EBC

EBC


#ቦረና

የቡሳ ጎኖፋ ምክትል ኃላፊ ዶ/ር ማሊቻ ሎጄ ለኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የሰጡት ቃል ፦

- ቦረና ዞን በተፈጠረው ድርቅ ምክንያት የተረጂዎች ቁጥር እየጨመረ መጥቶ ቁጥሩ ከ604 ሺህ በላይ ደርሷል።


- ድርቁ በቦረና ብቻ ሳይሆን ሁለቱን የጉጂ ዞኖች ጨምሮ በ10 ዞኖች የተከሰተ ነው። ቦረና ግን ቆላማነቱ ከሌሎቹ አካባቢዎች ከፍተኛ በመሆኑ የጉዳቱ መጠንም በዚያው መጠን ሊጨምር ችሏል።


- " በድርቁ ምክንያት ሰዎች በምግብ አጦት ሰውነታቸው እንደተጎዳ ነው " የሚሉት ኃለፊው፣ በርሃብ ምክንያት የሞተ ሰው እንደሌለ ቦታው ድረስ ተገኝቼ ከአካባቢው ሰዎች አረጋጫለሁ " ብለዋል።


- በሁለት ወቅቶች (የካቲት እና ሰኔ) የድርቁ ሁኔታ ያለበትን ለማወቅ ጥናት ይካሄዳል በዚሁ መሠረት ዘንድሮም ድርቁ መቀጠሉ ስለተረጋገጠ ክልሉ ዕቅዶችን አውጥቶ በየደረጃው እየተንቀሳቀሰ ነው።


- በአራት ዙሮች ተከፍሎ ዕርዳታ እየተሰጠ ነው ፤ ለቦረና ብቻ እስከ ሦስተኛ ዙር በክልሉ እና ፌዴራል መንግሥት ትብብር ለ375 ሺህ ለሚሆኑ ሰዎች የምግብ ዕርዳታ ማቅረብ ተችሏል። በአራተኛው ዞር የተረጂዎች ቁጥር እየጨመረ ስለመጣ የተረጂዎች ቁጥር 604 ሺህ ደርሷል።


- በቦረና ሲረዱ ከነበሩት 600 ሺህ በላይ ሰዎች ላይ ሌሎች 263 ሺህ 139 አስቸኳይ የምግብ ዕርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው በጥናት ስለተረጋገጠ ክልሉ ባለው አቅም እየተንቀሳቀሰ ነው።


- በፌዴራል መንግሥትም ድጋፍ እንዲደረግ የተጠየቀው ከወር በፊት ስለሆነ አሁን ዕርዳታውን ለማድረስ ሁሉም አካላት እየተረባረቡ ናቸው።


- በፊት በየወሩ ሲረዱ የነበሩትን ጨምሮ በአጠቃላይ ከ800 ሺህ በላይ ዜጎች በየወሩ ያልተቋረጠ ዕርዳታ እንዲያገኝ ዕቅድ ውጥቶ ወደ ተግባር ተገብቷል።


- በፌዴራል መንግሥት አሁን እስካለንበት ወር ድረስ ከ90 ሺህ ኩንታል በላይ የምግብ ዕርዳታ ለአካባቢው ደርሷል። 


- ባለፉት ስድስተ ወራት ብቻ የእናቶች እና ሕፃናት ምግብን ጨምሮ ከ34 ሺህ ኩንታል በላይ አስቸኳይ የምግብ ዕርዳታ እንዲደርስ መደረጉን ገልጸዋል። 


- መንግሥታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች በኩል ከ300 ሚሊዮን ብር በላይ ለኅብረተሰቡ ተከፋፍሎ እንዲጠቀሙበት ተደርጓል።


- ሕዝቡ በመረዳዳት ባህሉ መሠረት እንዲደጋገፍ እያስተባበርን እንገኛለን።


- የውኃ አቅርቦትን በተመለከተ በክልሉ ውኃ እና ኢነርጂ ቢሮ አስተባባሪነት 21 የውኃ ቦቴዎች ውኃ በቋሚነት እያከፋፈሉ ይገኛሉ። 


- የእንስሳት መኖን በተመለከተ ከክልሉ ግብርና ቢሮ ጋር በመተባበር ማዳን የሚቻውን ሁሉ ለማዳን እና የእንስሳቱ ዝርያም እንዳይጠፋ በርብርብ እየሠራን እንገኛለን።


- ይህ ሁሉ እንቅስቃሴ ቢደረግም ችግሩ በጣም ሰፊ ስለሆነ የሚፈለገውን ዕርዳታ ማድረግ አልተቻለም። ይህ ችግር እየተጠራቀመ የመጣ ችግር ስለሆነ በተወሰነ እንቅስቃሴ ብቻ የሚፈታ ባለመሆኑ ክልሉ ሁሉንም አቅሙን አስተባብሮ እያንቀሳቀሰ ይገኛል ፤ በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት ችግሩን ሊቀንሱ የሚችሉ ሥራዎች ይሰራሉ።


- አስቸኳይ የመድኃኒት አቅርቦት፣ የእናቶች እና ሕፃናት አልሚ ምግቦች እና ሌሎች ሕይወት አድን ድጋፎች ስለሚያስፈልጉ ሁሉም አካላት በትብብር ሊሠሩ እንደሚገባ ተናግረዋል።

Report Page