Ethio China

Ethio China


ቻይና በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ለመግባት የሚደረገውን ሙከራ ተቸች።

የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ይ ከኢትዮጵያ ምክትል ጠ/ሚ እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ውይይት አድርገዋል።

የውጭ ጣልቃ ገብነትን በተመለከተ ፦

በዚህ ውይይት አቶ ደመቀ ፥ መንግስት የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለሚያነሳቸው ጥያቄዎች በተለይ የሰብዓዊ መብት ጥሰት የፈፀሙ አካላትን ለህግ እንዲቀርቡ፣ የሰብዓዊ ጥሰቶችን በተመለከ ገለልተኛ ምርመራ እንዲካሄድ እንዲሁም የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት ተደራሽነት እንዲሰፋ መንግስት ተገቢ ምላሽ እየሰጠ ቢሆንም መሰረተ በመንግስት ላይ የሚሰነዘሩ መሰረተ ቢስ ትችቶች መቀጠላቸውን ለቻይናው አቻቸው አብራርተዋል።

 አክለውም ቻይና የኢትዮጵያ መንግስት ያደረጋቸውን ጥረቶች እንደምትገነዘብ ያላቸውን እምነት አንስተዋል። 

ዋንግ ይ መንግስት በትግራይ ክልል የሚያደርጋቸውን ጥረቶችን ማድነቃቸው ተነግሯል። በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ለመግባት የሚደረገውንም ሙከራ ተችተዋል። 

አያይዘውም ቻይና በምትከተለው በአገራት የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ያለመግባት መርህ መሆኑን ጠቅሰው፣ አገራት የራሳቸውን ጉዳይ በራሳቸው የመፍታት ልዑላዊ መብት ያላቸው መሆኑን ገልፀዋል። 

የትታላቁ ህዳሴ ግድብ ፦

በሌላ በኩል በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በተመለከተ በተደረገው ውይይት አቶ ደመቀ በአፍሪካ ህብረት አስተባባሪነት በሚደረገው የሶስትዮሽ ድርድር እልባት እንደሚያገኝ ኢትዮጵያ እምነት ያላት መሆኑን ገልፀዋል።

ዋንግ ይ በበኩላቸው ጉዳዩ ዘላቂ መፍትሔ እንዲያገኝ አገራቸው ድጋፍ የምታደርግ መሆኑን ገልፀዋል። 

የኢትዮ-ሱዳን ድንበር ጉዳይ ፦

በሁለቱ ሚኒስትሮች ውይይት የኢትዮ ሱዳን የድንበር ጉዳይ ተነስቶ ነበር።

አቶ ደመቀ የኢትዮ-ሱዳን ድንበር ጉዳይን በተመለከተ ዝርዝር ማብራሪያ ሰጥተዋል። ዋንግ ይ በበኩላቸው ቻይና የሁለቱን አገራት ወዳጅ እንደመሆኗ መጠን ውዝግቡ በሰላማዊ መንገድ መፍትሄ እንዲያገኝ ጥረት እንደምታደርግ ገልፀዋል። 

ምርጫ 2013 ፦

አቶ ደመቀ ኢትዮጵያ የምታካሂደው መጪው አገራዊ ምርጫ ነፃ፣ ገለልተኛና ሰላማዊ ሆኖ እንዲካሄድ የተከናወኑ ስራዎችን በተመለከተ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን ክቡር ሚስተር ይም ምርጫው በስኬት እንደሚጠናቀቅ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

የኮቪድ-19 ወረሽኝ ጉዳይ ፦

አቶ ደመቀ አክለውም ኢትዮጵያ የኮቪድ -19 ወረርሽኝን ለመከላከል በምታደርገው ጥረት በቻይና በኩል ለተደረገው ድጋፍ ምስጋናቸውን ገልፀው፣ የኮቪድ -19 ክትባት በአገር ውስጥ ለማምረት እንዲቻል ቻይና ድጋፍ እንድታደርግ ጠይቀዋል። 

ዋንግ ይ በበኩላቸው ኢትዮጵያ ክትባቱን ለማምረት እንድትችል መንግስታቸው የአገራቸው ኩባንያዎች ተሳታፊ እንዲሆኑ የሚያበረታታ መሆኑን ገልጸዋል። 

(የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር)

Report Page