For my Substitute
Pursuing Holinessአንተ
የሁሉ ፈጣሪ፣ ፍፁም ቅዱስ፣ ፍፁም መልካም፣ ለቃልኪዳንህ ታማኝ፣ በምህረትህ ባለጠጋ፣ በመግቦትህ ለጋስ፣ እጅግ ሩህሩህና ቸር.. ፍቅር ፤ የፍቅሮች ሁሉ አውራ።
And me.. well, I'm everything but that. ቅድስናህ የሚያሳየኝ ምን ያህል እንደአንተ እንዳልሆንኩ ነው። ለዚህ ነው ከምንም በላይ ሁልጊዜ እንደኢዮብ “በሁለታችን ላይ እጅ የሚጭን፣ በመካከላችንም የሚዳኝ ቢኖር.." (ኢዮብ 9፥33) እያልኩ መካከለኛ ፍለጋ የምኳትነው። አንተን ለአፍታ ትክ ብዬ ባይህ ጠበቃዬ ሆኖ የሚወክለኝን ፃዲቅ ፍለጋ እንከራተታለው እንጂ በምን አቅሜ ደፍሬ ቀርብሀለው?
"አንድ ሰው ሌላውን ቢበድል፣ እግዚአብሔር ጣልቃ ገብቶ ይፈርዳል፤ ነገር ግን ሰው እግዚአብሔርን ቢበድል፣ ማን ይማልድለታል? (1ኛ ሳሙ 2፥25) This reminds me of a story. ሽባ የነበረ ወዳጃቸው እንዲፈወስ ጣርያ ነድለው ወደኢየሱስ ሲያቀርቡት ጌታ እምነታቸውን አይቶ ያለው "ሀጥያትህ ተሰረየችልህ" ነበር።
This is stunning for so many reasons. ሲጀመር ሀጥያትን ይቅር የሚለው ተበዳይ ብቻ ነው። ታስሬ እየተቀጣሁ random ሰው መጥቶ ነፃ ነሽ ቢለኝ ምንም ጥቅም የለውም። የማስተሰረይ፣ የሀጥያትን ዋጋ የመክፈል የማወራረድ ስልጣን ያለው ዳኛው ብቻ ነው። በዚህም ክርስቶስ ጌታና ፈራጅ መሆኑን እናውቃለን።
በእርግጠኝነት ወዳጆቹም ጎበዙም ግር ብሏቸዋል። የሄዱበት አላማና ለነሱ ትልቅ የመሰላቸው ችግር ሌላ፣ ያገኙት መልስ ሌላ።This is still so relevant in our lives. We think our deepest need, our main problem is our suffering. Not sin. So we chase ease and comfort instead of forgiveness. "The degree to which you see your own need of forgiveness is the measure of how clearly you understand the Gospel." And this is the Gospel..
“እኛ በእርሱ ሆነን የእግዚአብሔር ጽድቅ እንድንሆን፣ ኀጢአት የሌለበትን እርሱን እግዚአብሔር ስለ እኛ ኀጢአት አደረገው።” (2ኛ ቆሮ 5፥21) ቅዱስና ነቀፋ የሌለበት ንፁህ ፤ ከሰማያት በላይ የከበረው ሊቀካህናት ክርስቶስ መስዋዕት ለመሆን መጣ።
መቶ የህይወት እድሎች ቢሰጡኝና ደጋግሜ ብሞክር attain ላደርግ የማልችለውን ፅድቅና ለህግህ ታማኝ መሆንን፣ መታዘዝን ችረኸኝ የእኔን በደልና አመፅ በሙሉ ወሰደክ። በክቡር ደምህ ዋጀኸኝ። የፀጋህ ክብር ይመሰገን ዘንድ ከታላቅ ፍቅርህ የተነሳ የኔን መስቀል ተሸከምህ። የእኔን ውረደት ተከናነብክ። መራቆት፣ መጠማት፣ ግርፋት የሚገባኝ ለእኔ ነበር። ልዘለፍ ፣ ሊለገጥብኝ፣ ሊተፋብኝ የሚገባኝ እኔው ነበርኩ። ስቅዩው ሎሌ ግን አዝነህልኝ በትህትና በህማምህ አገለገልከኝ።
“ታዲያ የሚኰንን ማን ነው? የሞተው፣ እንዲሁም ከሞት የተነሣው፣ በእግዚአብሔር ቀኝ የተቀመጠው ክርስቶስ ኢየሱስ፣ ስለ እኛ ይማልዳል።” (ሮሜ 8፥34) ዛሬም ብርታቴ አንተ ነህና እንደድካሜ ለራሴ አልተውከኝም። በፈተና እሳት ባለፍኩኝ ጊዜ እምነቴ የፀናው በራሴ አቅም እንዳልሆነ ጠንቅቄ አውቃለው።
ሰይጣን እንደስንዴ ሊያበጥረኝ ሲሰናዳ እኔም የጦር ዕቃን ለመታጠቅ ስሰንፍ እምነቴ ጠፍቶ ልሰናከል የምችልባቸው ስንት ጊዜያቶች አለፉ?
