Decha
DOCH HDየዕውቅና ሽልማቱ ይበልጥ ለህብረተሰባችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ይበልጥ የሚንተጋበት አደራ ነው። የዴቻ ወረዳ ረዳት የመንግስት ተጠሪና የፖለትካና ሕዝብ ግኑኝነት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብዮት ዓለሙ።
"አገልጋይነት ክብር ነው" በሚል መሪ ሀሳብ በተካሄደው የዕውቅና ሽልማት መረሃ ግብር በአፈፃፀማቸው ላቅ ያለ ውጤት ላስመዘገቡ ተቋማትና ሠራተኞች የዋንጫና የሰርቲፊኬት ሽልማት ተበረከተላቸው።
በዕለቱ መረሃ ግብር የዕውቅና ዋንጫና የሰርቲፊኬት ሽልማትን የዴቻ ወረዳ ረዳት የመንግስት ተጠሪና የፖለትካና ሕዝብ ግኑኝነት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብዮት ዓለሙ ያበረከቱ ስሆን የተሰጠው የዕውቅና ሽልማት ይበልጥ ለህብረተሰቡ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት አደራ እና ሀላፊነትን መቀበል ነው ብሏል።
በዚህም :-
1. የዴቻ ወረዳ ፍርድ ቤት 1ኛ በመሆን የዋንጫና የሰርትፊኬት ተሸላሚ ሆኗል።
2. የዴቻ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት 2ኛ በመሆን የዋንጫና ሰርትፊኬት ተሸላሚ ሆኗል።
3. የዴቻ ወረዳ ንግድና እንዱስትሪ ጽ/ቤት 3ኛ በመሆን የዋንጫና ሰርትፊኬት ተሸላሚ ሆኗል።
4.የዴቻ ወረዳ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት 4ኛ በመሆን የሰርትፊኬት ተሸላሚ ሆኗል።
በተያያዘ ከተቋማት 3 የህዝብ አገልጋዮች በበጀት ዓመቱ ታማኝና ታታሪ እንድሁም የላቀ አፈፃፀም በማስመዝገባቸው የዋንጫና የሰርትፊኬት የዕውቅና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል ሲል የወረዳው ኮሙኒኬሽን ዘግቧል ።