Dilla Bule Shakiso

Dilla Bule Shakiso


የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የኮሚኒኬሽን ዋና ዳይሬክተር ሳምሶን ወንድሙ ፦

" ይሄን መንገድ በአስፓልት መንገድ ደረጃ ለማሳደግ በያዝነው በጀት አመት እቅድ የተያዘው ጨረታ የማውጣት ከዛ የጨረታውን ሂደት አጠናቆ አሸናፊ ከሚሆነው የስራ ተቋራጭ ጋር የኮንትራት ውል ስምምነት በመፈራረም በቀጣይ በጀት አመት ወደ ግንባታ ማሸጋገር ነው። 

በያዝነው በጀት አመት ጥምቅት መጨረሻ ጨረታ እንዲወጣ ተደርጓል። ከዛም በኃላ ዶክመት ግምገማ ሂደት እንዲከናወን ተደርጓል።

በአሁን ሰዓት የጨረታ ዶክመንት ግምገማ ሂደቱ ተጠናቆ የመንገድ ግንባታውን ፋይናንስ የሚያደርጉት ባድያ እና ኦፔክ ፈንዶች ናቸውን የጨረታ ሰነድ ግምገማ እንዲላክላቸው ተደርጓል። 

በዚህ መሰረት አሁን ላይ የፋይናሰሮቹ ምላሽ እየተጠበቀ ነው። ምላሹን መሰረት አድርጎ ቀጣይ ተግባራት ይከናወናል። 

... ከእኛ መስራቤት እቅድ አንፃር ከታየ እስከ ሰኔ መጨረሻ ድረስ የጨረታ ሂደቱን የማጠናቀቅ፣ ስራ ተቋራጩን የመለየት እና የኮንትራት ውል ስምምነት የመፈረም እቅድ ተይዟል። 

ከዚህ በኃላ ፋይናነሰሩ አንዱ መስፈርት በዚህ መስሪያ ቤት የተካሄደ የጨረታ ግምገማ ሰነድ ማፅደቅ አለበት። ካፀደቀ በኃላ ምላሽ ሲሰጥ ነው ወደ ቀጣይ ትግበራ የሚገባው። ከፋይናነሰሩ ምላሽ ይጠበቃል እስካሁን ዘግይቷል። ፋይናነሰሩ ምላሽ እንዲሰጠን በእኛ በኩል የመግፋት ስራ እየተናወነ ነው።

የፋይናነሰሩ ምላሽ ባልተገኘበት ሁኔታ የቀጣይ ሂደቱን ይሄ ነው ማለት ያስቸግራል። "

(ከኢቲቪ ቃለ መጠይቅ የተወሰደ)

Report Page