeography ዋና branches እነማን ናቸው?

📍 ስለ scope እንደሱ ካልን ፥ በዚህ ረገድ ጂኦግራፊ ከቦታ ቦታ የበለጠ ሰፊ ነው ፡ በፕላኔቷ ወይም ምድር ላይ ብዙ አይነት ክስተቶችን ያስተናግዳል ። geography ወሰን[ scope ] አለው ? ካለውስ እንዴት ነው የgeography ወሰኑን የምንገልፀው ?

📍Generally, the geo-sphere is considered as geography’s scope.

✅ The geo-sphere itself is made up of five sub spheres, namely :

📍 Lithosphere,

📍 Hydrosphere,

📍 Atmosphere

📍Troposphere and

📍 Anthroposphere.

📚 በአጠቃላይ Geo - sphere እንደ ጂኦግራፊ scope ይቆጠራል። geosphere ራሱ ከአምስት ንዑስ ወሰን የተሰራ ነው ። እነሱም የሚከተሉት ናቸው ። እያንዳንዳቸው የጂኦግራፊን ወሰን እስከየት እንደሚሰፋ ብሎም የት ቦታ ላይ ትኩረት እንደሚያደርግ ያሳዮናል።

📌*Lithosphere : The solid part -i.e. the rock layers of the earth.

👉ጠንካራው ክፍል - ማለትም የምድር ዐለት ንብርብሮች ናቸው lithosphere የሚባለው soilም solid ስለሆነ ከዚው ጋር ይዛመዳል።

📌 Troposphere:- The lower part of the atmosphere where weather changes occur.

🔺የአየር ሁኔታ ለውጦች የሚከሰቱበት የከባቢ አየር የታችኛው ክፍል የሚያጠና ነው።

📌 Hydrosphere : The water surface's of the earth including oceans, seas and lakes.

📍የምድር የውሃ ገጽታዎች ውቅያኖሶችን ፣ ባህሮችን እና ሀይቆችን ጨምሮ የሚያጠና ነው ።

📌Biosphere ፥ The part of the earth that supports all sorts of life

👉ሁሉንም ዓይነት ሕይወት የሚያጠቃልለው የምድር ክፍል ሁሉንም ነፍስ ያላቸው አካላት የሚያጠና የጂኦግራፊ ከፍል ነው ።

➡️ biosphere ህይወት ያላቸውን ነገሮች ነው ሚመለከተው ።

📌Anthroposphere : The earth's cultural landscape :

🪧 የምድር ባህላዊ ገጽታ ነው ያ ማለት ከቦታው አንፃር የተቃኙ ባህሎችን ማለቱ ነው።

📍Geography’s area of study is very wide and diverse in its nature. The subject deals with from the dry land mass of the lithosphere to the extensive oceans of the hydrosphere.

🏷 From the earth’s crust (surface) high into its atmosphere

 (troposphere) and from the natural environment to human-related phenomena.

👉 የጂኦግራፊ ጥናት በጣም ሰፊ እና በባህሪው የተለያየ ነው ፥ ምክንያትቱም ከlithosphere (የደረቅ መሬት) እስከ ሰፊው የውሃ ውቂያኖሶች (hydrosphere) ፣ ከምድር ቅርፊት (earth Crust Surface) ከፍታ ወደ ከባቢ አየር (troposphere) እና ከተፈጥሮ አካባቢ እስከ ሰው ነክ ክስተቶች ድረስ ይመለከታል።

🪧 አረ የምር ጂኦግራፊ ይለያል የማያጠናው የማይገባበት የለም 🙊 ፤ አያቹኣ ስለዚህ ነው geography ሰፊ መስኮች(wide scope) አለው የተባለው።

