Eng mech other19

የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር IBDB/PWEM/10/12
የሶማሌ ከልል መስኖ እና ተፋሰስ ልማት ቢሮ ለሦስት የውሃ ጉድጎድ የኤሌክትሮ መካኒካል ግዥ ሥራን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ እና ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ በጨረታው እንድትወዳደሩ ተጋብዛችኋል፡፡
ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ እና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን የ ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ የተረጋገጠ ቼክ ( ሲፒ ኦ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 የሥራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ጅጅጋ ከሚገኘው የሶማሌ ክልል መስኖ እና ተፋሰስ ልማት ቢሮ በመገኘት የሥራውን ዝርዝርና የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 ( አምስት መቶ) በመክፈል ሙግዛት ይቻላል፡፡
በጨረታው መሳተፍ የሚችሉት ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ ሥራ ላይ የሠሩ መሆን ይኖርባቸዋል። ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣበት በስምንተኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4 ፡00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዕለቱ ከጠዋቱ 4 ፡30 መስሪያ ቤቱ በሚገኝበት ጅጅጋ ይከፈታል፡፡
መስሪያ ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- +251257753595/96
ፋክስ ቁጥር፡- +251257753598
ጅጅጋ ሶማሌ ክልል
የሶማሌ ክልል መስኖ እና ተፋሰስ ልማት ቢሮ
Posted: አዲስ ዘመን ግንቦት 05 ቀን 2012
Deadline: May 22, 2020
© walia tender