Freshman course information

Freshman course information

University information

 የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች የመጀመሪያ አመት የመጀመሪያው ሴሚስተር ላይ የምትወስዷቸው ኮርሶች👇


📌 Communicative English Skill I


📌 Economics

 

📌 Geography


📌 Maths(Social) 


📌 Logic and Critical Thinking 


📌 General Psychology 


📌 Physical Fitness 


🙌 አሁን ደግሞ ስለ እያንዳንዱ ኮርስ መጠነኛ የሆነ ገለፃ ወይም ጅንጀና እናድርግ።


      🎯 Communicative English Skill I


ይህ ኮርስ የብዙ ተማሪዎችን ውጤት የሚያነሳ ነው እንግሊዝኛ ሞካሪ ከሆናችሁ። በዚህ ኮርስ በዋናነት የምትማሩት  


🗞 Speaking skill ( ከ ክላስ presentation ታቀርባላችሁ። ማርክ አለው ፡ ስለዚህ ስታቀርቡ እንዳትፈሩ።) 


🗞 Reading skill ( ልክ Entrance እንደተፈተናችሁ አይነት የ passage ጥያቄ ትፈተናላችሁ።) 


🗞 Writing skill ( የስራ ማመልከቻ ደብዳቤ ( application letter) ፃፋ ልትባሉ ትችላላችሁ ፡ descriptive paragraph ፃፋ ልትባሉ ትችላላችሁ ወዘተ)


🗞 Grammar( Tense , passive and active voice , reported speech , conditional sentence, Modal Verbs etc ትማራላችሁ። mid exam, final exam እና CoC exam ላይ passive and active voice እና conditional sentence ብዙ ጥያቄ ስለሚወጡ ትኩረት ሰጥታችሁ በማንበብ ተረዱት።)


              🎯 Economics 


📚 ግቢ ላይ ብዙ ሰቃይ ተማሪዎች Economics ን አይሰሩትም🙇‍♂። 3.7 or 3.8 ያላቸው ልጆች Economics ን B- ምናምን ነው የሚያመጡት። ምን ልላችሁ ፈልጌ ነው ግቢ ላይ የ Economics ትምህርት ፈተናዎች ወይም ጥያቄዎች conceptual ናቸው። ስለዚህ Economics ን ስታነቡ አትሸምድዱ። በቻላችሁት መጠን ሳይንሱን ለመረዳት ሞክሩ ፡ ተግባራዊ እውነታውን ተረዱ ማለትም Economics የዋጋ ግሽበትን ለመቀነስ ፡ የማህበረሰቡን ኑሮ ለማቅለል ያለውን ሳይንሳዊ ፋይዳ ተረዱት። 11 እና 12 የተማራችሁት የ Economics ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ስትገቡም ስለሚጠቅማችሁ የ 11 & 12 ኛ ክፍል Economics መፅሀፍ pdf ቢኖራችሁ አሪፍ ነው።Extreme Economics👌


             🎯 Geography


📚 ለ Social science ተማሪ Geography አዲስ አይደለም። ግቢ ላይ የምትማሩትም የ Geography ትምህርትም አዲስ አይደለም። በዋናነት የኢትዮጵያን እና የምስራቅ አፍሪካን መልክአምድራዊ ገፅታ ነው በዚህ ኮርስ የምትማሩት ። ለ Geography ም አዲስ አይደላችሁም። ነገር ግን ይህ ትምህርት አንዴ ተነቦ የሚተው አደለም በተፈጥሮው ይተናል ብል ይቀላኛል 🤷‍♂ ስለዚህ ብትችሉ ስታነቡ Note ያዙ ቀጣይ ስትደግሙት Note ብቻ ማንበብ ነው የሚጠበቅባቹ ከ module ውጪ ፈተና አይወጣም PPT እንደ Apetizer ውሰዱ 😂 እንዳልኳቹ ስለሚረሳ ቶሎ ቶሎ ሳይበዛ ከልሱት አንዳንዴ Module ስታነቡት ደስ ላይል ሰለሚችል Note እየያዛቹ ዋና ዋና ነጥቡን አንብቡ 👍::


           🎯 Maths (Social)


ከ መጠነኛ ለውጥ ( modification) ውጭ 11 እና 12 የተማራችሁት ነው። 📚 በይበልጥ ፈተና ሲውጣ Basic ነገር ነው የሚያወጡት Module ማንበብ ለዚ ግዜ በጣም ወሳኝ ነው Module በደምብ ሳታነቡ Reference እንዳገልጡ አደራ Defintion , Properties , Exercises ..... module ላይ ያለውን በደምብ ያዙ የሚሰጣቹ Course outline ላይ ያለውንም ነጥብ በደምብ ተመልከቱ ምን ላይ ማተኮር እንዳለባቹ ይረዳቹሀል::



