DW
ከኢትዮጵያ አዕምሯዊ ባለሥልጣን የተገኘው መረጃ "አዕምሯዊ ንብረት ሐሳቦች፣ ፈጠራዎች፣ ምሥሎች፣ ሥዕሎች፣ ቅቦች፣ ሃውልቶች፣ ቅርፃ ቅርፆች፣ በቃላት፣ በእይታ፣ በሙዚቃ፣ በቲያትር የተገለጹ ሥራዎች ወይም የአእምሮ ሥራ ውጤቱ የንብረት መብት ያቋቋመ ይሁን አይሁን ግብሩ ከሚገለጽበት ልዩ ቁሳዊ ነገር ውጪ ህልውና ያለውን ነገር የሚገልፅ የሕግ ፅንሰ ሐሳብ" መሆኑን ይጠቅሳል። የአዕምሯዊ ንብረት እሴቶች "የሕግ ከለላ ካላገኙ በስተቀር ለፈጠሯቸው ወይም ላመነጯቸው ሰዎች መጠቀሚያ የመሆናቸው እድል ያነሰ ነው" ይላል የባለሥልጣኑ መረጃ፡፡ የዚህን ምክንያት ሲገልጽ "ንብረታዊ እሴቶቹን ለመፍጠር ከሚጠይቀው ወጪ ይልቅ እነሱን ለመቅዳት የሚያስፈልገው ዋጋ እጅግ ያነሰ በመሆኑ፣ በቀላሉ በሌሎች ሊወሰዱ የሚችሉ በመሆኑ" እንደሆነ አስፍሯል።