#ETH

#ETH


በአዲስ አበባ ሶስት ሰዎች ወንዝ ውስጥ ገብተው መሞታቸው ተገለጸ፡፡

የእሳትና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግኑኝነት ባለሙያ አቶ ስለሺ ተስፋዬ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት በከተማዋ በትላንትናው እለት ሶስት ሰዎች በወንዝ ውስጥ ገብተው ህይወታቸው አልፏል፡፡

የመጀመርያ የሞት አደጋ የደረሰው በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ ሁለት ኮካ የመዝናኛ ስፍራ ላይ በሚገኝው ወንዝ ውስጥ ሲሆን እድሜው በግምት 35 አመት የሆነ ወጣት ህይወቱ ሊያልፍ ችሏል፡፡

ሁለተኛው የሞት አደጋ የደረሰው ደግሞ በአቃቂ ክፍለ ከተማ ወረዳ ሰባት ጨሬ መድሀኒአለም አካባቢ እድሜው 30 ዓመት የሆነው ወጣት ወንዝ ውስጥ ገብቶ ህይወቱ አልፏል፡፡

ከላይ የተጠቀሱት የሞት አደጋዎች ምክንያት ሟቾች ወንዙን ለመሻገር፣ለመዋኘትና ለሌሎች አገልግሎቶች እንደሆነ በአካባቢዉ ነዋሪዎች ቢጠቀስም ፖሊስ ክስተቱን በመመርመር ላይ እንደሆነ ተገልጿል።

ሶስተኛው የሞት አደጋ የደረሰው ደግሞ በቦሌ ክፍለ ከተማ ሀሰን ኮንስትራክሽን አካባቢ አንድ ግለሰብ በፈሳሽ ማስወገጃ ውስጥ ገብቶ እንደሞተ ነው ኮሚሸኑ ያስታወቀው፡፡

በተያያዘ ዜና በትላንትናው እለት በከተማዋ አራት የእሳት አደጋዎች መከሰቱን ኮሚሽኑ ለኢትዮ ኤፍ ኤም አስታውቋል፡፡

አደጋዎች የደረሱት በጉለሌ ክፍለ ከተማ በወረዳ ስድስት ፖሊስ ጣበያ አካባቢ በሚገኝው የኩኪስ ማምረቻ እና መሸጫ ቤት የተከሰተ የእሳት አደጋ ነው፡፡

ሁለተኛው አደጋ የደረሰው ደግሞ እዛው ጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ ሰባት ሲሆን ሶስተኛ አደጋ የደረሰው በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ሰፈረ ሰላም ጭማድ ተብሎ በሚጠራው ባለቤትነቱ የሸበሌ ትራንስፖርት የሆነ ጋራዥ ላይ የተከሰተ የእሳት አደጋ ነው፡፡

አራተኛው አደጋ የደረሰው በአቃቂ ክፍለ ከተማ ወረዳ ስምንት ጨፌ ኮንዶሚኒየም ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው፡፡ በነዚህ አደጋዎች ሳብያም በግምት 2 ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት መውደሙ ተገልጿል።

ምንጭ፦ ኢትዮ ኤፍ ኤም

Report Page