EOTC
ቅዱስ ፓትርያርኩ በመልካም ጤንነት ላይ ይገኛሉ።
ጥር ፯ ቀን ፳፻ ወ ፲፬ ዓ.ም
አዲስ አበባ
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ባጋጠማቸው ህመም ምክንያት ህክምናቸውን በመከታተል ላይ ይገኛሉ። በዚህም መሰረት ቅዱስነታቸው በአሁኑ ሰዓት በመል ካም ጤንነት ላይ እንደሚገኙና ህክምናቸውን በንቃት እየተከታተሉ እንደሚገኙ ታውቋል።
ስለሆነም መላው የቅድስት ኦርቶዶከስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ምዕመናንና ምዕመናት ለቅዱስነታቸው መልካም ጤንነትን በመመኘት ከምታደርጉት ጸሎት ጎን ለጎን መጪው የጥምቀት በዓል በሰላም ፣በስምምነትና በአንድነት ተከብሮ መዋል ይችል ዘንድ ፍፁም ክርስቲያ ናዊ ሥነምግባርን በተላበሰ ጨዋነት ከምታደርጉት ጥረ ረት ጎን ለጎን አንዳንድ የሀገራችንን ሰላምና አንድነት የማይሹ አካላት የሀገራችን ቀደምት ሥልጣኔ መሰረት የሆነችውን የቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያናችንን በዓል ለማጠልሸትና የእኩይ ዓላማቸው ማሳኪያ ለማድረግ ከሚጥሩ አካላት ራሳችንን በንቃት በመጠበቅ እና በየዓመቱ እንደምናደርገው ሁሉ ከመንግ ሥት የጸጥታ አካላት
ጋር በመተባበር በዓለም ዓቀፍ ደረጃ በማይዳሰስ ቅርስነት የተመዘገውን የጥምቀት በዓላችንን የለአንዳች የጸጥታ ችግርና ኮሽታ እናከብር ዘንድ የተለመደ ትብብራችሁን እንድታደርጉ መንፈሳዊ መልዕታችንን እናስተላልፋለን።
ጥር ፩ቀን ፩፻ ወ ፲፬ ዓ.ም በመስቀል አደባባይ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች ያከናወኑትን መርሐ ግብር ተከትሎ የተከሰተውን ችግር በተመለከተም ቅዱስነታቸው በቅርቡ ጤንነታቸው ተመልሶ ወደ መን በራቸው ስለሚመለሱ ቅዱስነታቸው በርዕሰ መንበርነት በሚመሩት ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባዔ ክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ በሚገኙበት፤የመስቀል አደባባይን ታሪካዊ ዳራን፣ህግ፣ሥርዓትና ማስረጃን መሰረት ባደረገአግባብ በሚደረግ ውይይት እንደሚፈታ እንገልጻለን።
ይህንን ተግባራዊ ለማድረግም በቅዱስ ሲኖዶስና በከተማ አስተዳደሩ በኩል አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት የተጠናቀቀ በመሆኑ ቅዱስ ሲኖዶስ በሚወስነው ቀን ውይይቱ የሚካሄደው መሆኑን እየገለጽን አስከዚያው ድረስ ሁላችንም የቤተክርስቲያን ልጆች በትዕግስትና በክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር በታነጸ መልካም ጠባይ ፈጣሬ ዓለማት መድሃኔ ዓለም ለቅዱስ አባታችን ምህረቱን እንዲልክልን ከመጸለይ ጋር እንድትጠባበቁ ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተከክርስቲያን ከአደራ ጋር በድጋሜ መልዕክቷን ታስተላልፋለች።
(የኢኦተቤ ህዝብ ግንኙነት)