Eng bui

የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር DCE/SF/71/2020
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለኢንሳ ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውሉ Supply, Install and Test of Stand By Generator ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም፡
ተጫራቾች ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘኑን ግብር የከፈሉ እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
ተጫራቾች ለጨረግተ ማስከበሪያ ዋስትና የሚያቀርቡት የገንዘብ መጠን በተጫራቾች መመሪያ ተራ ቁጥር 7.3 እና 7.4 በተጠቀሰው መሠረት መሆን አለበት።
ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 ( ሁለት መቶ) በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ወሎ ሰፈር አካባቢ በሚገኘው የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ዋና መ/ቤት የምሕንድስና ዕቃ ግዥ ኬዝ ቲም ቢሮ መግዛት ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች ናሙና እስከ ጨረታው መክፈቻ ሰዓት ድረስ ብቻ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
ተጫራቾች በጨረታው ለተጠቀሰው ዝርዝር ሥራ በሙሉ ዋጋ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ ግንቦት 18 ቀን 2012 ዓ. ም. ከጠዋቱ 4 ፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
ጨረታው ግንቦት 18 ቀን 2012 ዓ. ም. ከጠዋቱ 4 ፡15 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።
ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
አድራሻ፡- የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የቀጥታ መስመር ቁጥር 0114-40-34-34 ማዞሪያ 0114-42-22-70/71/72 ፖ. ሳ. ቁ 3414 ፋክስ ቁ. 0114-40-04-71/0114-42-07-46
ወሎ ሰፈር የቀድሞው ኖሬሳ ግቢ ድህረ ገፅ:- WWW.dce.gov.com/www.dce.et.com ኢሜል INFO @dce-et.com
Posted: ሪፖርተርግንቦት 02 ቀን 2012
Deadline: May 26, 2020
© walia tender