Diet & Mental Health

Diet & Mental Health

Crohn’s & Colitis Ethiopia | Dr. Kaleb Yirgashewa & Dr. Armoniam Mulatu Teshome

የአመጋገብ ስርዓት እና የአይምሮ ጤና

አካላዊ ጤና እና ምግብ ያላቸውን ተዛምዶ በተመለከተ ለረጅም ጊዜ የጥናት እና ምርምር ዋና ርዕሰ ጉዳይ ነበር። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን፣ የአመጋገብ ሥርዓት እና የአይምሮ ጤና ስላላቸው ግንኙነት ማወቅ ልዩ ትኩረትን አግኝቷል።

✔️አንጎላችን የገንቢ ምግቦች እንዲሁም ንጥረ ምግቦች አቅርቦትን በከፍተኛ መጠን ይፈልጋል።  አንጎላችን በቀን ውስጥ ከምንጠቀመው ምግብ የምናገኘውን ጉልበት በአማካኝ ሃያ በመቶ ፍጆታን ይጠቀማል ።

✔️በተጨማሪም ስልሳ በመቶ ስብ ሲሆን ከፍተኛ የኮሌስትሮል ክምችት እና እንደ ኦሜጋ-3 ያሉ Polyunsaturated fatty acids/PUFA/ የተሰኙ የስብ አይነቶችን ይዟል። ኦሜጋ-3 fatty acid እንደ አሳ፣ የባህር ምግቦች እና ሣር በል የበሬ ሥጋ ውስጥ ይገኛል።

✔️አንጎላችን የተገነባበት ሞኖአሚን የነርቭ አስተላላፊዎች/ Monoamine neurotransmitters/፣ የነርቭ ሥር ሽፋን/Myelin/፣ እና ገለፈተ ስስ የነርቭ ህብር ህዋስ ሽፋን/Neuronal Membrane/ በበቂ የንጥረ ምግብ አቅርቦቶች ላይ ይደገፋሉ።ለዚህም ነው የአመጋገብ ስርዓታችን በተለያየ መንገድ የአዕምሮ ጤና ላይ ተፅዕኖ ያደርጋል የሚባለው፡፡

👉ደካማ የአመጋገብ ስርዓት ለወረደ ስሜት አንደኛው ምክንያት ሊሆን ይችላል። በሌላ ጎኑ ደግሞ ተገቢ የአመጋገብ ስርዓት አካላዊ ጤናን ከመጠበቅ በተጨማሪ የአይምሮ ጤናን ጉልህ በሚባል ደረጃ ያሻሽላል። ጥናቶች እንደሚያሳዩት፤ ቀጣይነት ባለው መልኩ "የሜድትራኒያንን የአመጋገብ ስርዓት" መከተል በሰውነታችን ውስጥ የሚለቀቁ ብግነት ጠቋሚ ንጥረ ነገሮችን እንደሚቀንስ ታይቷል። ይህ የአመጋገብ ስርዓት በውስጡ በዋናነት ፍራፍሬዎች፣ አታክልት፣ ለውዝ እና ጥራጥሬዎች ያካተተ ሲሆን፣ በመጠነኛ መልኩ ደግሞ የዶሮ ሥጋ፣ እንቁላል እና የእንስሳት ተዋጽኦ ናቸው፡፡ በተጨማሪም አልፎ አልፎ ቀይ ሥጋን መጠቀምን ያካትታል። ይህ የአመጋገብ ስርዓት በድባቴ የመጠቃት እድልን ይቀንሳል።

