Deeper– Chapter 1 :JESUS

Deeper– Chapter 1 :JESUS

Dane Ortlund

I love it when a book on holiness starts with Jesus. Not as a means to show His holiness and scold you for not looking like him. ነገርግን ከስሙ ጋር የተላመድን ሰዎች ስለሆንን አውቀን የጨረስነው መስሎን እንዳንታለል ጠንከር ባለ ማሳሰቢያ ይጀምራል። ብዙዎቻችን ነገረ ክርስቶስ ላይ የምንለውን ብዙ እውነት ሸምድደናል። አባቶች ከዘመን ዘመን ባስተላለፉት summary እንስማማለን። ልናሻሽለውም ስላልቻልን ይዘነው ቀጥለናል። 

ኢየሱስ ግን የሚውጠነጠን ፅንሰ ሀሳብ ወይ ደግሞ ምትሀታዊ ሀይል አይደለም። He is an actual person to be related to. የሚታመን፣ የሚወደድ፣ የሚናገር፣ የሚደመጥ ማንነት ነው። እድሜ ዘመናችንን ሁሉ ብንመራመረው አንጠፍጥፈን የማንጨርሰው ውቂያኖስ ነው። There's more wondrous depth to discover. Even in these 7 regions Dane chose to highlight as they pertain to spiritual growth– I'm compelled to read them prayerfully so that I dont reduce his attributes to "manageable predictable proportions."

1, Ruling –

ልዑል ሆይ በአለማት ሁሉ ትልቁ ስልጣን የአንተ ነው። ፍጥረታትን የምታስተዳድረው አምላክ ደግሞ የእኔ ትንሽዬ ህይወት ውስጥ የሚፈጠረውን ጠንቅቀህ ታውቃለህ። ሁሉን ስለምታይ ፍርድህ አይዛነፍም። ፍፁም ነው። (1 ቆሮ 4:5 ካንተ የሚሸሸግ ስውር motive እንኳን የለም። ስለራሴ የማይገባኝ ሁሉ ይገባሀል። በአይኔ ባላይህም በህይወቴ ካሉት ነገሮች ሁሉ እውነት እንደሆንክ እርግጠኛ የምሆነው በአንተ ነው። ሁሉ በአንተ ተጋጥሟልና ያላንተ ይፈረካከሳል። ይፈርሳል። (ቆላሲስ 1:17) በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ ለስምህ ይንበረከካሉ። አንተን በክብርህ ያየህ “ባየሁትም ጊዜ እንደ ሞተ ሰው ሆኜ ከእግሩ በታች ወደቅሁ።”( ራእይ 1፥17) ነበር ያለው። ቃልህ ውስጥ ያለውን ይሄን እውነት እንደሚረዳ ሰው ሊኖረኝ የሚገባው አክብሮታዊ ፍርሀት ይበልጥ እንዲበዛልኝ በዚህ እውነት ልቤን ቃኘውና እኔም በፊትህ ልራድ፣ ልቅለጥ።

 

2, Saving

ቆስዬ አግኝተህ ያከምከኝ ረዳት ብቻ አይደለህም። በበደሌና በሀጥያቴ ሙት ሳለው የደረስክልኝ ታዳጊ አዳኜ ነህ። ሉቃስ 7:36-50 ላይ እንዳለው ምሳሌ ልከፍለው የማልችለው የ 500 ዲናር ባለዕዳ ነበርኩ። ጌታ ኢየሱስ እኔን ለማዳን የወረድክበትን ርቀት ማሳነስ ከጀመርኩ 50 ዲናር ብቻ እንደተበደረ ሰው ሊሰማኝ ይችላል። ከአንተ ተቃራኒ በሆነ መንገድ እየተንደረደርኩ ነበር። ደርሰህ አመፄን አሸነፍከው። እውር ነበርኩ። ብርሀን ሰጠኸኝና ምን ያህል እንደምታስፈልገኝና ፍላጎቴን ሁሉ ለመሙላት በቂ መሆንህን መመልከት ቻልኩ። አንዳንዶች እንደሚሉት እየሰመጥኩ እያለ ያገኘሁህ life preserver አይደለህም። ከበላኝ የጥፋት ውሀ በታች የሰጠምኩትን በድን ነው ነፍስ የዘራህብኝ። ለእያንዳንዷ እስትንፋስ ያንተ ባለዕዳ ነኝ።