        🎯 Logic and Critical Thinking


ይህ ኮርስ ለእናንተ አዲስ ነው። የዚህ ትምህርት መሰረቱ ፍልስፍና እና ምክንያታዊነት ነው። ስለዚህ የእናንተ የመረዳት ችሎታ እና አገናዛቢነት በዚህ ኮርስ በእጅጉ ይፈተናል። የማስጠነቅቃችሁ ነገር ቢኖር ይህን ትምህርት ስታነቡ ገረፍ ገረፍ አድርጋችሁ ወይም ላይ ላዩን በፍፁም እንዳታነቡ። ፅንሰ ሀሳቡ ገብቷችሁ ነው ማንበብ ያለባችሁ ምክንያቱም አንድ በአንድ ካልገባችሁ ፈተናውን ለመስራት ትቸገራላችሁ። ሽምደዳ ብዙም አያዋጣችሁም እዚህ ኮርስ ላይ። ስለዚህ ለመረዳት ሞክሩ። ለዚህ ኮርስ አጋዥ የሆኑ ሁለት ምርጥ መፅሀፎችን ልንገራችሁ፡


1ኛው) Freshman Logic የሚለው መፅሀፍ ነው። ይህ መፅሀፍ በተወሰነ መልኩ በ አማርኛ እያብራራ ስለሚያስረዳ ብታነቡት ሳይንሱን በቀላሉ እና ቶሎ ትረዱታላችሁ። 

የዚህ መፅሀፍ መገኛ ላይብረሪ በተለይም ሶሻል ላይብረሪ ታገኙታላችሁ።


2ኛው) Concise Introduction to Logic የሚለው ነው። ይህ መፅሀፍ የከባባድ ጥያቄዎች መፍለቂያ ነው። የግቢ መምህሮች ይህን መፅሀፍ በብዛት ይጠቀሙበታል በተለይ ጥያቄ ለማውጣት። በቃ በአጭሩ ከዚህ መፅሀፍ ላይ ያሉትን ጥያቄዎች ቀጥታ ፈተና ላይ ያወጡታል🤓። ስለዚህ እዚህ መፅሀፍ ላይ ያሉትን ጥያቄዎች ስሯቸው። መፅሀፋ በ pdf ስላለኝ በቀጣይ በዚህ ቻናል እለቅላችሗለሁ።


           🎯 General Psychology


📚ይህ ኮርስ በብዙ መልኩ አድስ ሊሆንባችሁ ይችላል:: ይህ ትምህርት ለየትው የሚያረገው በደምብ መረዳትን ይጠይቃል Module ካነበባችሁ በቂ ቢሆንም Module በደምብ የማያብራራው ሀሳብ ስለሚኖር Google ማድረግ በጣም ተመራጭ ነው በይበልጥ ከ ምዕራፍ 3 ጀምሮ የ Case ጥያቄ ስለሚበዛ በደም Exercise መስራት ይጠቅማቹሀል በቀላሉ Google ላይ በ Topicu ርዕስ worksheet search ብታረጉ ከፈተናው ተመሳሳይ ጥያቄ ታገኛላቹ።

ሌላኛው አማራጭ YouTube ነው እኛ ሀገር በስፋት ባይለመድም በአጭር ግዜ Concept ለመረዳት ፍቱን ነው ሞክሩት ።

11 ምዕራፎች ሲኖሩት ቢበዛ እስከ ምዕራፍ 8 ብትማሩ ነው አታስቡ A+ የናንተ ናት 👍


           🎯 Physical Fitness 


📚 ይህ ኮርስ ውጤት የለውም። ማለትም A, B+ ,C ምናምን ተብሎ Grade አይሰራለትም። pass or fail ነው የምትባሉት። ኳስ ሜዳ ወጥታችሁ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን ነው የምትሰሩት ፡ ስለዚህ የስፖርት ትጥቅ ያስፈልጋችሗል። attendance ካልቀራችሁ እና መምህሩ የሚያሰራችሁን ስፖርት ከሰራችሁ pass ትባላላችሁ ማለትም ታልፋላችሁ።

https://t.me/Campus_Info_bot


https://t.me/Campus_Info_bot


Report Page