Finfinne Press
Fastinfo99በትግራይ ሕዝብ ላይ በተካሄደው የዘር ማጥፋት ወንጀል ግንባር ቀደም ተሳታፊ ወንጀለኛና፤ ከትግራይ ጋር በሂደት ላይ ያለው ሰላም ዕንቅልፍ የነሳው የአዲስ አበባው ሲኖዶስ እነ አቶ ጴጥሮስ፤ መረን አልባ ወንጀለኛ በትግራይ ኦርቶዶክስ ቤተ ክህነት መንበረ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን ላይ ያልተገራ አፉን ዳግም መክፈት ጀምሯል::
ይህ እስከ አንድ ሚልዮን በሚደርስ የትግራይ ሕዝብ ደም የተጨማለቀ፣ በትግራይ ገዳማትና መስጊዶች ውድመትና በንዋየ ቅዱሳት ስርቆትና ሽያጭ ከእነ ዳንኤል ክብረት ጋር ግንባር ቀደም ተዋናይ የሆነ የጦር ወንጀለኛ፣ በቃህ ሊባል ይገባል!
የትግራይን ሕዝብ ስለእምነቱና ክብሩ የአዲስ አበባው ሲኖዶስም ሆነ በውስጡ የተሰገሰጉት እስከ ጦር ግንባር የዘመቱ፤ የጀኖሳይድ አቀንቃኝ ቀስቃሽና አዝማች ወንጀለኞች፤ ሊነግሩት ክህሎትም ሆነ የሞራል ብቃት የላቸውም::
እነጴጥሮስ ዳንኤል ክብረትና ግብረአበሮቻቸው ያዘመቱት የመሩት የባረኩት የጀኖሳይ ኣሕዛብ እኮ፤
▪ ክቡሩን የሰውን ልጅ እንደ እንሰሳ ያረዱ፣
▪ የሰውን ልጅ ጭንቅላት በእንጨት ላይ ሰክተው የፎከሩና በጀብድ ፎቶ የተነሱ ቪድዮ የተቀረፁ፣
▪ ትግራዋይ ከሚገዛን ሰይጣን ይግዛን ብለዉ በመስቀሉ ፊት የተገዘቱ፣
▪ የሰውን ልጅ ከእነ ህይወቱ በእሳት አጋይተው የገደሉ፣
▪ የሰውን ልጅ አካላት እየቆረጡ ቆዳ እየገፈፉ የገደሉ፣
▪ በርካታ ሺዎች የትግራይ ካህናትን ባህታውያን መነኮሳትን ሓጂዎችንና ሙላህዎችን እንደ እንሰሳ እያደኑ እያሳደዱ የገደሉ፣
▪ በመቶ ሺዎች የትግራይ እናቶችንና ልጃገረዶችን፣ መነኮሳት ደናግል፣ የቆረቡ ካህናት ሚስቶችን ሳይቀር እንደእንሰሳ እየተፈራረቁ የደፈሩና ያራከሱ፣
▪ ከዚህም በከፋ በሴት ልጅ ማሕፀን ውስጥ ከምስማር ቁርጥራጭ ብረት፣ ላስቲክና እንጨት አንስቶ፣ በርካታ ግዑዝ ነገር የከተቱ፣
▪ ተጋሩ ስለሆኑ ብቻ በርካታ ሺዎችን በገመድና በሽቦ የፊጥኝ እያሰሩ ነፍሰጡር እናቶችን ሳይቀር ወደ ጎርፍና ገደል እየወረወሩ የገደሉ ....
በአፈ ታሪክ እንኳን ተነግሮ ተሰምቶ የማያውቅ ከልክ ያለፈ ግፍ፤ ከአራዊትም የከፋ እጅግ አሰቃቂ አረመኔነት የፈፀሙ ናቸው!
እነዚያ እስከ አንድ ሚልየን የሚደርሱ በነጴጥሮስና መሰሎቻቸው አስተባባሪነትና አዝማችነት የተጨፈጨፉ የትግራይ ሰማእታት እኮ ገና በክብር አልተቀበሩም! እነጴጥሮስ ባርከው ያዘመቷቸው ፋኖዎዎችና ልዩ ሃይል አሁንም ድረስ በምዕራብና ደቡብ ትግራይ ሕዝቦችን እየገደሉ እያሰቃዩ እያፈናቀሉ እያሳደዱ ነው!
እናማ እነዚህ ኣረመኔ ኣሕዛብ እነጴጥሮስና መሰሎቹ የአዲስ አበባው ሲኖዶስ ተብየዎች ናቸው፤ እውነት የትግራይ የሃይማኖት አባቶችንና የትግራይን ሕዝብ ስለእምነቱና ስርዓተ ሃይማኖቱ ሊነግሩት የዳዳቸው! ሬድዋን ሑሴን እውነት ብሏቸዋል፤ «...የሚሉሽን በሰማሽ ገበያም ባልወጣሽ...»