Furn print hopr12

Furn print hopr12


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ጽ/ቤት ከዚህ በታች ለተጠቀሱት እቃ የመንግስትን ግዥ መስፈርቶች የሚያሟሉ እና በዘርፉ ከተሰማሩ ህጋዊ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

1. ሎት1 ፡- ለ2ኛ ጊዜ የወጣ Heavy duty high speed copy Printer ግዥ
2. ሎት 2፡- ለ2ኛ ጊዜ የወጣ የሕትመት ውጤቶች (አጀንዳ፣የጠረጴዛ ካላንደር፣የኪስ ካላንደር፣ የእንኳን አደረሳችሁ ካርድ፣ የምክር ቤቱ ሎጎ የታተመበት እስክርቢቶ እና የምክር ቤቱ ሎጎ የታተመበት ቁልፍ መያዝ ግዥ
3. ሎት 3፡- ለ2ኛ ጊዜ የወጣ የኮቲንግ ዲስፕሌይ ሲስተም ግዥ
4. ሎት 4፡- ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የተለያዩ የቢሮ ፈርኒቸር ግዥ
ተጫራቾች አግባብ ያለው የዘመኑ ግብር የተከፈለበት እና የታደሰ ንግድ ሥራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ሊስት ላይ የተመዘገቡና በጨረታ ላይ መሳተፍ የሚያስችል ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ የተጨማሪ እሴት ታክስ እና የግብር ከፋይነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ

5. የጨረታ ሰነዱን ለሚወዳደሩበት ሎት የማይመለ ስ ብር 50.00 ( ሃምሳ ብር) በመክፈል ይህ ማ ስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናቶች ዘወትር በሥራ ቀንና ሰዓት ግዥ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 1 በመቅረብ ለሚፈልጉት የሰነድ ዓይነት ክፍያ ፈጽመው ሰነዱን አንደኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 12 ከግዥ ክፍል መውሰድ ይችላሉ፣

6. ተጫራቾች ከላይ ለተጠቀሱት፡-፣ ሎት 1 Heavy duty high speed copy Printer ግዥ 13,000.00( አስራ ሶስት ሺ ብር ብቻ) ፣ሎት 2 የሕትመት ውጤቶች 10,000.00( አስር ሺህ ብር) ሎት 3 ፡- የቮቲንግ ዲስፕሌይ ሲስተም ግዥ 10,000.00( አስር ሺህ ብር) ፣ እና ሎት 4 ፡- የተለያዩ የቢሮ ፈርኒቸር ግዥ 5,000.00 ( አምስት ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ CPO በጥሬ ገንዘብ ለጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

7. አሸናፊው ድርጅት እንደታወቀ ውል ለመዋዋል የሚያስችል ለአሸነፈው እቃ ከጠቅላላ ዋጋ 10% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም ቢድ ቦንድ የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፣

8. ሲፒኦ ወይም ቢድ ቦንድ ሲዘጋጅ፡- በአማርኛ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ጽ/ቤት በእንግሊዝኛ secretariat of The House of People's Representative በሚል መዘጋጀት ይኖርበታል፡

9. ተጫራቾች ለሚያቀርቧቸው ዕቃዎች ዋጋ ፋይናንሻል፤ ቴክኒካል፣ ኦርጅናል እና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16 ኛው ቀን ጠዋት ከ4 ፡00 ሰዓት በፊት ሁለተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 46 ከግዥ ክፍል አካባቢ ለዚህ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ የመጫረቻ ሰነዱን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

10. የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ላይ ከወጣበት 16 ኛው ቀን 4 ፡00 ሠዓት ላይ የጨረታ ሣጥኑ ታሽጎ በእለቱ 4 ፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ለዚሁ በተዘጋጀው አዳራሽ በግልጽ ይከፈታል፣

11. የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጽ/ቤት የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ መሆኑን እንገልፃለን።

12 ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር ፡- 0111-24-1037 የውስጥ መስመ ር 195 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፣

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጽ/ ቤት


Posted: አዲስ ዘመን ግንቦት 08 ቀን 2012

Deadline: May 31, 2020


© walia tender


Report Page