#ETH

#ETH


#OLF 

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) በቀጣዩ ምርጫ በአገር አቀፍ ደረጃ እንደሚወዳደር አስታውቋል። በምርጫ ቦርድ የምዝገባ ሂደቱን ገና ያልጨረሰው ኦነግ ፤ በመላ ሃገሪቱ ምርጫ መወዳደር የሚያስችል ቁመና አለኝ ብሏል።

ከምርጫ ቦርድ የምዝገባ ሰርተፍኬት የማግኘት ሂደቱን ከጨረሰ በኋላ ተግባራዊ እንቅስቃሴ እንደሚጀምርም አስታውቋል፡፡ የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኦቦ ቀጀላ መርዳሳ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት አንድ ፓርቲ በመላ የሃገሪቱ ክፍል በነፃነት ተንቀሳቅሶ ቅስቀሳ እንዳያደርግና ምርጫውን በሰላም እንዳይሳተፍ ማድረግ ህገ ወጥ ነውና ከዛ መታቀብ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ አንዱ ፓርቲ የሌላውን እንቅስቃሴ ማደናቀፍና ዘመቻ ማድረግ እንደሌለበት፣በምርጫ ስነ ምግባር ደንቦች በአዋጁ የተካተተ ነው፡፡

በፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ የስነ ምግባር ደንብ ላይ የቃልኪዳን ሰነድም ተፈራርመናል ያሉት ኦቦ ቀጀላ ማንም የትም ሄዶ መወዳደር እንዲቻል የሚመለከተው ሁሉ በተለይ የመንግስት አካል የበኩሉን ሊወጣ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ፓርቲ የወከሉም በግል የሚወዳደሩም ከተፅዕኖ ነፃ ሆነው በሁሉም ቦታ በእኩልነት መወዳደር እንዲችሉ ፓርቲዎች አባላቶቻቸውንና ደጋፊዎቻቸውን ማስተማርና ማስገንዘብ አለባቸው ብለዋል፡፡ በቅርቡ በፀደቀው የፖለተካ ፓርቲዎችና የምርጫ አዋጅ መሰረት አንድ ፓርቲ ሃገር አቀፍ ፓርቲ ለመሆን 10 ሺህ አባላት እንዲኖሩት ያስገድዳል፡፡

ምንጭ፦ ኢትዮ ኤፍ ኤም 

@tsegabwolde @tikvahethiopia

Report Page