Engineering department

Engineering department

𓄂‌Tesfa

👌 Engineering በውስጡ እጅግ በጣም በርካታ የ Engineering አይነቶችን የያዘ የ Science ወይም technology ዘርፍ ነው።  


📌 Electrical and Computer Engineering


🙌 ይህ department የ Electrical engineering እና computer engineering ቅይጥ ነው። ስለዚህ


ወደዚህ Department መግባት የምትፈልጉ ልጆች ከ እናንተ ምን ይጠበቃል🤔??


🔰 Applied maths ትምህርት ላይ ጎበዝ መሆን ይጠበቅባችሗል። Applied maths I , Applied maths II , Applied maths III ትማራላችሁ። እነዚህን ኮርሶች ስትማሩ Integration, Laplace transformer , Ordinary Differential Equation የመሳሰሉትን ገብቷችሁ ተማሩ ምክንያቱም ከ እናንተ ጋር አብረው የሚቀጥሉ ህጎች ናቸው። በቃ ፈለጣ ላይ ጎበዝ መሆን አለባችሁ። ደግሞ የ Electrical ተማሪ ፈለጣ ላይ አይታማም🙈።


🔰 የ Electrical part ቶች ላይ ጎበዝ መሆን ይጠበቅባችሗል። ስለ circuit(electronics) , resistor, diode, gate, capacitor... የ 10 ኛ እና 12 ኛ ክፍል Physics ትምህርት ላይ ተምራችሁታል። ግቢም ላይ እነዚህን ትምህርቶች ሰፋ ብለው ትማሩታላችሁ። የ 12 ኛ ክፍል Physics መፅሀፍ በ pdf ያዙት circuit ትምህርት ላይ ያግዛችሗል። እኔ የምመክራችሁ ውጤት ለመስራት ብላችሁ theory ላይ ብቻ ትኩረት አታድርጉ። ተግባራዊ ትምህርቱን ከ theory ጋር አጣምራችሁ ተረዱት። ተግባሩን ካወቃችሁት ስራ በማጣት አትቸገሩም።


📳 የራሳችሁን ጥገና ቤት፡ ኤሌክትሮኒክስ ቤት መክፈት ትችላላችሁ።


🏦 ለተለያዩ ህንፃዎች Installation መስራት ትችላላችሁ ። በዛ ላይ ጨላው ራሱ😋።


✈️ አየር መንገድ መስራት ትችላላችሁ።


⛽️ የ ሀይል ማመንጫ ጣቢያዎች (power station) ላይ መቀጠር ትችላላችሁ።


🛸 መብራት ሀይል እና ቴሌ ተቀጥራችሁ መስራት ትችላላችሁ። ወዘተ


🔰 Programming Language ላይ ጎበዝ ወይም ሞካሪ መሆን ይጠበቅባችሗል።


😘 C++ , Java , Python የመሳሰሉትን የ programming or code ትምህርቶችን ትማራላችሁ። በጣም ልመክራችሁ የምፈልገው ነገር የ programming ትምህርት እጅግ በጣም በጣም ደስ የሚል ትምህርት ነው ፡ ከ computer ጋ ማውራት ነው። computer ሩን እንዲህ እንዲህ አድርግልኝ ብለህ በአግባቡ ታዘዋለህ/ሽ ፡ እሱም ታዛዥ ነው የ ልብህን/ሽን ያደርግልሀል/ሻል😁። የ programming ትምህርት ከ መምህር ብቻ አትጠብቁ ፡ Google እያደረጋችሁ አንቡብ። በ አማርኛ እያስረዳ የሚያስተምር video አለ ፡ እሱን ከ Google download አድርጋችሁ ወይም ደግሞ ከ senior ተማሪዎች ተቀብላችሁ በደንብ እዩት፡ ያግዛችሗል። 