👉በተቃራኒው በጠጣር ቅባት የበለጠጉ ከፍተኛ ሀይል ሰጪ ምግቦች የሰውነታችንን የመከላከል አቅም ባልተፈለገ መልኩ በማነቃቃት የአይምሮን ጤና፤ ይህም የማሰብ፣ የመገንዘብ፣ የመረዳት/Cognitive Function/ አቅም መዳከም፤ ከማስታወስ ችሎታ ጋር በተገናኘ የሚሰራውን የአይምሮ ክፍል/የHippocampus'ን/ ሥራ ማዛባት፤ እንዲሁም ወደ አንጎላችን ከሚፈሰው ደም ውስጥ የሚገኙ አንዳንድ ንጥረ ነገሮችን በማገድ የሚያገለግለውን በአንጎላችን ውስጥ ከሚገኙ የተሻሻሉ ቅንጣት የደም ሥሮች የተሠራውን ይህን ማገጃ ይጎዳል። የተለያዩ የአይምሮ ጤና ችግሮች፣ እንደ የስሜት/Mood/ መረበሽ ያሉ በሰውነት ውስጥ ከሚገኝ ከፍ ያለ የብግነት መጠን ጋር ተያያዥነት አላቸው፤ በተጨማሪም በጠጣር ቅባት የበለጠጉ ከፍተኛ ሀይል ሰጪ ምግቦች በአዕምሮ ጤና ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ አላቸው።

👉ምግቦች አጠቃላይ የአይምሮ ጤና ላይ የሚያመጡትን ተፅዕኖ ለማሳየት በቅርቡ የተደረሰበት ማብራሪያ እንደሚያሳየው፦ ስርዓተ አመጋገብ በሆድ እቃችን ውስጥ የሚገኙ ረቂቅ ተህዋሳት ላይ የሚያመጣው ተፅዕኖ ነው። በሆድ እቃ ውስጥ የሚገኙ እና የሚኖሩ ረቂቅ ተህዋሳት በትሪሊየን የሚቆጠሩ የደቂቅ ዘአካል ስብስብ ናቸው፤ ይህም የተለያዩ ባክቴርያ፣ ቫይረስ፣ ነጠላ ህዋስና ደቂቅ ዘአካሎችን ያካትታሉ።

እነኚህ ረቂቅ ተህዋሳት ከአንጎላችን ጋር በሁለትዮሽ መንገድ መስተጋብር ያደርጋሉ፤ እነዚህም

🟣በነርቭ ስርዓተ መንገድና

🟣የብግነት ንጥረ ነገሮች መለቀቅ እንዲሁም በሰውነታችን የሚሰሩ ንጥረ ቅመሞችን በመጠቀም ነው።

ጤናማ ያልሆነ የሆድ እቃ ረቂቅ ተህዋሳት እንዲፈጠሩ ከሚሆኑበት ምክንያቶች ውስጥ፤ አነስተኛ አሰር ያለው ማዕድ፣ በጠጣር ቅባት የበለጠጉ ምግቦች፣ የተጣሩ ስኳሮች እና ኢተፈጥሮአዊ ማጣፈጫዎች በምንጠቀምበት ጊዜ ነው። ይህ አይነቱ ስርዓተ ምግብ የሆድ እቃን መዋቅር እንዲሁም የአንጀታችንን ጎጂ ንጥረ ነገሮች በማጣራት ወደ ሰውነታችን እንዳይሰርፅ የማገድ ሥራን ያዛባል።


✅️ስለዚህም የአመጋገብ ስርዓታችን በተለያየ መንገድ የአዕምሮ ጤና ላይ ተፅዕኖ እንዳለው በመገንዘብ የአዕምሮ ጤናን ለመደገፍ ፤ የአመጋገብ ስርዓታችንን መቆጣጠር እጅግ አስፈላጊ ነው። እንደ፦ አሳ፣ የባህር ምግቦች፣ ባቄላ፣ ጥራጥሬዎች፣ ቅጠላ ቅጠሎች፣ አታክልት፣ የወይራ ዘይት፣ እርጎ፣ የመሳሰሉ ምግቦችን መጠቀም ስኬታማ እና በአንፃራዊ መልኩ ደግሞ ቀላል በሆነ መንገድ የአይምሮ ጤናን ለማሻሻል እንዲሁም ከአይምሮ ህመም ለማገገም አይነተኛ መንገዶች ናቸው።

በቀጣይ ሳምንት ስር የሰደዱ ህመሞችና የአእምሮ ጤና ጋር በተያያዘ ሰፋ ያለ ማብራሪያ፣ ተግባራያዊ ማሳያዎችና መፍትሔዎችን ይዘን እንቀርባለን፡፡

ይከታተሉን!

Report Page