EOTC

EOTC


ቅዱስ ፓትርያርኩ በደቡብ አፍሪካ ጁሐንስበርግ


ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ፣ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የደቡብ ኦሞና አሪ ዞኖች ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት፣ ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ የዳውሮ-ኮንታ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ የጠቅላይ ቤተክህነት የመምሪያ ኃላፊዎች ደቡብ አፍሪካ ጁዋንስበርግ ገብተዋል።

ቅዱስነታቸው ወደ ደቡብ አፍሪካ የተጓዙት የጆሐንስበርግ መንበረ ጵጵስና ጽርሐ ጽዮን መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን የተመሠረተበት ፳፭ኛ ዓመት በዓል ላይ ለመገኘት፣ቅዳሴ ቤቱን ለማክበርና በደቡብ አፍሪካ በተለያዩ ግዛቶች በሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት በመዘዋወር ምዕመናንን ለመባረክና ለማስተማር ነው። 

በደቡብ አፍሪካ ጁሐንስበርግ ጽርሐ ጽዮን መድኀኔዓለም ካቴድራል የተደረገላቸው የአቀባበል ሥነሥርዓት በፎቶ፦

(EOTC)



Report Page