👷‍♂️ Programming ላይ ጎበዝ ከሆናችሁ የተለያዩ ድርድቶች ላይ በቀላሉ ትቀጠራላች።NASA መግባት ትችላላችሁ።


👷‍♀️ programming ላይ ጎበዝ ከሆናችሁ የራሳችሁን software አበልፅጋችሁ ራሳችሁንም ሀገራችሁንም መጥቀም ትችላላችሁ። 🙏🙏 ደጋግሜ የምነግራችሁ ነገር የ programming language ትምህርት እጅግ በጣም በጣም ደስ የሚል የ ተግባር ትምህርት ስለሆነ ጊዜ ሰጥታችሁ አንብቡት ተረዱት በጣም ትወዱታላችሁ ፡ ለዚች ሀገር የ ቴክኖሎጂ ዕድገትም ተስፋ ትሆናላችሁ። 


✅ Electrical and Computer engineering መግባት የምትፈልጉ ልጆች ከ 3 ኛ አመት በሗላ Stream ትመርጣላችሁ። 👇👇


👷‍♀️ power  

👷‍♀️Installation

👷‍♀️Communication 

👷‍♀️ Computer


👆 ከ እነዚህ አንዱን የፈለጋችሁትን stream መርጣችሁ specialize ታደርጋላችሁ። ውጤት ቢኖራችሁ አሪፍ ነው ወደ ምትፈልጉት stream ለመግባት።

📌 Mechanical and Chemical Engineering


😁 Mechanical Engineering እና Chemical Engineering የ አንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች ናቸው። ስለዚህ ወደ እነዚህ ዲፓርትመንት የምትገቡ ልጆች የምትወስዷቸው ኮርሶች በብዛት ተመሳሳይ ስለሆኑ ህብረት ፍጠሩ☺️። እስኪ ለየብቻ እንያቸው🤔።


 📌Mechanical Engineering

 

🚸 ወደዚህ ዲፓርትመንት የምትገቡ ልጆች ከእናንተ ምን ይጠበቃል🤔?


Mechanical Engineering በዋናነት ስራው የተለያዩ መሳሪያዎችን Design, Develop, operate and manufacture ማድረግ ነው።


እነዚህ መሳሪያዎች ምንድን ናቸው🤔 ?


🚘🚄 የመኪና ሞተር እና ሌሎች ሞተር

🆒 ፍሪጅ

🚨 የ ተለያዩ turbines

☢️ Air conditioner 

🚹 ሊፍት እና ሌሎችም።


እነዚህ መሳሪያዎች Design ለማድረግ የተለያዩ parameters ትማራላችሁ። Design ካደረጋችሁ በሗላ develop ታደርጋላችሁ። ይኸን ለማድረግ ደግሞ 


👨‍🔧 Mechanics

👩‍🏭 Dynamics

👨‍🔧 Thermodynamics 

👩‍🏭 Structural Analysis

👨‍🔧 Material 

 

ትማራላችሁ። ስለዚህ👆👆 እነዚህን ትምህርቶች ላይ deep understanding ሊኖራችሁ ይገባል። ፈለጣ ይበዛባቸዋል ፡ ስለዚህ ፈለጣ ላይም ጎበዝ ሁኑ። እኔ ግን የምመክራችሁ ሳይንሱን እወቁት። ኸረ Google አድርጉ🙈 ብዙ ነገር ታገኛላችሁ።


እሺ design and develop ካደረጋችሁ በሗላ operate ታደርጋላችሁ። ራሳችሁ የሰራችሁትን መሳሪያ ራሳችሁ ታንቀሳቅሱታላችሁ ትጠግኑታላችሁ። ስለዚህ 


 🛫Airport

🚕Automotive

 🛳Shipment

🏘 Building

🚈Railway


እና ሌሎችም ጋ ተቀጥራችሁ መስራት ትችላላችሁ ።።።


Share 👇👇👇👇

https://t.me/HU_University


https://t.me/HU_University

Report Page