#EASE2020

#EASE2020


How to view solar eclipse with out Eclipse glasses?

pls look this home made video that inform how we can use house made and low cost methods of viewing solar eclipse in Amharic.

ራሳችንን ከአደጋ በመጠበቅ ግርዶሹን ለማየት የሚረዱ መንገዶች

እንግዲህ በባዶ አይናችን በቀጥታ ፀሐይን ስንመለከት ጉዳት የሚደርስብን ከሆነ፤ ታዲያ እንዴት የፀሐይን ግርዶሽ ማየት እንችላለን?

የአነስተኛ ሽንቁር ቀዳዳ ሳጥን (Pin-hole Box )

ፒን-ሆል ወይም አነስተኛ ሽንቁር ቀዳዳ በርቀት ያለን አንድ አካል ገልብጦ እንደሚያሳይ ከብዙ ዘመናት በፊት ጀምሮ እናውቃለን፡፡ እንደውም በዝቅተኛ ክፍሎች ት/ቤት በነበርን ወቅት የፒን ሆል ሳጥን (አነስተኛ ሽንቁር ቀዳዳ ያለው ሳጥን) ሰርተን፤ እርሱን ተጠቅመን የዛፎችን እና የጓደኞቻችንንም ምስሎች ተገልብጠው ያየን አንጠፋም፡፡ አሁንም ፀሐይዋን በግርዶሽ ወቅት ለማየት የምንጠቀመው ይህንኑ መርህ ነው፡፡

ይህንን የፒን ሆል ሳጥን መስራት እጅግ ቀላል በመሆኑ ዛሬ በቤታችን ውስጥ በማዘጋጀት መጠቀም እንችላለን፡፡ ይህንንም ለመስራት የሚያስፈልገን ማንኛውም ልሙጥ ወረቀት ወይም የካርቶን ወረቀት ሲሆን፤ ወደ ፀሐይ ስናዞረው፤ በሌላኛው ጎን በኩል የፀሐይዋ ምስል ይታያል፡፡ ይህ ቀለል ያለ ሲሆን፤ የሚሰራው ሰው ብልህነት የሚወሰነው በሚሰራው ፒን ሆል አይነት፤ በማሳያ-ገጹ (ስክሪን)፤ የካርቶን ሳጥኑና የመሳሰሉትን ጉዳዮች ላይ ነው፡

የራሳችንን ፒን-ሆል ሳጥን እንደሚከተለው ማዘጋጀት እንችላለን፡፡ ረዘም ያለ ካርቶን ሳጥን ወስደው በአንደኛው ገጽ መሀል ላይ ይብጡት (ይብሱት)፡፡ ነጭወረቀት ወስደው ቀዳዳው ከተበሳበት ገፅ ተቃራኒ ባለው በውሰጠኛው በኩል ይለጥፉ፤ አጮልቀው ምስሉን የሚያዩበትም ቀዳዳ ከሳጥኑ በአንዱ ገፅ ላይ ያብጁ (ይቅደዱ)፡፡ ሌሎቹን ጎኖች በሙሉ ብርሃን እንዳይገባና ነጩ ወረቀት ላይ እንዳያርፍ ይዝጓቸው፡፡ ሳጥኑ በረዘመ ቁጥር፤ ተለቅ ያለ ምስል ማየት እንችላለን፡፡ ለተጨማሪ መረጃ የሚከተለውን ማገናኛ ተጭነው ይመልከቱ ፡

https://astroedu.iau.org/en/activities/1409/build-a-safe-sun-viewer/

ሌላው ሊታሰብበት የሚገባው ነገር አነስተኛው ቀዳዳው ምን ያህል መሆን እንዳለበት ነው፡፡ አነስ ያሉ ቀዳዳዎች ጥርት ያሉ ምስሎችን ይፈጥራሉ ፡፡ ሆኖም ግን ፣ አናሳ ምስሎችንም ይፈጥራሉ፡፡ በተጨማሪም ፣ ቀዳዳው በጣም ትልቅ ከሆነ ልክ እንደ አነስተኛ-ቀዳዳ እንዲሆንና የፀሐይ ምስል እንዲፈጥር ለማድረግ የማያ-ገጹን ወደ ኋላ ማራቅ ያስፈልጋል፡፡ ይህ ካልሆነ ግን፣ ሊያዩት የሚችሉት የራሱ የቀዳዳውን ጥላ ብቻ ነው! ከማያ-ገፁ ርቀት ጋር የሚጣጣሙ የተለያዩ መጠኖችን ግርዶሹ ከመምጣቱ በፊት ባሉት ቀናት ውስጥ መሞከር ያስፈልግዎታል።


Report Page