#ETH
የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ም/ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ በአክቲቪስት ጀዋር መሐመድ ላይ የተከሰተውን ጉዳይ አስመልክቶ ከሰጡት መግለጫ የተወሰዱ አንኳር ነጥቦች:-
• ትናንት ማታ የተፈጸመው ድርጊት ስህተት ነው፤ ስህተቱን ማን እንደፈጸመው፣ ለምን ጉዳዩን ምሽት ላይ ማድረግ እንደተፈለገ አጣርተን እርምጃ የምንወስድ ይሆናል፡፡
• ዛሬ ለሞቱት ወገኖች በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ስም የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸዋል፡፡
• ዛሬ በተደረገው ሰልፍ ላይ ኦሮሚያን የግጭት አውድማ ለማድረግ የሚፈልጉ ኃይሎች ሰልፉ ላይ አስነዋሪ ተግባራትን ፈጽመዋል፡፡
• እነዚህ ኃይሎች ጉዳዩ የሃይማኖትና የብሔር መልክ እንዲይዝ ጥረት እያደረጉ ነው፡፡
• የተለያዩ አካላት ለውጡ ዘላቂነት እንዳይኖረው የተለያዩ ሙከራዎች ሲያደርጉ ነበር፡፡
• ዛሬ የተፈጸመው መሆን የሌለበት ነገር ነው፡፡
• መንግስት ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችን ለመከላከል ነው ለወንድማችን ጀዋርና ለሌሎች ከውጭ ለገቡ ሰዎች ጥበቃ የሚያደርገው፡፡
• አሳዛኝ ክስተቶች ዛሬ ተፈጽመዋል፣ የሕግ የበላይነትን ለማስከበርና ድርጊቶቹን የፈጸሙ አካላት ላይ መንግስት እርምጃ ይወስዳል፡፡
• በኦሮሞ ህዝብ መካከል ልዩነቶች እንዲፈጠሩ ገንዘብ መድበው እየሰሩ ያሉ አካላት ስላሉ ህዝባችን ነቅቶ መንቀሳቀስ አለበት፡፡
• የአገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶች ጉዳዩን ለማረጋጋት ላደረጋችሁት አስተዋጽኦ ልትመሰገኑ ይገባል፡፡
• ህዝባችንን ተጠቃሚ የማያደርግ ማንኛውንም ተግባር አንፈጽምም፡፡
• ከሌሎች ብሔር ብሔረሰቦች ጋር እኩልነት ላይ የተመሰረተ እና ለሁላችንም የምትሆን የጋራ አገር በጋራ ለመገንባት መስራት አለብን፡፡
• በኦሮሚያ ውስጥ ያሉት ብሔር ብሔረሰቦችን ለማቀፍና ምንም ዓይነት ችግር እንዳይገጥማቸው ለማድረግ የኦሮሚያ ቄሮዎችና ቀሬዎች መስራት አለባቸው፡፡
• አሁን ወንድማችን ጀዋር በሰላም ሁኔታ ውስጥ ነው ያለው፤ መንግስት የሚያደርግለት ጥበቃም ይቀጥላል፡፡
OBN