Eng bishoftu mec2

Eng bishoftu mec2


በድጋሚ የ ወጡ የጨረታ ማስታወቂያ

የቢሾፍቱ ከተማ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ትብብር በግልጽ ጨረታ ህጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ የመንገድ መብራት “SOLAR STREET LIDHT MAINTENANCE” በኤሌክትሮ መካኒካል ኢንጂነሪግ ደረጃ - 5 እና ከዚያ በላይ ያላቸው ላይ እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡፡

ተጫራቾች በዘርፉ ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው::
የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀንና ሰዓት የማይመለስ ብር 300 ( ሶስት መቶ ብር) ኦሮሚያ ሕብረት ሥራ ባንክ በባንክ ሒሳብ ቁጥር 071 በቢሾፍቱ ከተማ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ትብብር ስም በማስገባት የገቢ ደረሰኙን ከቢሾፍቱ ከተማ ገቢዎች ባለስልጣን በመቁረጥ ከቢሾፍቱ ከተማ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር የግዥና ንብረት የሥራ ሂደት 2ኛ ፎቅ አስፈላጊውን መረጃ ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ በመያዝ እስከ 27/09/2012 ዓም 8፡00 ሰዓት ብቻ መግዛት ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች በጨረታው ለመወዳደር የጨረታ ማስከበሪያ (BID BOND) ለመንገድ መብራት “traffic light” ብር 50000 ( ሃምሳ ሺህ) በባንክ በተረጋገጠ (CPO) ወይም ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (unconditional bank guaranty) በመጫረቻ ሰነድ ላይ በሚጠየቀው መሰረት ማቅረብ አለበት፡፡
ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዱን በመጫረቻ ሰነድ ላይ በሚጠየቀው መሰረት በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ በኤንቨሎፕ ላይ የተጫራቹን ስምና አድራሻ ሰነዱ ኦርጅናል ወይም ኮፒ መሆኑን በመጻፍ ከጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት በፊት በቢሾፍቱ ከተማ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር የግዥና ንብረት የሥራ ሂደት 2ኛ ፎቅ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
ጨረታው የሚከፈተው በ27/09/202 ዓም ከሰዓት በኋላ በ8 ፡00 ሰዓት ተዘግቶ ወዲያውኑ በ8:30 ሰዓት በቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር መሰብሰቢያ አድራሽ ይሆናል፡፡
መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙለ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ በአካል ቀርበው ወይም በስልክ ቁጥር 0114 30 17 58 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

ቢሾፍቱ ከተማ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር




Posted: አዲስ ዘመን ግንቦት 08 ቀን 2012

Deadline: June 4, 2020


© walia tender

Report Page