👉ጅኦግራፍይ የሚዳስሳቸው ቦታዎች በጣም ብዙ ና ሰፊ ነው(wide scope)። እንዴት መሰላችሁ ውዶቼ 😘 ፤ ቅድም ከላይ እንዳየነው geography ስለ ምድር ና በወስጧ ስላሉ ነገሮች ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ የሚያጠና disciplines ነው ብለናል ፤ ምድር ደግሞ በጣም በብዙ ነገር የተሞላች ናት አይደል ለምሳሌ በ ውሃ [hydrosphare] ፤ ህይወት ባላቸው ነገሮች[biosphere] ወዘተ። ቅድም ስለምድር በሳይንሳዊ መንገድ ያጠናል ያልነው ፤ እነነዚህን ሰፊ ነገሮችን ከ ጊዜ እና ከ ቦታ አንፃር ይዞ ይተነትናል ያብራራል 🙌።

ቆይ ግን ከጊዜ እና ከቦታ አንፃር ማለታችን ምን ማለት ነው🤔❓

📮Rift valley እንውሰድ ና በ geography ጥናት መሰረት Rift Valley ስምጥ ሸለቆ የተፈጠረው በ Cenozoic Era ከ 70million አመት በፊት🙆‍♂🙆‍♂ ነበር።

  💁‍♂ geography ደግሞ ምድር ላይ በተፈጥሮም ይሁን ሰው ሰራሽ ክስተቶች ከ ጊዜ አና ከ ቦታ አንፃር ይተነትናል ብለናል ፤ ስለዚህ rift valley ን ከ ጊዜ አኳያ ከ 70 ሚሊዮን ዓመት በፊት ከቦታው አንፃር አፍሪካ ውስጥ ኢትዮጵያ እያለ ይተነትናል ያጠናል።

 📜 Geography can be approached by considering two continuums:

🎯 ጂኦግራፊ ሳይንሳዊ ጥናቱን የሚያካሒደው በ ሁለት ዘዴ(approach) ነው ወይም ጂኦግራፊ ስለ አንድ ነገር ሲያጠና ሁለት ዘዴዎችን መሰረት በማድረግ ነው። እነርሱም፤

🧩1ኛ) human-physical continuum. 

🧩2ኛ) topical-regional continuum.

📖 መማሪያ ሞጁላችሁ ላይ ያለው ስለ ሁለተኛው ዘዴ ስለሆነ የሚያወራው ፤ እሱን እንመልከት።

📚 The topical(systematic) fields of Geography view particular categories of physical or human phenomena as distributed over the Earth.

      E.g air condition of africa

⭐️ Topical Continuum በሌላ ስሙ Systematic Fields of Geography ይባላል።

🙌 ታዲያ ይህ Topical(systematic) Field of Geography በምን አይነት ዘዴ ነው ነገሮችን የሚያጠናው❓

📖 Geograpgy ከ ጊዜና ከ ቦታ አንፃር ምድር ላይ ስለተፈጠሩ ሰው ሰራሽ ወይም ተፈጥሮአዊ ክስተቶች ነው የሚያጠናው ብለናል። ታዲያ ጂኦግራፊ ምድር ላይ ካሉ በጣም በርካታ ተፈጥሯዊም ሆነ ሰው ሰራሽ ክስተቶች መካከል አንዷን ክስተት ብቻ ነጥሎ የሚያጠና ና ስለዛች ክስተት ብቻ የሚተነትን ከሆነ ፤ ይህ የጂኦግራፊ ማጥኛ ዘዴ Topical Approach ይባላል።

🇧🇴🇨🇲🇨🇮 ምሳሌ አፍሪካ አሁጉርን እንመልከት ፤አፍሪካ አህጉር በጣም ሰፊ ነው በውስጡ በርካታ ተፈጥሯዊ ና ሰው ሰራሽ ክስተቶች ይገኙበታል። ለምሳሌ የ ውሀ አካላት💦 ፤ ተራራ⛰️ሸለቆ ሜዳ ኮረብታ ፤ የአየር ሁኔታ🏖️ ፤ ደን 🌿🌱 ፤ ሰዎች ና አካባቢያቸው(population) ፤ አለት ፤ እሳተ ገሞራ ፤ ወዘተ ተዘርዝረው የማያልቁ በጣም በርካታ ነገሮች አሉ። 