3 Befriending

You are both lion and the lamb, transcendent and immanent, far and near, great and good, king and friend. The dearest and truest friend one can have! መፅሀፍ እንደሚል ወዳጅ በክፉ ቀን ይጠጋጋል እንጂ አይሸሽም። ጓደኛ አብሮ ይቆማል፣ ሸክምን ይጋራል፣ ያዳምጣል። በሚፈለግበት ጊዜ ሁሉ ይገኛል። ዩሃንስ 15:15 እንደሚለው የልቡን ሚስጥር ያካፍላል። የዘላለም እቅድህ ውስጥ እንድንሳተፍ inner circle'ህ ውስጥ አካትተኸናል። የሀጥያተኞች ወዳጅ ነህና በደለኝነቱን የተረዳ አይሸሽህም። ፀፀትና ሀፍረት ያጎሳቆለውን ፍቅርህ አይገፋውም። (ሉቃስ 15:1) ስበድልህ ንዴትህ እስኪበርድ አኩርፈህ አትርቀኝም። እንደ employee treat ብታደርገኝ ምን ይውጠኝ ነበር?!

4, Persevering :

ከሰው ጋር ያለ ህብረት ሁሉ ይዋዥቃል። ቃል ገብተን ለተሰጠንባቸው ነገሮች ጭምር መፅናት ይከብደናል። ትዳር ኪዳን ላይ የሚመሰረተውም ለዚህ ነው። እንደስሜት በሚቀያየር ነገር ላይ መቆም አይችልም። አንተ ግን ልዩ ነህ። የወደድካቸውን እስከመጨረሻ ትወድዳለህ። (ዩሃ 13:1) ፍቅርህ ተንጠፍጥፎ የሚያልቅበት ቀነ ገደብ የለም። የሆነ ቀን ላይ ለምናምነኛ ጊዜ ስወድቅ "You have failed him enough" የሚል alarm አይጮህብኝም። በቅድስና ለማደግ ይህ እውነት ጥርት ብሎ ሊገባኝ ይገባል። በመዳፍህ ስለቀረፅከኝ I can't sin my way out of your grip. የሮሜ 5 logic ይህ ነው። ገና ደካማ ሳለው ሞተህልኛል። አሁን የራስህ አድርገህ ከገዛኸኝ በኋላ ትተወኛለህ ብዬ አልሰጋም።


5, Interceeding-

ከውልደትህ አንስቶ ህይወትህ፣ ሞትህ፣ ትንሳኤህ፣ እርገትህና አሁን ላይ ያለው የመማለድ አገልግሎትህን ሁሉ ማሰላሰል ለቅድስና ወሳኝ ነው። (ሮሜ 8:34) በማንኛውም ጊዜ፣ ሳስደስትህም ሆነ ስበድልህ ያንተ ምልጃ አይቋረጥም። በቀራንዮ መስቀል ላይ እንዳደረከው የማደርገውን ሳላውቅ ሳምፅ ምህረትህን ታበዛልኛለህ። አሁን በዚህች ቅፅበት ሰው የማዳን ተልዕኮህን ስላጠናቀቅክ ያለስራ አልተቀመጥክም።

ምክኒያቱም አንተን በማመን ለሀጥያታችን ስርየት ባገኘንበት እለት ዳግም ሀጥያትን ያለመስራት ልዕለ ተፈጥሯዊ ፍፅምናን አልተቀበልም። አሁንም ያለነው በወደቀች አለም፣ የወደቀን ስጋ ስጋ ለብሰን ነው። ስለዚህ ምልጃህ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የተሰራውን ስራ ለየዕለቱ ህይወቴ የሚያስፈልገኝን ፀጋ ያስገኝልኛል። (ዕብ 7:25) አብሮኝ የሚቆም አንድ ሰው ቢጠፋ እንኳ አብ ፊት ስለኔ ቆሞ የምትከራከር ጠበቃ ስላለኸኝ ሆድ አይብሰኝም። አንተ ደግሞ ስለእኔ ቅድስና ከእኔ በላይ committed መሆንህ ትልቅ እረፍት ነው።


