Debol daily
👤 DMF
🎙#Debol_Daily
Interview with Dr. Robel Alemu Admassu
MD| Consultant OBGYN| Gyn_Oncologist : Association of German Gynecology oncology (AGO) certified
ደቦል
1. በ Gyn-oncology ሰብ ስፔሻሊቲ ለመስራት ምን አነሳሳዎት?
ዶ/ር ሮቤል
"በመጀመሪያ የቲም ደቦል ላደረገልኝ መጠይቅ በጣም አመሰግናለሁ።እኔ በጎንደር ህክምና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ 27ኛ ባች ስሆን አስቸጋሪውን የአምስት አመት ጨርሼ ኢንርንሺፕ የጀመርኩት በ2002ዓ/ም ነዉ።
እንደሚታወቀዉ ህክምና ተማሪዎች ስራ የሚጀምሩበትን የመጀመሪያ የት/ት ክፍል የመዉደድ እና inclined የመሆን ዝንባሌ አለ። እኔም የማህፀንና ፅንስ ት/ት ክፍል "ሀ" ብዬ ስራ የጀመርኩበት ስለነበር ወደዛ ልሳብ ችያለሁ።
በነበረኝ ቆይታ ያለዉን የሰዉ ሀይል እጥረት ፣ በጊዜዉ የነበረዉን ክፍተት ስለተረዳሁ በዚህ field ብቀጥል በምሰራዉ ስራ ደስተኛ እንደምሆን የተረዳሁት በጊዜ ነዉ።
ይሄን ተከትሎ በሌክቸረርነት ማዕረግ ከተቀጠርኩ በኃላ ለሀገራችን በዚህ ሙያ ትልቅ አስተዋፆ ካደረጉት ከዶ/ር አና ካይፈር እና ከዶ/ር ደብሩ ጋር የመስራት ከነሱ የመማር እድል አገኘሁ።
በጀርመን ሀገር ከሚገኙ ዩንቨርስቲዎች ጋር በመተባበር የተጀመረዉ የስፔሻሊቲ እና የሰብ ስፔሻሊቲ ፕሮግራም ዋናዉ ወደ ካንሰር ህክምና እንድሳብ የሆንኩበት ምክንያት ነዉ።"
ደቦል
2. የህክምና ተማሪዎች እና ሬዚደንቶች የወደፊት ዕጣ ፈንታ በእርስዎ እይታ ብሩህ ነው ብለው ያስባሉ?
ዶ/ር ሮቤል
"በሀገራችን በተለይ የሬዚደንሲ ፕሮግራም በስፋት ከተጀመረ ብዙ እሩቅ አይደለም። ይሄም ህክምናን በሀገራችን ገና ያልተነካ ብዙ እና ሰፊ እድል ያለዉ ያደርገዋል። ተማሪዎች እና ሪዚደንቶች አሁን በሚያዪየቸዉ እና በሚሰሟቸዉ ነገሮች Interest ሊያጡ አይገባም። ሀኪሞች ብዙ የሚሰሯቸዉ ስራዎች አሉ። ብዙ አቅም ያላቸዉ ወጣቶች አሉ። በእኔ እምነት ይሄ ትልቅ ሀይል ነዉ።ነገሮች ይስተካከላሉ።"
ደቦል
3. ለህክምና ተማሪዎች እና ሬዚደንቶች የሚያስተላልፋት መልዕክት ካለ?
ዶ/ር ሮቤል
"ህክምና እንደ ሙያ ትልቅ ነዉ። ትምህርቱን ከመረዳት ጎን ለጎን ከተገልጋዮች ጋር የሚኖረዉ መግባባት (Social aspect) እና Ethical ጉዳዮችን የያዘ ጥንቃቄ የሚፈልግ ስራ ነዉ።
የህክምና ተማሪዎች ከነዚህ ሀሳቦች የሚቀዱ እዉቀቶችን እና እዉነቶችን ከስር ጀምረዉ በመማር በዚህም መትጋት ይኖርባቸዋል።
ሬዚደንቶች በየፊልዳቸው ... አሁን አለም የደረሰበት ህክምና ምንድነዉ?!... እንዴትስ ወደዛ ደረጃ እንደርሳለን?!... በሚል መንፈስ መጓዝ አለባቸዉ።
ኢንስቲቱሽኖች ላይ በቅንነት አብሮ የመስራት ነገር ደግሞ በተለይ ትኩረት ሊሰጠዉ ይገባል ።"
ደቦል
4. የሚወዱት አነቃቂ ምሳሌያዊ አነጋገር?
ዶ/ር ሮቤል
"የምወደውን አነቃቂ ምሳሌያዊ ንግግር የምዋሰዉ ከዶ/ር ደብሩ ነዉ..."knowledge has no color don't stop to learn" "

Robel Alemu Admassu
MD| Consultant OBGYN| Gyn_Oncologist : Association of German Gynecology oncology (AGO) certified
@debolteam