Construc 2

Construc 2



የቢሮ ግንባታዎች የጨረታ ማስታወቂያ
በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/ መንግስት በጎፋ ዞን መሎ ኮዛ ወረዳ ፋይናንስ ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ለመሎ ኮዛ ወረዳ የትም/ትእና ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት የቢሮ ግንባታ ሥራ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

1ኛ የዘመኑን ግብር ከፍሎ ንግድ ፍቃዱን ያደሰና የብቃት ማረጋገጫ ያለው ኮፒ ማቅረብ የሚችል
2ኛ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ኮፒ ማቅረብ የሚችል
3ኛ/ በሥራው ላይ ያለውን ማስረጃ የሚያቀርብ ኮፒ ማቅረብ የሚችል
4ኛ/ የሙያ ፈቃድ GC ወይም BC የሆነ እና ደረጃው 8 እና ከዚያ በላይ የሆነ
5ኛ መልካም የሥራ አፈፃፀም የ2011 ዓ/ም ማቅረብ የሚችልና ተደራራቢ ሥራ በእጁ የሌለ መሆኑን በወረዳው ደረጃ ማቅረብ የሚችል።
6ኛ/ የተጨማሪ እሴት ታከስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆነና ሴርተፈኬት ማቅረብ ሚችል።
7ኛ/ የግብር መለያ ቁጥር ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችል
የመሎ ኮዛ ወረዳ ፋይናንስ ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት በሚቀርበው የሥራ ዝርዝርና የግንባታ ዲዛይን መሠረት ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ አሸናፊው ድርጅት ሙሉ የግንባታውን ማቴሪያል በማቅረብ ሥራውን ለማከናወን ፈቃደኛ የሆነ፡፡

ጨረታው የሚከናወነው በግልጽ ጨረታ ሥነ-ሥርዓትና ይህንኑ አስመልክቶ በኢትዮጵያ ፌዲራላዊ ዲሞክራሲዊ ሪፐብሊክ መንግስት በወጣው የመንግስት ግዥ አዋጅ እና መመሪያ መሠረት ነው፡፡
ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጁ የተሟሉ የጨረታ ሠነዶችን የማይመለስ ብር 200 / ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመከፈል መሎ ኮዛ ወረዳ ፋይናንስ ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 8 ሰተገለጸው አድራሻ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የከፍያውም ዘዴ በጥሬ ገንዘብ ሲሆን፣ ክፍያውን በመፈጸምና የተጫራቾች ስም ለማስመዝገብ በተዘጋጀው ፎርም ላይ በመመዝገብና በመፈረም የጨረታ ሠነዱን መውሰድ አለባቸው፡፡ መ/ቤቱ ለሠነዱ መጥፋት ወይም መዘግየት ኃላፊነት የለበትም::
መ/ቤቱ ብቁ ተጫራቾች የመጫረቻ ሠነዳቸውን ዋና እና ኮፒውን በማዘጋጀት በጥንቃቅ በታሸገ በአንድ ወይም በሁለት ወጥ ፖስታዎች የሚወዳደሩበትን ዓይነት በፖስታው ላይ በመለየት ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት እስከ 8፡00 ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ሁሉም ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከላይ በሠንጠረዥ እንደተመለከተው ለሚጫረቱት ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማቅረብ አለባቸው:: ዘግይቶ ያቀረበ የጨረታ ሠነድ ውድቅ ይደረጋል ::
ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት መሎ ኮዛ ወረዳ ፋይናንስ ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት በቢሮ ቁጥር 1 በ21ኛው ቀን በ8፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ የጨረታ መክፈቻ ቀኑ በበዓል ቀን ወይም ቅዳሜ እና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው ሥራ ቀን ይሆናል፡፡

ግንባታው የሚከናወንበትን ቦታ ተጫራቶች በራሳቸው ወጪ ባለበጀት መ/ቤቱን በማስፈቀድ ማረጋገጥና መረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
6. ተጫራቾች ከላይ የተዘረዘረትን መሥፈርትና ማስረጃዎችን ማሟላት አለባቸው:: ይህንን ያላሟሉ ተጫራቾች ከውድድር ውጪ ይሆናል፡፡

ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ መሎ ኮዛ ወረዳ ፋይናንስ እና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ቢሮ ቁ 8 በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር ፡0916480564/0916320102 ወይም 0926567609 በመደወል መረጃዎችን ማግኘት ይችላሉ፡፡
በደ/ ብ/ ብ/ ህ/ ክ/ መንግስት የጎፋ ዞን የመሎ ኮዛ ወረዳ

ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ ቤት / ላሃ/



_______________________________
Category : Construction and Construction Machinery, Construction Service and Maintenance, House and Building Construction
Posted Date : አዲስ ዘመን መጋቢት 11 ቀን 2012
Deadline :2020-04-09[ሚያዝያ 1]

Report Page