ኢየሱስ ክርስቶስ የናዝሬቱ..መካከለኛዬ ፣ ወኪሌ ጠበቃዬ ፤ ራሴን የምጥልብህ ማረፊያ አምባዬ፤ የምሸሸግብህ ሰንጣቃው አለቴ፤ እኔ ሳልታመን እንኳን ታማኝ ሆነህ የምትኖር ቤዛዬ ነህና ባንተ እፅናናለሁ።
ምንም እንኳን እንደሰው ለአይን የሚስብ ውበት ወይ ግርማ የሚያስወድድ መልክ ሳይኖርህ ተንቀህና ተጠልተህ የመጣህ ስቅዩ ሰው ሆነህ ብትመጣም በህማምህና በመስቀልህ ያንፀባረቅከው ውበትና ግርማ ግን የዘለዓለም ውዳሴዬ ነው።
ማንነትህና ስራህ ያልገባቸው ሁሉ ፊታቸውን ያዞሩብሀል። ነገርግን አንተን በሞትህ ያዩህ.. ደዌያችንን እንደወሰድህ.. ሕመማችንንም እንደተሸከምክ ፤ ስለ መተላለፋችን እንደተወጋህ ስለ በደላችንም እንደደቀቅህና በአንተ ቅጣት ለእኛ ሰላም እንደመጣ የገባቸው ሁሉ ይሰግዱልሀል።
ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ። መልካም ነገር ሁሉ የተገባህ ፍፁም አምላክና ሰው። ሀያሉ አምላክ የዘለዓለም አባት ስጋን ለብሰህ በፈጠርከው ፍጥረት ውስጥ ፍጥረትህን ሆነህ ገባህ።
You didn't come as a wealthy king expecting to be served though you owned the entire world, You humbled yourself to identify with the poor, the oppresed and the despised.የትህትናህን ልክ ገና መች ተረዳነው..
እንደ በጎች ተቅበዝብዘን በየራሳችን መንገድ የነጐድነውን በደል ሁሉ አባትህ በአንተ ላይ አኖረው። መጨነቅህ፤ ስቃይህ ስለኛ ነው። እንደ ጠቦት ለዕርድ ስትነዳ፤ በሸላቾች ፊት ዝም እንደሚል በግ፣ አፍህን አልከፈትክም።ምንም ተንኰል ሳይገኝብህ፣ ያለ ወንጀልህ የክፉዎችን ሞት ሞትክ።
በአብ ፍቃድ ድቀቅህ፤ ነፍስህ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የኀጢአት መሥዋዕት ሆነልን። ከነፍስህ ሥቃይ በኋላ ብዙዎችን አፀደቅህ ፣ ደስም አለህ። እስከ ሞት ድረስ ህይወትህን አሳልፎ ለመስጠት ሳትሰስት፣ መልካሙ ከክፉ አድራጊዎችም ጋር ተቆጠርክ። የብዙዎችን ኀጢአት ተሸክመህ ስለ ዐመፀኞችም ማለድክ።
ትሁቱ አምላኬ..ያንተን የእግር ጠፍር እንኳ ሊፈታ የሚገባው የለም። ምንም እንኳን ለብዙዎች እዚህ ግባ ማትባል አይሁዳዊ የህማም ሰው ሆነህ ብትመጣ ጉልበት ሁሉ የሚሰግድልህን ቀን የቀጠርህ ባለግርማ ንጉስ የሀጥያንን እድፍ ልታፀዳ ዝቅ አልህ። በከበረው ደምህ ከአንተ ያጣላን ሀጥያት ያሳደፈውን ህይወታችንን ባታጠራልን ማን ከአንተ ጋር እድል ፈንታ ይኖረው ነበር?
ስለዚህ ስምህን ስጠራ አላፍርም። አይተውህ ስምህን ሲያሞግሱልኝ ደስ ይለኛል። ታርደሀልና፤ በፍቅርህም ገዝተኸኛልና እኔነቴ ፍቅሬ ሙሉ ጊዜዬ ሀሳቤ ቀልቤ ቀኔ ዘመኔ ሁሉ ላንተ ብቻ ይገባሀል።
በስቃይ የደቀቀው መሲህ ለኔ ቤዛነት ሲል የሞተው ሞትና በትንሳኤው ያመጣልኝ የሀጥያት ስርየት ትምክህቴ ነው። እንደውድና ክቡር መዝገብ ፣ መተኪያ እንደሌለው ዕንቁ ሀሴት የማደርግበትን መስቀል ትቼ ወዴትም አልሄድም። ደግሞ ከጎልጎታ መራቅ ህይወትን ብኩን ሲያደርግ እንጂ እፎይታ ሲያመጣ አይተን አናውቅም።
የሆንከውን ሁሉ የሆንኩበት መስቀልህን፣ ሞትና ትንሳኤህም ዘውትር የሚወሳ ጀብዱ፣ ዜና፤ ትዝታዬ እንጂ የአንድቀን ሆይ'ሆይታ (ብቻ) አይሁንብኝ።