Eng mec

Eng mec


የጨረታ ማስታወቂያ

በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይ/ኢኮ/ልማት መምሪያ በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋ/ኢ/ል/መምሪያ ለሀዋሳ ከተማ አሰተዳደር ከተማ ልማትና ኮን/ መምሪያ በቱላ ክ/ከተማ የመንገድ መብራት (street light) ዝርጋታ ሥራን በዘርፉ ህጋዊ ፈቃድ ካላቸው መካከል በጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፤፤

በዚህ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተቋራጮች መወዳደር ይችላሉ:

በኤሌክትሮ ሜካኒካል ዘርፍ የተሠማሩ ደረጃ BC-5 GC-5 እና ከዚያ በላይ ያላቸው።
በሥራ መስኩ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ፣
የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፣
ተጫራቾች የጨረታ ማስከ በሪያ 100,000 ( አንድ መቶ ሺ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ( የተመሰከረ) ሲፒ ኦ (CPO) ወይም ቢድ ቦንድ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አሰበት::
የጨረታ ሰነዱ ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይ/ኢኮ/ልማት መምሪያ አንደኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 2 በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 /ለሃያ አንድ/ ተከታታይ ቀናት ብር 200 ( ሁለት መቶ ብር) በመከፈል መግዛት ይችላሉ።
ጨረታ ሰነዱ በሰም ለየብቻቸው በታሸገ ኤንቨሎፕ አንድ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ ፋይናንሻል በመያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሥራ ቀናት ሥራ ሰዓት በመጠቀም ጨረታውን በፋይ/ኢኮ/ልማት መምሪያ ቢሮ ቁጥር 10 (ግዢ ኬዝ ቲም) ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
ጨረታው በ21 ሃያ አንደኛው ተከታታይ ቀናት ከቀኑ 8 ፡00 ሰዓት ታሽጎ በ8:30 ሰዓት ተጫራ ቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሆነ ባልተገኙበት በቢሮ ቁጥር 10 ይከፈታል። ይህ ቀን ቅዳሜ ወይም እሁድ እንዲሁም የበዓል ቀን ከሆነ ደግሞ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል።
በጨረታ አከፋፈት ስነ-ስርዓት የተነበበው ዋጋ እና በአርትሜቲክ ቼክ በሚደረግበት ጊዜ በሁለቱ መካከል 2% በላይ ሆነ በታች ከሆነ ቀጥታ ከጨረታ ውጪ ይደረጋል።
በጨረታው ላይ ያለው ጠቅላላ ዋጋ ከመሀንዲስ ግምት (ከወቅቱ የገበያ ዋጋ ስፐርሰንት (15%) በላይ ከሆነ ቀጥታ ከጨረታ ውጪ ይደረጋል።
መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ

ስልክ ቁፕር 046-212-13-34

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይ/ ኢኮ/ ልማት መምሪያ

ሀዋሳ



Posted: አዲስ ዘመን ሚያዝያ 29 ቀን 2012
Deadline: May 27, 2020


© walia tender

Report Page