#ETH

#ETH


#AdigratUniversity

ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ከ414 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የማስፋፊያ ግንባታዎች እያካሔደ መሆኑን አስታወቀ። የዩኒቨርስቲው የግንባታ ፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ኪደይ ገብረማርያም ለኢዜአ  እንዳሉት፣ የፕሮጀክቶቹ ግንባታ ተማሪዎች፣መምህራንና የዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ ውብና ጽዱ የሆነ አከባቢ እንዲኖራቸው ለማድረግ ነው።

ዩኒቨርስቲው ለፕሮጀክቶቹ ከመደበው ገንዘብ ውስጥ በ327 ሚሊዮን ብር ወጪ ባለሁለት ፎቅ ዘመናዊ የመዝናኛ ማእከል ግንባታ በመፋጠን ላይ ነው ብለዋል። የመዝናኛ ማእከሉ በ2013 የትምህርት ዘመን ሙሉ በሙሉ ግንባታው ተጠናቅቆ ለአገልግሎት ሲበቃ ደረጃቸውን የጠበቁ የሬስቶራንት፤ የካፊተሪያ፤ የቤት ውስጥና ከቤት ውጪ ዘመናዊ መጫወቻዎችን እና ሌሎች የተለያዩ የስፖርት ማዘውተሪያዎች ይኖረዋል ተብሏል።

እንዲሁም በ87 ሚሊዮን ብር ወጪ በዩኒቨርስቲው ግቢ ውስጥ ከአስር ሄክታር በሚበልጥ ቦታ ላይ በሳርና በተለያዩ ችግኞች የማስዋብ ስራ በመጠናቀቅ ላይ መሆኑን ኢንጅነር ኪደይ ገልጸዋል። በተጨማሪም ከአንድ ነጥብ ሁለት ኪሎ ሜትር በላይ የውስጥ ለውስጥ መንገድ በኮብል ስቶን የማንጠፍ ስራ የተጠናቀቀ ሲሆን፣ነባር መንገድ የመጠገን ስራም በመፋጠን ላይ መሆኑን ተናግረዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለም ከ16 ሺህ በላይ መደበኛ ተማሪዎችን የሚስተናገዱባቸው እና 170 ብሎኮች የያዙ ነባር የማስተማሪያ ህንጻዎችን የማጽዳት ስራ ለማከናወን ዝግጅት መደረጉን ተናግረዋል።

VIA ENA

Report Page