Freedom & Equality Party

Freedom & Equality Party

Tikvah-Ethiopia

ነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ ፦

ነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ በይፋ የምርጫ ቅስቀሳውን ማካሄድ መጀመሩን የፓርቲው ሊቀመንበር አብዱልቃድር አደም ገልፀውልናል።

ፓርቲው የምርጫ ቅስቀሳ የጀመረው በአዲስ አበባ ከተማ ሲሆን በጎዳና ላይ የምርጫ ቅስቀሳ አድርጓል።

በቀጣይ በስፋት በሀገር አቀፍ ደረጀ ወደ ምርጫ ቀስቀሳ እንደሚገባ ዶ/ር አብዱልቃድር አሳውቀውናል።

ነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ አሁን ላይ የእጩ የማስመዝገብ ስራ ላይ በትኩረት እየሰራ ነው።

በየክልሉ ያሉት የፓርቲው አደረጃጀቶችን ሰፊ ትኩረት ሰጥተው እየሰሩ የሚገኙት በዚሁ በእጩ የማስመዝገብ ስራ ላይ ነው።

ጎን ለጎን እንዲሁም ምዝገባው እንዳለቀ ነፃነት እና እኩብነት ፓርቲ በሰፊው የምርጫ ቅስቀሳ ለመስራት ዝግጅት እያደረገ ይገኛል።

ነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ የአዲስ አባባ ቅስቀሳ እንዴት ነበር ?

ነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ በጀመረበት አዲስ አበባ ከተማ ይሄ ነው ተብሎ የሚገልፅ ምንም ችግር እንዳልገጠመው አሳውቆናል። ቅስቀሳው በሁሉም ክፍለከተማ በሰላማዊ እና በተሳካ ሁኔታ ነው የተካሄደው።

ነገር ግን ፓርቲው ወደክልል በሚወርድበት ጊዜ ችግር ይገጥመኛል የሚል ስጋት አለው ይህም የመነጫው አሁን ላይ ሌሎች ፓርቲዎች ችግር እየገጠመን ነው በማለት ሪፖርት እያደረጉ በመሆኑ ነው።

ሌላው በርካታ የቲክቫህ አባላት ነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ ለምንድነው በስፋት በሚዲያዎች ላይ የማናገኘው የሚል ጥያቄ አንስታችኃል ፤ ለዚህም የፓርቲውን ሊቀመንበር ዶ/ር አብዱልቃድርን ጠይቀናል።

ዶ/ር አብዱልቃድር አደም ፥ ነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ ባሉት የሚዲያ አማራጮች እንደሚንቀሳቀስ ገልፀዋል፤ ነገር ግን የፖለቲካ ጉዳይ ጥንቃቄ የሚፈልግ በመሆኑ ፓርቲው በሚዲያ ላይ ወጥቶ ወደህዝብ ለሚያስተላልፈው መልዕክት ከፍተኛ ጥንቃቄ እንደሚያደርግ አብራርተዋል። 

ያም ሆኖ ግን ፓርቲው በአግባቡ ሚዲያዎችን እንደሚጠቀም ገልፀዋል።

ፓርቲው ሚዛናዊ ለሆን እንደሚጥርና ባለፉት 2 ዓመት ህዝብ ፊት ከመቅረቡ በፊት ጠንካራ ዝግጅት ሲያደርግ እንደነበር ዶ/ር አብዱልቃድር አስታውሰዋል፤ ከተለመደው መንገድ ወጣ ባለመልኩ አስፈላጊውን ዝግጅት ካጠናቀቀ በኃላ በምርጫው ላይ በስፋት ለመስራት አቅዶ ሲቀሳቀ ነበር ብለዋል።

ከዚህ በኃላ ነፃናት እና እኩልነት ፓርቲ ከዚህ ቀደም ከነበረው በላቀ ሁኔታ እጅግ በጣም በስፋት ያሉትን የሚዲያ አማራጮች በመጠቀም ህዝብ ጋር እንደሚደርስ ዶ/ር አብዱልቃድር ገልፀውልናል።


ቲክቫህ ኢትዮጵያ

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

Report Page