Federal Police Commission

Federal Police Commission

Tikvah-Ethiopia

ባለቤቱንና ልጁን የገደለው ግለሰብ የሞት ውሳኔ ተላለፈበት።

በስልጤ ዞን በሳንኩራ ወረዳ አለም ገበያ ከተማ ልዩ ስሙ ጤና ተብሎ በሚጠራው አከባቢ የካቲት 13 ቀን 2012 ዓ/ም ከሌሊቱ 9፡00 ሰዓት የገዛ ባለቤቱንና የ4 ዓመት ልጁን በቤት ውስጥ እያሉ ቤት ላይ ቤንዝል አርከርክፎ ያቃጠለው ግለሰብ በሞት እንዲቀጣ ውሳኔ እንደተላለፈበት የስልጤ ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ፡፡

የስልጤ ዞን ፖሊስ አዛዥ ዋ/ኢ/ር ካሚል ሀምድ ስለወንጀል ድርጊቱ እንዳስታወቀው ተከሳሽ ይልማ ዱባለ የተባለው ግለሰብ ሟች ሀዲሪያ ሲራጅ የተባለችውን ባለቤቱን 12 ዓመት አረብ አገር ለፍታ ያመጣችውን ሀብት በስሜ አዙሪ በማለት የተጀመረው ጭቅጭቅ ውሎ እያደረ ሌላ አጀንዳ እያስከተለ በባልና ሚስት ያለውን ግንኙነት ይበልጥ እየከረረ ሲሄድ በስሜ ማዞር ያልፈለግሽው ንብረትሽን በጎን ሌላ ፍቅረኛ ስላለሽ ነው በማለት በመሀላቸው ያለውን ግንኙነት ወደ አደገኛ ደረጃ እንዲሸገር አድርገል፡፡ 

ተከሳሽ የገዛ ባለቤቱንና የልጁን የሚገልበትን ምቹ ሁኔታ አመቻችቶ የካቲት 13 ቀን 2012 ዓ/ም ቤንዝል ገዝቶ ወደ ቤት ሲመጣ ሟች ቤንዝሉን ለምን ገዛህው ብላ ስትጠይቀው ገዝቸው ሳይሆን ሞቴር ያለው ጓደኛ አስቀምጥልኝ ብሎኝ ነው ይላታል።

ቀኑ መሽቶ የ5 ወር ነፍሰ ጡር የሆነችው ባለቤቱ ሀገር አማን ነው ብላ የ4 ዓመት ህፃኑዋን በጉያዋ ታቅፋ በተናችበት በውድቅት ሌሊት ባሏ በቡና መውቀጫ ዘነዘና የተለያየ የሰውነት ክፍሏን ደጋግሞ በመምታት ህይወቷ እንዲያልፍ ካደረገ በኋላ ቤቱን ዘግቶ በህይወት የነበረችው የ4 ዓመት ህፃን በቤቱ እያለች በቤንዝል አርከፍክፎ ቤቱን እንዲቃጠል አድርጎ የእናትና የልጅ ህይወት እንዲያልፍ ካደረገ በኋላ ወደ ኦሮሚያ ክልል አጋሮ ከተማ ለጥቂት ወራት ተሰውሮ መኖር ይጀምራል፡፡  

የስልጤ ዞን ፖሊስ ተከሳሽ ይልማ ዱባለን ከተደበቀበት ኦሮሚያ ክልል አጋሮ ከተማ አድኖ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራውን ከዓቃቤ ህግ ጋር በመሆን ለስልጤ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ያቀርባል የክስ መዘዝገቡ የቀረበለት የስልጤ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ጉዳዩን በጥንቃቄ መመልከት ይጀምራል፡፡ 

የቀረበለት የክስ መዝገብ የተመለከተው ፍ/ቤት ግራና ቀኙን ተመልክቶ ተከሳሽን እንዲከላከል ቢጠይቀውም ተከሳሽ መከላከል ባለመቻሉ ለተፈፀመው ወንጀል ተከሳሽን ይመጥናል ሌሎችንም ያስጠነቅቃል በማለት የስልጤ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ታህሳስ 16 ቀን 2013 ዓ/ም በዋለው ችሎት በሞት እንዲቀጣ ወስኖበታል መረጃውን ያገኘነው ከስልጤ ዞን ፖሊስ መምሪያ ነው፡፡

(ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

Report Page