🙌 ታዲያ Geography ከነዚህ ከተዘረዘሩት በርካታ ክስተቶች መካከል ፥ አንዷን ክስተት ብቻ ነጥሎ ስለ አንዷ ክስተት የሚያጠና ከሆነ ፤ ይህ የጂኦግራፊ ማጥኚያ ዜዴ Topical(systematic) approach ይባላል። ለምሳሌ ስለ አየር ንብረት ብቻ ነጥሎ የሚያጠና ከሆነ

📚 የ አፍሪካ አየር ንብረት ባህሪን ያጠናል ከዛም ይተነትናል ፣ ስለ ቅዝቃዜው ፣ ስለ የሙቀት መጠኑ በቁጥር በአማካይ ያስቀምጣል ፤ በ 12ቱ ወራቶች የአየር ንብረቱ ምን እንደሚመስል ፤ የአየር ንብረቱ በሆነ አካባቢ ለምን ሞቃታማ እንደሆነ ፥ በሆነ አካባቢ ለምን ቀዝቃዛ እንደሆነ ወዘተ ያጠናል። ያ ማለት ስለ አየር ንብረት ብቻ ወስዶ በስፋት የሚያጠናበት ሲስተም(ዘዴ) ነው። ማን 👀❓Topical Approach ፤ ስለዚህ Topical Approach ስለ አንድ specific(ውስን ጉዳይ) ነው የሚያጠናው።

☺️ Regional Approach of Geography ስ እንዴት ነው የሚያጠናው❓ከ Topical Approach በምን ይለያል❓እስኪ እንመልከተው።

📚 Regional geography is concerned with the associations within regions of all or some of the elements and their interrelationships.

    e.g, geography of africa.

👉 ጂኦግራዊ ምድራዊ ክስተቶችን የሚያጠናበት ሁለተኛው ዜዴ ፤ Regional geography approach ተብሎ ይጠራል።

📖 Geograpgy ከ ጊዜና ከ ቦታ አንፃር ምድር ላይ ስለተፈጠሩ ሰው ሰራሽ ወይም ተፈጥሮአዊ ክስተቶች ነው የሚያጠናው ብለናል። ታዲያ ጂኦግራፊ ምድር ላይ ካሉ በጣም በርካታ ተፈጥሯዊም ሆነ ሰው ሰራሽ ክስተቶች መካከል በሆነ ክልል(ቦታ) ውስጥ የሚገኙ ሁለት ና ከዚያ በላይ የሆኑ ክስተቶችን ሲያጠና ፤ ስለእነዛ ክስተቶች እርስ በርስ ያላቸውን ዝምድና መደጋገፍ ሲያጠና ሲተነትን ፤ Regional geography ተብሎ ይጠራል።

🇧🇴🇨🇲🇨🇮 ምሳሌ አፍሪካ አሁጉርን እንመልከት ፤አፍሪካ አህጉር በጣም ሰፊ ነው በውስጡ በርካታ ተፈጥሯዊ ና ሰው ሰራሽ ክስተቶች ይገኙበታል። ለምሳሌ የ ውሀ አካላት💦 ፤ ተራራ⛰️ሸለቆ ሜዳ ኮረብታ ፤ የአየር ሁኔታ🏖️ ፤ ደን 🌿🌱 ፤ ሰዎች ና አካባቢያቸው(population) ፤ እንስሳት🦁 🐅 🐒 ፤ አለት 🧗‍♂️ ፤ እሳተ ገሞራ ፤ ወዘተ ተዘርዝረው የማያልቁ በጣም በርካታ ነገሮች አሉ። 

