#FBC
በዩኒቨርሲቲዎች ሁከትና ብጥብጥ ጋር በተያያዘ 1,207 ሰዎች እርምጃ ተወስዶባቸዋል!
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፌሰር ሂሩት ወልደማርያም ዛሬ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ6 ወራት የስራ ሪፖርት አቅርበዋል።
- ከህዳር 30 ጀምሮ በዩኒቨርሲቲዎች ሁከቶች መቀስቀሳቸውን ተገልጿል። ለዚህ ምክንያት ተደርጎ የቀረበው ተዛባ የሚዲያዎች ዘገባ አንዱ ሆኖ ተጠቅሷል። ሚዲያዎች ግጭቱ የብሄር እና የሃይማኖት መልክ እንዲይዝ ሲሰሩ ነበር ተብሏል።
- ሌላው ለሁከቶች መቀስቀስ ምክንያት የመሰረተ ልማት አለመሟላት እንደ ዋነኛ ችግር ተጠቅሷል። ግጭቶች ሲፈጠሩ መንግስት በአፋጣኝ ደርሶ እርምጃዎችን እንዳይወስድ የመሰረተ ልማት ችግሮች በዋነኛነት ተጠቅሷል።
- የአካባቢ ፖለቲካ ሁኔታ ለግጭቶች መባባስ ከፍተኛ አስተዋፆ እንደነበረው ተገልጿል።
- የዩኒቨርሲቲ አመራር ድክመት፣ አስተዳደራዊ እርምጃ አለመውሰድ፣ ዝቅተኛ አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰድ፣ ተቀናጅቶ አለመስራት...ግጭቶች እንዲባባሱ እንዳደረገ ተገልጿል።
- ሚኒስቴሩ ችግሮችን ለመፍታት ከጠቅላይ ሚኒስትሩና ከ20 ዩኒቨርሲቲዎች ጋር ምክክር ካደረገ በኃላ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በግል አመራር እንዲሰጡበት መደረጉ ተገልጿል። በዚህም ዩኒቨርሲቲዎች በፌደራል ፖሊስ እንዲጠበቁ፣ የግቢ አጠባበቅ በቴክኖሎጂ እንዲደገፍ መመሪያ መተላለፉ ተገልጿል።
- 1,207 ግለሰቦች ላይ ከፍተኛ ቅጣት ተላልፏል። 921 ተማሪዎች የተለያዩ ቅጣቶች ተወስኖባቸዋል ተብሏል።
- 421 ተማሪዎች ከ1 ዓመት አንስቶ ሙሉ በሙሉ እስከ ማባረር እርምጃ ተወስዷል።
- 140 ተማሪዎች እና መምህራን የተለያየ ቅጣት ተላልፎባቸዋል፤ ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ እንደሚገኝ ተገልጿል።
- የተዛባ መረጃ ሲያስተላልፉ የነበሩ ሚዲያዎች ለብሮድካስቲንግ ባለስልጣን ስማቸውን በመጥቀስ ያቀረቡትን መረጃም በመገምገም ለባለስልጣኑ እርምጃ እንዲወሰድባቸው ሚኒስቴሩ ማስተላለፉን ገልጿል።
[ፋና ብሮድካሲንግ፣ ብስራት መለሰ]
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot