#ET

#ET


የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሚሊየን ማቲወስ ባለፉት 25 አመታት የተመዘገበው የቋንቋና ባህል እድገት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተናገሩ፡፡ 

የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሚሊየን ማቲወስ ይህን ያሉት በሀዋሳ ከተማ እየተከበረ ባለው የሲዳማ ብሄር ቋንቋ እና ባህል ሲምፖዚየም ላይ ባደረጉት ንግግር ነው፡፡

የሲዳማ ቋንቋና ባህልን ለማሳደግ ባለፉት 25 አመታት የተከናዎኑ ተግባራትን በአወንታ የጠቀሱት ርዕሰ መስተዳድሩ በቀጣይ መሰራት ያለባቸው ቀሪ ስራዎች መኖራቸውን አንስተዋል፡፡

የሲዳማ ህዝብ ለረጅም ዘመናት ከሌሎች ማህበረሰቦች ጋር በአንድነት አብሮ የኖረ አቃፊ ህዝብ መሆኑን በመግለጽ አዲሱ ትውል ይህን ተቀብሎ ማስቀጠል እንዳለበትም መልክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ 

የምንፈልገው እድገትና ለውጥ የሚመጣውም ከሌሎች ህዝቦች ጋር ያለንን አብሮነትና አንድነት አጠናክረን ስናስቀጥል ነው ብለዋል፡፡ ሀገራዊ ለውጡን በመደገፍ ዳር ማድረስ ከሁሉም የሚጠበቅ ተግባር መሆኑንም ነው ርዕሰ መስተዳድሩ የተናገሩት። በሲምፖዚየሙ ላይ የተለያዩ ጥናታዊ ጽሁፎች በምሁራን ቀርበው ውይይት ይደረግባቸዋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

Via #FBC

Report Page