🙌 ታዲያ Geography ከነዚህ ከተዘረዘሩት በርካታ ክስተቶች መካከል ፥ ሁለት ና ከዚያ በላይ የሆኑ ክስተቶችን ወይም ሁሉንም ክስተቶች የሚያጠና ከሆነ ና አንዱ ክስተት ከሌላኛው ክስተት ያለውን አሉታዊ ና አዎንታዊ ዝምድና ና ቁርኝነት የሚያጠና ከሆነ ፤ ይህ የጂኦግራፊ ማጥኚያ ዜዴ Regional geography በመባል ይጠራል። ለምሳሌ አፍሪካ ውስጥ ስላለው የአየር ንብረት ፤ አፍሪካ ውስጥ ስላሉ አንስሳት ና አፍሪካ ውስጥ ስላሉ እፅዋት ስለ ሶስቱ በአንድ ላይ የሚያጠና ከሆነ ፤ ይህ የጂኦግራፊ ማጥኚያ ዘዴ Regional Geography ተብሎ ይጠራል።

📚 የአየር ንብረቱ ለየትኞቹ እፅዋት ና እንስሳት ተስማሚ እንደሆነ ፤ በበረሀ አካባቢ የሚኖሩ እንስሳት ና እፅዋት ባህሪያቸው ምን እንደሆነ ፤ በቀዝቃዛ አካባቢ የሚኖሩ እፅዋት ና እንስሳት ባህሪ ና ምንነት ፤ የእፅዋቶቹ ና የአንስሳቶቹ ተፅዕኖ በአየር ንብረቱ ምን እንደሆነ ወዘተ ያጠናል። ያ ማለት ስለ አየር ንብረት ፤ ስለ እፅዋት ፤ ስለ እንስሳት ስለ ሶስቱ ቁርኝነት የሚያጠናበት ዘዴ ነው። 

🙌 ተማሪዎች በ ሁለቱ approch መካከል ያለው ልዩነት ገብቷችሗል❓

😇The topical (systematic) ፤

Specific ወይም ስለ አንድ ነገር ክስተት ብቻ ነው የሚያጠናው። ቅድም በምሳሌው እንዳየነው ስለ አየር ንብረቱ ብቻ የሚያጠናበት ዘዴ ነው።

😇 Regional geography ፤ ስለ በርካታ ክስተቶች ና የነዛ ክስተቶችን ቁርኝት የሚያጠና ዘዴ ነው። ስለ አየር ንብረት ፤ ስለ ደን ፤ ስለ እንስሳት ፤ ስለ ውሀማ አካላት ወዘተ በአንድ ላይ የሚያጠና ነው።

📖Themes of Geography.

👉 Theme ማለት ጭብጥ ፥ መሰረት ፥ ዋና ማዕከል ማለት ነው። ለምሳሌ የዚህ ፊልም ጭብጥ ይባላል አይደል። የፊልሙ ዋና ሀሳብ ማለት ነው፤ ከዛ ሀሳብ በመነሳት ነው ሌሎች የፊልሙ ትወናዎች የሚደረሱት የሚፃፉት ና የሚተወኑት። Geography ም ክስተቶችን የሚያጠናበት ምሰሶ ወይም ጭብጥ አለው፤ እነዚህን ጭብጦች መሰረት በማድረግ ነው የሚያጠናው። የ Geography ጭብጦች እነማን ናቸው❓

📌Geography has five basic themes namely ፡ location, place, human-environment interaction, 

movement, and region.

👉ጂኦግራፊ አምስት መሰረታዊ ጭብጦች አሉት እነሱም location, place, human-environment interaction, 

movement, and region ናቸው ፤ እያንዳንዱን እንመልከት።

🔰Location.

📌 Location is defined as a particular place or position.

🤸‍♂ Location(መገኛ ቦታ) ማለት የአንድ የታወቀ ቦታ አቀማመጥ ወይም መገኛ ማለት ነው። 😁ለምሳሌ ባህርዳር ከአዲስ አበባ በስተምስራቅ 425km ርቀት ላይ ይገኛል። በስተምስራቅ የሚለው የባህርዳርን መገኛ ቦታ አቀማመጥ ያመለክታል።

📌 Most studies of geography begin with the mention of this theme of geography.

