Eng wag 46

Eng wag 46


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በዋግ ኽምራ ዞን የፃግብጅ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት የግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት ለፃ/ወ/ጤና ጽ/ቤት በ2012 ዓ/ም በክልል ጤና ቢሮ በጀት የጣራ ውሃ ማሰባሰብ ግንባታ በግልጽ ጨረታ እንዲወጣላቸው በቁጥር ፃ/ወ/ጤ/01202/012 በ26/08/2012 ዓ.ም በጠየቁት መሰረት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ የግንባታ ባለሙያዎች አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።

የቢሮ ግንባታ ፍቃድ ያላቸው ወይም የህንጻ ግንባታ ስራ ደረጃ 9 እና ከዛ በላይ ማቅረብ የሚችል።
የ2012 ዓ/ም የታደሰ የሙያ ፍቃድ ያለው ት/
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከፃ/ወ/ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት በመገኘት መረጃችሁን ዋናውን እና የማይመለስ ፎቶ ኮፒ በመያዝ ከ 09/09/2012 እስከ 29/09/2012 ዓ.ም ድረስ በስራ ሰዓት መውሰድ ይችላሉ።
የዋጋ ማቅረቢያ ሰነዳቸውን ዋናውን እና ፎቶ ኮፒውን በመለየት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ አለባቸው።
ተጫራቾች ከጠቅላላ የጨረታ ዋጋ ላይ 1% ፣ ፕርሰንት የጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ ወይም በመሂ 1 ገቢ አድርገው ማቅረብ አለባቸው ።
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን እስከ 30/09/2012 ከጠዋቱ 4 ፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው።
ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾቹን ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 30/09/2012 ዓ. ም ከጠዋቱ 4:30 በፃ/ገ/ኢ/ት/ጽ/ ቤት ይከፈታል።
ተጫራቹ እራሱ ጨረታውን አሸንፎ ራሱ መስራት የሚችል እንጂ አሳልፎ ለሌላ ወገን የማይሰጥ መሆን አለበት።
ስርዝ፣ ድልዝ ወይም ስእርሳስ፣ በቀይ እስክርቢቶ፣ እና በተለያዩ ቀለም ባላቸው እስክርቢቶዎች እና ቀለሞች የተጻፈ እና የማይነበብ አጠራጣሪ የሆኑ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም እንዲሁም ካስገባሁት ዋጋ ይህን ያህል ፐርሰንት ቀንሼ ወይንም ጨምሬ እሰራለሁ ማለት ተቀባይነት አይኖረውም።
በፖስታው እና በሰነዱ ላይ የድርጅቱ የማህተምእና የተወዳዳሪው ስም፣ ፊርማ እና ቀን ካላረፈበት ተቀባይነት አይኖረውም።
የጨረታ ሰነድ የመሸጫ ዋጋ 200 ብር ሲሆን ሰነዱንም በፃ/ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 ላይ መውሰድ ይችላሉ ::
መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ከነቫቱና ከቫቱ ውጭ የሚለውን ለይተው መፃፍ አለባቸው።
ከአሸነፉ በኋላ ያሸነፉበትን የብር መጠን 10% ማስያዝ የሚችሉ መሆን አለበት።
አሸናፊው ያሸነፈበትን ዋጋ ከ200,000 ብር በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለበት ።
ለበለጠ መረጃ ፃግብጅ ወረዳ ጤና ጽ/ ቤት ዘወትር በስራ ሰዓት በአካል ቀርበው ማነጋገር ይቻላል

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በዋግ ኽምራ ዞን የፃግብጅ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ ቤት



Posted:አዲስ ዘመን ግንቦት 10 ቀን 2012
Deadline: June 7, 2020


© walia tender

Report Page