Eng com buil chemical cloth

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር WSSF/LP/006/2020
ስኳር ኮርፖሬሽን (የወንጂ/ሸዋ ስኳር ፋብሪካ) ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልፅ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው ተጫራቾች ጨረታውን ለመግዛት የታደሰ ንግድ ፍቃድ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ እና የአቅራቢዎች የምዝገባ ሰርተፍኬት በማቅረብ እና የማይመለስ 200 ብር በመክፈል ከላይ ለተጠቀሱት እቃዎች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከዚህ በታች ከተገለጸው አድራሻ በመግዛት በጨረታው መወዳደር ይችላሉ፡፡
ወንጂ/ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ያግዢ ቡድን
ሜክሲኮፊሊፕስ ህንፃ3 ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 301
ለተጨማሪ መረጃ 0115585229/0115516082
ፋክስ ቁጥር 0115516608
2. ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ሰነድ ጋር የታደሰ ንግድ ፍቃድ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ምዝገባ ሰርተፍኬት፤ የግብር ከፋይነት የምስክር ወረቀት፤ የአቅራቢዎች የምዝገባ ሰርተፍኬት እና ለጨረታ ማስከበሪያ በጨረታ ሰነድ ውስጥ የተጠቀሰውን የገንዘብ መጠን በሲ.ፒኦ በማድረግ ማቅረብ አለባቸው፡፡
3 ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ሰነድ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ለመጀመሪያ ጊዜ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉ 30 ተከታታይ ቀናት ከጠዋቱ 4 ፡00 ሰዓት ከመሆኑ በፊት ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
4 ጨረታው በተመሳሳይ ቀን ከጠዋቱ 4 ፡30 ሰዓት ላይ ከላይ በተገለጸው አድራሻ ቢሮ ቁጥር 305 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚሆን ሲሆን ትከክለኛው ቀን በጨረታ ሰነዱ ውስጥ የሚጠቀስ ይሆናል፡፡
5. ወንጂ/ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስኳር ኮርፖሬሽን
( ወንጂ/ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ)
Posted: አዲስ ዘመን ሚያዝያ 29 ቀን 2012
Deadline: June 5, 2020
© walia tender