👉አብዛኛው የጂኦግራፊ ጥናት የሚጀምረው ይህን Location የተባለ የጂኦግራፊ ጭብጥ በመጥቀስ ነው።

📌Location can be of two types: absolute location and relative location.

Location በሁለት ይከፈላል። እነርሱም ፍፁማዊ ትክከለኛ መገኛ ቦታ(Absolute location) እና አንጻራዊ መገኛ ቦታ(relative location) ናቸው።

In the former case, the location of a place is defined by its latitude and longitude or its exact address.

📌 Absolute location(ፍፁማዊ መገኛ) ማለት ፤ የቦታውን መገኛ በኬክሮስ(latitude )እና በኬንትሮስ(longitude ) የምንገልፅበት ዘዴ ሲሆን ፤ Absolute location ቦታዎችን በትክክል የመግለጫ ዘዴ ነው። ለምሳሌ ኢትዮጵያ በ 35° latitude ና በ 80° longitude ትገኛለች ብንል ይህ Absolute location ይባላል።

📌 Relative Location(አንፃራዊ መገኛ) ማለት ደግሞ ፤ የ አንድን ቦታ መገኛ ስንገልፅ ፤ ቦታውን በሚያዋስኑት ነገሮች የምንገልፅ ከሆነ ነው። የ ውሃ አካል ፥ ተራራ ምናምን እያዋሰንሰ የምንገልፅበት መንገድ ነው። ለምሳሌ ኢትዮጵያ በስተ በሰሜን ከኤርትራ ጋ ፥ በስተምስራቅ ከሶማሊያ ጋ ፤ በስተ ደቡብ ከኬንያ ፤ በስተምስራቅ ከጅቡቲ ጋ ትዋሰናለች ብንል፤ ይህ relative location ይባላል። በሌላ አባባል ኢትዮጵያ ከ ኤርትራ በስተሰሜን ትገኛለች ወዘተ ብለን የምንልፅበት ዘዴ ማለት ነው።

🔰 Place.

📌 Place refers to the physical and human aspects of a location.

👉 Place(ቦታ) ማለት የአንድ አካባቢ ወይም ስፍራ አካላዊ(physical) እና ሰብአዊ(Human) ገጽታዎችን ያመለክታል። ለምሳሌ የኢትዮጵያ መልካምድር ፤ የሰዎች አሰፋፈር ሁኔታን ብንገልፅ።

📌Each place in the world has its unique characteristics expressed in terms of landforms, hydrology, biogeography, pedology,characteristics and size of its human population, and the distinct human cultures.

   👉በዓለም 🌎ውስጥ ያለው እያንዳንዱ ቦታ የራሱ የሆነ ልዩ ባህሪ ና መገለጫ አለው። ስለዚህ እያንዳንዱ ቦታ(place) በመሬት አቀማመመጡ ፣ በሃይድሮሎጂ(ባሉት ውሀማ አካላት) ፣ ባዮጂኦግራፊ(ህይወት ያላቸው ነገሮች አሰፋፈር) ፣ ፔዶሎጂ ፣በሰዎቹ ብዛት ወዘተ ነው የሚገለፀው።

🔰 Human-Environment Interaction

📌Humans have always been on ceaseless interaction with their natural environment.

👉 ሰዎች ሁልጊዜ ከተፈጥሮ ና አካባቢያቸው ጋር የማያቋርጥ( ceaseless)መስተጋብር አላቸው።

📌Thus, human-environment interaction involves three distinct aspects. 1)dependency,

2)adaptation,

3) modification.

👨‍🏫👩‍🏫 የሰው ልጅ ከ አካባቢው ጋ የሚያደርገው መስተጋብር ሶስት መገለጫዎች አሉት።

1) Dependency refers to the ways in which humans are dependent on nature for a living.

