Furn 1 dmu bure campus1

Furn 1 dmu bure campus1


ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ

የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር ብግጨ 10/2012

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ቡሬ ካምፓስ በ2012 የበጀት አመት ከመንግስት በተመደበለት በጀት ለካምፓሱ ለኮምፒውተር ላብራቶሪ አገልግሎት የሚውል ጠረጴዛ /Table/ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሰረት በጨረታ መወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርበታል፡፡

በዘመኑ የታደሰ ንግድ ስራ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ እና የቲን ምዝገባ የምስክር ወረቀት ፤ ማቅረብ የሚችሉ ፤
ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድዋጋሞልተው ሲመለሱ ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ብር 15000.00 / አስራ አምስት ሺህ ብር / በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ቡሬ ካምፓስ ስም ማስያዝ የሚችሉ፤ እንዲሁም ጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ካደራጃቸው አካል በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ቡሬ ካምፓስ ስም የሚጻፍ የዋስትና ደብዳቤ አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
የጨረታውን ፋይና ኦርጅናል እና ኮፒ እንዲሁም ማስከበሪያውን ለየብቻው አስተማማኝ በሆነ ማጣበቂያ በታሸገ ፖስታ በማድረግና በእያንዳንዱ ፖስታ ላይ የአሰሪ መስሪያ ቤቱን ሙሉ ስምና አድራሻ በመፃፍ ፊርማና ማህተም በማድረግ በተጠቃለለ በአንድ ፖስታ በማሸግ ማቅረብ የሚችል ፤
አሸናፊው ተጫራች አሸናፊነቱ በተገለጸለት ከ7 የስራ ቀናት በኋላ ከ8ኛው ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 8 የስራ ቀናት ውስጥ አሸናፊ የሆነበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና የውል ማስከበሪያ በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ቡሬ ካምፓስ ስም በማሰራት ውል መያዝ የሚችል ፤
የጨረታ ሰነዱን ከደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ቡሬ ካምፓስ ህንጻ 13 ግዥ አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 03 በአካል በመቅረብ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ መስፈርቱን የሚያሟሉ ሁሉ የጨረታ ዶክመንቱን እስከ ግንቦት 28/2012 ዓ . ም ከጥዋቱ 3 ፡ 30 ሰዓት ድረስ የማይመለስ 100.00/ አንድ መቶ ብር / በመክፈል መግዛት ይቻላል፡፡
የጨረታ መክፈቻና መዝጊያ ቀን

ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በአግባቡ በመሙላትና በማሸግ ግ ንቦት 28/2012 ዓ . ም ከጠዋቱ 3 ፡ 59 ሰዓት ድረስ በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ቡሬ ካምፓስ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ መመለስ ይኖርባቸዋል፡፡ጨረታው ግንቦት 28/2012 ዓ . ም 4 ፡ 00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ እለት ከጠዋቱ 4 ፡ 30 ሰዓት ላይ ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ቡሬ ካምፓስ ህንጻ 13 ግዥ አስተዳድር ቡድን ቢሮ ቁጥር 03 በተገኙት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ፊት ይከፈታል፡፡ሆኖም ተጫራቾች በጨረታው ላይ መገኘት ካልቻሉ መስፈርቱን እስካሟሉ ድረስ በጨረታው ላይ ያልተገኙ ተጫራቾችን ፖስታ ጨምሮ ጨረታው በእለቱ ይከፈታል፡፡

ዩኒቨርሲቲው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 058-774-11-49 /09-1311-09-84

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ቡሬ ካምፓስ መጠየቅ ይቻላል፡፡

በደብረማርቆስ ዩኒቨርሰቲ

ቡሬ ካምፓስ



Posted:አዲስ ዘመን ግንቦት 09 ቀን 2012

Deadline: June 5, 2020


© walia tender

Report Page