#EthioFM

#EthioFM


የኮሮና ወረርሽኝን የሚያቆም መድሀኒት መገኘቱን የቻይና ሳንቲስቶች ተናግረዋል። ወረርሽኙን ክትባት ያቆመዋል ተብሎ ይገመት ነበር የሚሉት የቻይና ላብራቶሪ ተመራማሪዎች የኮሮናን ስርጭት በፍጥነት የማቆም ሀይል ያለው መድሀኒት እያዘጋጀን ነው ብለዋል፡፡ 

በአንጋፋው የፔኪንግ ዩኒቨርሲቲ የሚገኙ አጥኚዎች እንደሚሉት ይሄ መድሀኒት የተጠቂዎችን ማገገሚያ ጊዜ ማሳጠር ብቻ ሳይሆን ለተወሰነ ጊዜ ከቫይረሱ ሙሉ በሙሉ ነፃ ያደርጋል ብለዋል፡፡ 

ይሄ መድሀኒት በእንስሳት ደረጃ ተሞክሮ ስኬታማ ሆኗል ብለዋል በቤጂንግ ዩኒቨርሲቲ የጄኖሚክስ መዕከል የኢኖቬሽን ዳይሬክተር ሱኔይ ዚ፡፡

ከ60 ከኮሮና ካገገሙ ሰዎች ላይ ኢምዩኒቲ (ከሰውነታቸው በሽታ የመከላከል አቅም) ላይ በመውሰድ ተዘጋጅቷል ነው የተባለው መድሀኒቱ፡፡ 

ካገገሙ ሰዎች ላይ የተዘጋጀው ይሄ መድሀኒት ለበሽታው መድሀኒት ሊሆን እንደሚችል እርግጠኛ እየሆንን ነው፤ የማገገሚያ ጊዜውም ከዚህ ወዲያ ያጥራል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ እንደ ሱኔይ ዚ መድሀኒቱ በዚህ አመት ይደርሳል መባሉን AFP ዘግቧል።

ምንጭ፦ ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 (በሔኖክ አስራት)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

Report Page