6, Returning-

ይህች አለም በዚህ መልኩ ለዘለዓለም አትቀጥልም። የምፅዓትህ ቀጠሮ የምር ነው eventhough I might not feel it vividly. እስከዚያች ቀን ሙሽራችን የሆንከውን አንተን በመናፈቅ እንድንጠብቅ የአለምን ፍቅር ከውስጣችን አጥፋው። ከወረሰን ምድራዊነት ገላግለን። በዚህ የአለም ታሪክ ውስጥ ላይ በሚኖር የሆነ ዓመት፣ የሆነ ወር ፣ የሆነ ቀን ላይ ዳግም ትመጣለህ። “ቀን ቀጥሮአልና፥ በዚያም ቀን ባዘጋጀው ሰው እጅ በዓለሙ ላይ በጽድቅ ሊፈርድ አለው፤ ስለዚህም እርሱን ከሙታን በማስነሣቱ ሁሉን አረጋግጦአል።”(ሐዋ 17፥31) በዚያች እለት ስለስንፍናዬ፣ ወደአንተ ማደግ በምችልበት ልክ አለማደጌንና ቡዙ አለማፍራቴን እያሰብኩ መቆጨት አልፈልግም። ዛሬ big deal የሚመስሉኝ የማካብዳቸው ነገሮችን የዛኔ እንደምንቀው በመረዳት እንድኖር እርዳኝ። ዘላለምን በግንባሬ አትምልኛ በየዕለቱ አንተን የማየት one day closer እንደሆንኩ በማሰብ ልትጋ።


7, Tender-

ከማቲ 11:29 የምማረው ይሄን ነው። ልብ የሁሉ መውጫ፣ ትክክለኛው ማንነት ከሆነ አንተ ትሁት በልብህም የዋህ ፥ የምትገኝ፣ ገር ነህ። በውስጤ ያለውን አስቀያሚነት ብቻ ብመዝን የቅዱሱ አምላኬ የአንተ ወደእኔ አብዝቶ መቅረብና መጠጋጋት ግራ አጋቢ ነው። It only works because of your tenderness in how you deal with sinners.

ሸክሜን ለማራፍ ወዳንተ ስመጣ የማልፍበት ረጅም የsecurity ፍተሻ የለም። ከእኔ በተሻለ ጉዳይ ተጠምደህ የምታስጠብቀኝ ሰልፍና ወረፋም የለም። የአንተን attention ለማግኘት ብዬ አበሳዬን አላይም። በጫጫታ መሀል እንድታደምጠኝ ጉሮሮዬ እስኪሰነጠቅ መጮህ የለብኝም። የማውቅህ እንዲህ ነው፥ ከነደቂቅነቴ ስታስተውለኝ፣ ከነበደለኝነቴ ስትጠጋኝ፣ ከነመከራዬ አብረኸኝ ስትቆም! አንተን የሰው ሀዘንና ባዶነት አያሸሽህም። ከተጠቁት ጋር አብረህ በsolidarity መቆምን ተክነህበታል።

ስከተልህና በቅድስና ለማደግ ስፍጨረጨር አንድ ቀን ሀጥያቴ ፀጋህን አንጠፍጥፎ ይጨርሰዋል በሚል ስጋት ከሆነ ማደግ እስከምችለው እንዳላድግ እንቅፋት ይሆንብኛል። ሀጥያት በበዛበት በዝቶ የሚትረፈረፍ ፀጋ እንዳለ እንዳይ እርዳኝ። አብዝቶ ራስን ከመመርመር በራስ መዋጥ እንጂ ምንም ደህና ነገር አይገኝም። አባቶች እንዳሉት for every look at myself help me to look up and take ten looks at Christ. ህይወት ማለት አንተን ማወቅ ነውና (ዩሃ 17:3) ከዛሬ ቀን ጀምሮ እስከእድሜዬ ፍፃሜ ድረስ ከመታወቅ በላይ የሆነውን፣ ማንም exhaust አድርጎ የማይጨርሰውን ኢየሱስ ክርስቶስ በማወቅ ለማደግ እንድወስን እርዳኝ።

Report Page