#ETH
የኢትዮጵያና ኤርትራ ግንኙነት እየቀዘቀዘ መምጣቱ ተነገረ!
ከሃያ አመታት በኋላ ወደ ወዳጅነት ተመልሶ የነበረው የኢትዮጵያና ኤርትራ ግንኙነት ከአራት ወራት በላይ ሳይዘልቅ እየተቀዛቀዘ መምጣቱን ምሁራን ተናገሩ፡፡ ዛሬ በአዘማን ሆቴል “ፎረም ፎር ሶሻል ስተዲስ” ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ጥናታቸውን ካቀረቡት ምሁራን አንዱ የሆኑት አምባሳደር ህሩይ አማኑኤል የቅርብና አስቸጋሪ የሆነው የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ግንኙነት ከአራት ወራት በላይ መጀመሪያ በነበረው ስሜት መቀጠል አልቻለም ብለዋል፡፡
ይህ እንዲሆን ካደረጉ ምክንያቶች ውስጥ የኢጋድ ጉባኤ ላይ አለመሳተፏ፣ የቀይ ባህር ፎረም ላይ የኢትዮጵያ ሚና አለመለየቱ፣ የድንበር አከፋፈት ላይ ስምምነት አለመኖሩና በሱዳን ጉዳይ ላይ ተመሳሳይ አቋም አለመያዝ የሚጠቀሱ እንደሆኑ ተናግረዋል፡፡
የኢትዮጵያ የውጪ ግንኙነት ፖሊስ በአፍሪካ ቀንድና በመካከለኛው ምስራቅ በሚል መጠሪያ በተካሄደው በዚሁ መድረክ ላይ የምስራቅ አፍሪካ አገራት በመሰረተ ልማት እየተሳሰሩ መሄዳቸው ለንግድ ስራዎች ውጤታማነት የሚበጅ ቢሆንም ከደህንነት አንፃር እየተጤነ ሊኬድ ይገባዋል ተብሏል፡፡ በኬንያ ከላሙ ወደብ ጋር ተያይዞ የተጀመረው ግንኙነት፣ ከሱዳን ጋር በወሰንና በአባይ ውሃ ጉዳይ፣ ከግጭት ጠባሳ ያልሻረውን የሶማሊያ ጉዳይ እና የጅቡቲ ስትራቴጂካዊ ተፈላጊ አገር እየሆነች መምጣት በተለይ ኢትዮጵያ እያስተዋለች ልትሄድባቸው የሚገቡ ጉዳዮች እንደሆኑም ምሁራኑ ተናግረዋል፡፡
Via Sheger FM