Eng water work kenbata24

Eng water work kenbata24


በድጋሚ የወጣ ግልጽ
ጨረታ ማስታወቂያ

በከምባታ ጠምባሮ ዞን ዶዮጋና ወረዳ ጤ/ጥ/ጽ/ቤት በ04/06 2012 ዓም በቁጥር ዶወ/34/076/77 ለሠራራ ጤና ጣቢያ ውሃ ለማስገባት ጨረታ እንድናወጣ በተፃፈልን ደብዳቤ መሠረት የዶዮገና ወረዳ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት የውሃ መሥመር ዝርጋታ ሥራን ከዚህ በታች የተገለጹትን መመዘኛዎችን የሚያሟሉ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

በዘርፉ ህጋዊ የሥራ ፍቃድ ያለው፤ የዘመኑን ግብር የከፈለ እና
የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያለው፧
ተጫራቹ የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለበት ፤
የምዝገባ ምስክር ወረቀት እና የግብር ከፋዮች መለያ ቁጥር /Tin number/ ያላቸው፣
የመወዳደሪያ ሂሳብ በአንድ ኦሪጅናልና በአንድ ኮፒ ሆኖ በታሸገ ኤንቨሎፕ የሚያቀርብ መሆን አለበት፣
ተጫራቾች ጠቅላላ ዋጋውን በቁጥርና በፊደል መጻፍ አለባቸው ፣

ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO 10,000 ብር/ አስር ሺህ ብር ብቻ ወይም በጥሬ ገንዘብ ከጨረታ ሠነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ አለባቸው፡፡የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው ከተከፈተ ጊዜ አንስቶ ለ20 ቀናት ብቻ ይሆናል፣
ተጫራቾች በእያንዳንዱ ገጽ ላይ ፊርማ እና የድርጅቱን ማህተም ማስፈር ይገባቸዋል፣
ተጫራቾች የሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ቫትን የሚያካትትና የማያካትት መሆኑን መግለጽ አለባቸው፡፡ታክስ በትክክል ካልተገለጸ የቀረበው ዋጋ ቫት እንደተካተተ ተቆጥሮ ውድድሩ ይካሄዳል፣
ማንኛውም ተጫራች የጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት በፊትም በኋላም የዋጋ ማቅረቢያው ሰነድ/የመወዳደሪያ ሂሳብ/ ማስገባት የለበትም፣
ተጫራቾች ደረጃ ስድስት/6/እና ከዚያ በታች በ WWC ግንባታ ሥራ ዘርፍ ለተሰማሩ ብቻ ይሆናል፣
የጨረታ ሰነድ ግዥ ብር 200/ ሁለት መቶ ብር ብ ቻ ለገቢዎች ጽ/ቤት ገቢ በማድረግ ከዶ/ወ/ግ/ፋ/ን/አስ/ር ሥራ ሂደት መግዛት ይችላሉ፣

ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10/ ለአስር ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ከዋለ በኋላ በ11 ኛ ቀን ወይም 11 ኛ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን 4 ፡30 በዶ/ ወ/ ፋ/ ኢ/ ል/ ጽ/ ቤት ቢሮ ቁ4 ላይ ሳጥኑ ታሽጎ ወዲያውኑ ተጫራቾች/ ሕጋዊ ወኪሎች/ በተገኙበት ጨረታው የሚከፈት ይሆናል፡

ተጫራቹ በውሃ ሥራ የ2011 በጀት ዓመትና በ2012 በጀት ዓመት ቢያንስ አንድ ጊዜ መልካም ሥራ አፈጻጸም ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡

***ማሳሰቢያ:- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው:: ***

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0913189122፤0910118455

በከምባታ ጠምባሮ ዞን

ዶዮጋና ወረዳ ጤ / ጥ / ጽ / ቤት



Posted: አዲስ ዘመን ግንቦት 20 ቀን 2012

Deadline: June 6, 2020


© walia tender

Report Page