1ኛ) Dependency(ጥገኝነት) የሰው ልጅ ለመኖር ከተፈጥሮ ጋር ጥገኛ ነው። የተፈጥሮን እገዛ ይፈልጋል፤ ያለ ተፈጥሮ መኖር አይችልም።

2) 🎡Adaptation relates to how humans modify themselves, their lifestyles and their behavior to live in a new environment with new challenges.

2ኛ) Adaptation(መላመድ) ፤ ሰዎች እራሳቸውን በአዲስ አካባቢ ውስጥ ለመኖር ከአዳዲስ ችግሮች ጋ ተላምደው ለመኖር ራሳቸዉን እንደሚያሻሽሉ እንዲሁም የአኗኗር ዘይቤዎች እና ባህሪያቸው ይቀይራሉ። ምሳሌ በጣም ወደ ደጋ አካባቢ ይበርዳል እዛ ቦታ ለመኖረ እና ለመልመድ ሰዎች እራሳቸውን ያሻሽላሉ እዛ አካባቢ ያለውን ችግር መቀየር ባይችሉም ተቃቁመው ወይም ለምደው ለመኖር ልብሶችን በመደረብ ተላምደው ይኖራሉ እንጂ ሁኔታውን አይቀይሩትም።

3) 🎡 Modification allowed humans to “conquer” the world for their comfortable living.

3ኛ) Modification(ማሻሻል) ፤ ሰዎች ለኑሯቸው አመቺ በሆነ መልኩ አካባቢያቸውን ወይም ዓለምን የመፍጠር ና የማሻሻል ፀጋ ና አቅም አላቸው ።

             🔰Movement 

📚 Movement entails to the translocation of human beings, their goods, and their ideas from one end of the planet to another.

📌 አራተኛው የ Geography ጭብጥ ፤ Movement(እንቅስቃሴ) ነው። Movement ማለት የሰው ልጅ ከቦታ ቦታ ከአንዱ የአለም ክፍል ወደሌላኛው የአለም ክፍል ፤ ንብረቱን ሀሳቡን ማዘዋወር ማለት ነው እንዲሁም ሰዎች ራሳቸው ከቦታ ቦታ መዘዋወር ማለት ነው።

🔰Region

📚 A region is a geographic area having distinctive characteristics that distinguishes itself from adjacent unit(s) of space.

 🙌 አምስተኛውና የመጨረሻው የ ጂኦግራፊ ጭብጥ Region(ክልል) ማለት ነው። 😁ክልል ሲባል አማራ ክልል ደቡብ ክልል ምናምን ብቻ ማለት አይደለም። Region ማለት በአንድ ውስን ና ግልፅ የሆነ ቦታ የታቀፈ ፤ ከሌላው አካባቢ የሚለይበት የራሱ የሆነ መገለጫ ባህሪያቶች ያሉት ማለት ነው።

📌 It could be a formal region that is characterized by homogeneity in 

terms of a certain phenomenon (soil, temperature, rainfall, or other cultural elements like language, religion, and economy)

📚 በአንድ በሆነ ክስተት ማለትም (አፈር ፣ ሙቀት ፣ ዝናብ ፣ ወይም ሌሎች ባህላዊ አካላት ቋንቋ፣ ሃይማኖት እና ኢኮኖሚ) ወዘተ አንድነት አንድነት ካለው formal region ይባላል።

📌It can also be a functional or nodal region characterized by 

functional interrelationships in a spatial system defined by the linkages binding particular

phenomena.

🙌ለዛሬ ከዚህ ላይ እናብቃ ፤ በቀጣይ የቀረውን ክፍል እናያለን። መልካም ጊዜ📌

©️ A+ Tutorial Class.

ለመመዝገብ @Aplustutoriallbot ን ይጠቀሙ።

Report Page