Elfor sale other 27

Elfor sale other 27


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

ኤልፎራ አግሮ ኢንዱሰትሪ ኃ/የተ/የግ/ማኅበር በስሩ ለሚገኙት ቢሾፍቱ ዶሮ ልማት እና ቢሾፍቱ ቄራ የሚያገለግሉ ከዚህ በታች ከተራ ቁጥር 1 እስከ 4 የተጠቀሱትን ግብዓቶችን በራሳቸው ትራንስፖርት ማቅረብ የሚችሉ ልምድና ብቃት ያላቸውን አቅራቢዎች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ቁጥር አንድ፡የቁመና ክብደታቸውም ከ18-25 ኪሎ ግራም የሚመዝኑ በሳምንት አቅርቦታቸው በቁጥር 127 የቆላ ፍየሎች ጠነ ላላ ብዛት በቁጥር 6,905 ቢሾፍቱ ኤልፎራ ኤክስፖርት ቄራ ድረስ፡፡
ቁጥር ሁስት፡ሙሉ የስጋ ይዘት ያላቸው፣ ያልከሱና በቆዳቸው ላይ ጉዳት (ጠባሳ) የሌለባቸው ሆነው የቁመና ክብደታቸውም ከ250 ኪሎ ግራም በላይ የሚመዝኑ፤ በሳምንት አቅርቦት በቁጥር እስከ 4 የሚደርሱ የዳልጋ ከብቶችን ጠቅላላ ብዛት በቁጥር 1,580 ቢሾፍቱ ኤክስፖርት ቁራ ፋብሪካ ድረስ ማቅረብ የሚችሉትን ተወዳዳሪዎች በመጋበዝ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ቁጥር ሶስት፡የቁመና ክብደታቸውም ከ19-30 ኪሎ ግራም የሚመዝኑ በሳምንት አቅርቦታቸው በቁጥር 44 የሆኑ በጎች ( ዋንኬ ያልሆነ) ጠቅላላ ብዛት በቁጥር 19905 ቢሾፍቱ ኤልፎራ ኤክስፖርት ቄራ ድረስ፡፡
ቁጥር አራት፡ያጥሬ ዕቃው ዓይነት ብዛት በኩንታል
1. በቆሎ -----------------7,783
2. ፍሩሽካ-----------------2,113
3. ኑግ ኬክ -------------1,644
4 ሶያቢን ኬክ ------------1,496
5. ጨው-----------------58
ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ አቅራቢ ድርጅቶች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

ተጫራቾች የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚመለስ ብር ለእያንዳዳቸው 100,000 ( አንድ መቶ ሺህ ብር) በሲፒኦ ወይም በካሽ ማስያዝ ይጠበቅ ባቸዋል፡፡
ጨረታውን ያሸነፈው ድርጅት ለመልካም ስራ አፈጻጸም ዋስትና ጠቅላላ ካሸነፈው አቅርቦት ክፍያ ብር ላይ 10% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ተጫራቾች በዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱ ላይ በተዘረዘረው እና በተያያዘው የአቅርቦትና የጥራት መሥፈርት መሠረት መጫረት ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱን አዲስ አበባ ላም በረት አካባቢ ከሚገኘው የድርጅቱ ፋይናንስ ክፍል በስራ ሰዓት ከግንቦት 11 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሰኔ 1 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ የሚጫረቱበትን የመጫረቻ ሰነድ ለእያንዳን ዱ የማይመለስ ብር 100.00 ( አንድ መቶ ብር) በመግዛት ላምበረት በሚገኘው አዲሱ የኤልፎራ ህንጻ ሶስተኛ ፎቅ በመቅረብ ቅጹ በሚፈቅደው መሠረት ዋጋ ሞልተው በማቅረብ እስከ ሰኔ 1 ቀን 2012 ዓ.ም ከረፋዱ 400 ሰዓት በሚዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ሰነዳቸውን ያስገባሉ፡፡
የጨረታው ሰነድ የተቀመጠበት ሳጥን ሰኔ 1 ቀን 2012 ዓ. ም ዓ. ም ከጠዋቱ 4 ፡00 ሰዓት ታሽጐ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4 ፡30 ሰዓት ላምበረት በሚገኘው አዲሱ የኤልፎራ ህንጻ ሶስተኛ ፎቅ በሚገኘው የምስራቅ ሪጅን ዋና መስሪያ ቤት ይከፈትና ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይካሄዳል፡፡
አቅርቦት መጠንን በተመለከተ እንደሁኔታው መጠኑ ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፡፡
የክፍያው ሁኔታ አቅርቦቱ ከቀረበ ከ45 ቀን በኋላ፡፡
ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በክፈል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር +251 11 515 96 88 /+251 11 515 96 84 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡

ኤልፎራ አግሮ ኢንዱስትሪ ኃ/ የተ/ የግ/ ማ



Posted: አዲስ ዘመን ግንቦት 11 ቀን 2012
Deadline: June 8, 2020


© walia tender

Report Page